AM/Prabhupada 0629 - እያንዳንችን የአብዩ ጌታ የተለያዩ ልጆች በተለያየ ልብስ (ገላ) ቀርበን ማለት ነው፡፡



Lecture on BG 2.13 -- Pittsburgh, September 8, 1972

የክርሽና ንቃታችንን ለማዳበር መረዳት የሚኖረብን ነገሮች ሶስት ናቸው፡፡ ብሆክታራም ያግና ታፓሻም ሳርቫ ሎካ ማሄሽቫራም ሱህርዳም ሳርቫ ብሁታናም ግያትቫ ማም ሻንቲም ርቻቲ፡፡ (ብጊ፡ 5.29) እያንዳንዳችን ደስታን ለማግኘት እና ለመርካት ብዙ ጥረት ስናደርግ እንገኛለን፡፡ ይህም የኑሮአችን ትግል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሶስት መመሪያዎች በጥልቅ ብንረዳ በመጀመሪያ አብዩ ጌታ ታላቁ አባታችን እንደሆነ አብዩ ጌታ የሁሉም ነገር የበላይ ባለንብረት እንደሆነ እና አብዩ ጌታ የበላዩ ጓደኛችን እንደሆነ እነዚህን ሶስት ነገሮች ብንረዳ ወዲያውኑ ሰላም የተሞላብን ለመሆነ እንችላለን፡፡ ይህም ወዲያውኑ ነው፡፡ ጓደኞችን ለማግኘት እና ከእነርሱም እርዳታ ለማግኘት ብዙ ጥረት እናደርጋለን፡፡ በቀላሉ ክርሽናን እንደ ታላቁ ጓደኛችን አድርገን የምንቀበለው ከሆነ ግን የጓደኝነት ችግራችን ሁሉ ሊጠፋ ይችላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽናን እንደ የበላዩ ባለ ንብረት መሆኑን ብንረዳ ችግራችን ሁሉ ሊፈታ ይችላል፡፡ ይህም ችግራችን በአብዩ ጌታ የቀረበልንን ነገሮች የራሳችንን ንብረት አድርገን በስህተት ሰለምናየው ነው፡፡ በስህተት እንዲህ ብለን እናስባለን፡፡ "ይህ መሬት ወይንም ይህ የአሜሪካ መሬት የአሜሪካኖች ነው፡፡" "የአፍሪካ መሬት ለአፍሪካኖች ነው፡፡" አይደለም መረዳት ያለብን የሁሉም ነገር ባለንብረት አብዩ ጌታ ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዳችን በተለያየ ልብስ ወይንም ገላ የተሸፈንን የአብዩ ጌታ ልጆች ነን፡፡ የአባታችንንም ሀብት ለመደሰት የመጠቀም መብት አለን፡፡ ይህም የሌሎችንን መብት ሳንነካ ነው፡፡ ልክ እንደ ቤተሰብ አስተዳደር፡፡ ከብዙ ወንድሞች እና እህቶች ጋር እንኖራለን፡፡ አባት እና እናቶቻችን ያቀረቡልንን ሁሉ እንድንበላ ሲያቀርቡልን እንበላለን፡፡ የሌሎችን ሳህን ግን አንቀማም፡፡ ይህ የስልጠና ምልክት አይሆንም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በአብዩ ጌታ ንቃት የዳበርን ከሆነ ወይንም በክርሽና ንቃት የዳበርን ከሆነ ሁሉም ዓይነት ችግር ሊጠፋልን ይችላል፡፡ የሕብረተሰብ ጥናት የሀይማኖት ጥናት የኢኮኖሚ መዳበር የፖሎቲካ ችግሮች ሁሉ ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ይህንን የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ በማስፋፋት ላይ እንገኛለን፡፡ ይህም ለሰው ልጅ እና ሕብረተሰብ ትልክ ጥቅም ይሰጣል ብለን እናስባለን፡፡ እኛም በአሁኑ ሰዓት የምንጠይቀው ነገር ቢኖር አዋቂ የሆኑት ሰዎች እና በተለይ የተማሪው ህብረተሰብ ይህንን እንቅስቃሴ እንዲገቡበት ነው፡፡ ይህንንም እንቅስቃሴ በሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ልትረዱት ሞክሩ፡፡ ብዙ መፃህፍቶችንም አትመናል፡፡ ቢያንስ ሁለት ደርዘን የሚሆን ተለቅ ተለቅ ያሉ መፃህፍቶችን አትመናል፡፡ እነዚህንም በፃህፍት በማንበብ እና ይህንንም እንቅስቃሴ በመረዳት ከእኛ ጋር መግጠም ትችላላችሁ፡፡ እናመሰግናለን፡፡ ሀሬ ክርሽና፡፡