AM/Prabhupada 0753 - እነዚህ ታላላቅ ሰዎች አንድ የመፃህፍቶቻችንን ጥቅል ወስደው በጥናት ላይ ይሰማሩ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

እነዚህ ታላላቅ ሰዎች አንድ የመፃህፍቶቻችንን ጥቅል ወስደው በጥናት ላይ ይሰማሩ፡፡
- Prabhupāda 0753


Room Conversation -- May 4, 1976, Honolulu

ፕራብሁፓድ፡ እነዚህ ሁሉ ትላልቅ ሰዎች አንድ የተጠቀለለ መጻህፍቶቻችንን እንዲወስዱ እና እንዲያጠኑ አድርጓቸው፡፡ ለእነርሱም ወጪ አይደለም፡፡ ነገር ግን በደስታ ግዜያቸው ከመጻህፍቶቹ የተወሰነ ያህል ቢያነቡ ጥሩ ነው፡፡ ሁሉም አዋቂ ሰዎች ይመስላሉ፡፡ በማንበብም ክርሽና ንቃት ምን እንደሆነ ሊረዱ ይችላሉ፡፡ በአባቶቻችሁ ትውውቅም ለእነዚህ ትላልቅ ሰዎች መፅሀፍቶቻችንን ለማስተዋወቅ ሞክሩ። በላይብረሪያቸው ሊያስቀምጧቸው ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለመዝናናት ግዜ ባገኙበት ቁጥር ግዜ ሁሉ አንድ መስመር እንኳን ቢያነቡ ይህ በጣም ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ድህርታጁምና፡ ልጆቻቸውም ሊያነቡት ይችላሉ፡፡

ፕራብሁፓድ አዎን ልጆቻቸውም ሊያነቡት ይችላሉ፡፡ ድህርስታጁምና፡ አባቴም በዓለም ሲዘዋወር እያለ የአንዳንድ ጓደኞቹ ልጆች ይህንን እንቅስቃሴያችንን ገብተው እንደሚሳተፉበት አይቶ ነበረ፡፡ አሁን ልጆቻቸው የእኛን እንቅስቃሴ ገብተው እንደሚሳተፉበት ተረዳ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ያድ ያድ አቻራቲ ሽሬስትሀህ ሎካስ ታድ አኑቫርታቴ (ብጊ፡ 3.21) እነዚህም የዓለም ትልቅ ሰዎች ይህንን መልእክት ለመረዳት ቢሞክሩ “ኦ በእርግጥ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ትክክለኛ ነው“ ብለው ቢረዱ በዚህም እውቀታቸው ምክንያት ሌሎች ብዙዎች ሊከተሉት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የዓለምን ታላላቅ ሰዎች የምንሰብክበት ጥሩ እድሉ ይህ ነው፡፡ ስለዚህ በትክክል እድሉን ተጠቀሙበት፡፡ ሁለታችሁም አዋቂዎች ናቸሁ፡፡ ስለዚህ ጥንቃቄ ወስዳችሁ አነጋግሯቸው፡፡ ከዚያም ሊረዱን ይችላሉ፡፡ ”ኦ እነዚህ ሰዎች በጣም ጥሩ እውነተኛ አንደበት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡“ ”እንደዚሁም ታላቅ እውቀት እና የአምላክም እውቀት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡“ ይህም የእኛን እንቅስቃሴ የሰመረ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡