AM/Prabhupada 0764 - ሰራተኞቹም እንዲህ አሉ፡፡ “ይህ ኢየሱስ ክርቶስ የሚባለው ከእኛ መሀከል በስራ ላይ የተሰማራ መሆን አለበት፡፡”



Lecture on SB 2.3.14-15 -- Los Angeles, May 31, 1972

ስለዚህ በየከተማው እና በየሰፈሩ እየሄዳችሁ ይህንን የክርሽና ንቃትን ለማስተማር ተነቃቁ፡፡ ወደ ሕይወትም መልሷቸው፡፡ ይህ ብስጭታቸውም ሁሉ ይጠፋል፡፡ የህብረተሰቡም መሪዎች የፖለቲካም ሰዎች ወዴት እንደሚሄዱ መገንዘብ አለባቸው፡፡ ስለዚህም እንዲህ ተብሏል፡፡ ”ካትሀ ሀሪ ካትሆዳርካሀ ሳታም ስዩህ ሳዳሲ ድህሩቫም“ (ሽብ፡ 2.3.14) ይህንንም የሀሪ ከትሀ ወይንም የክርሽና ንቃት ላይ ውይይት ብናደርግ ልክ የሽሪማድ ብሀገቨታምን ውይይት እንደምናደርግበት ”ሀሪ ከትሀ“ ይህም ከትሀ ”ሀሪ ከትሀ ኡዳርካህ ሳታም ስዩህ ሳዳሲ ድህሩቫም” ይህም ከድቮቲዎች ጋር በውይይት የተደረገ ከሆነ አንድ ሰው በትክክል ሊረዳው ይችላል፡፡ ይህ የሽሪማድ ብሀገቨታም መጽሀፍ በድቮቲዎች መሀከል ትልቅ ጥቅም ያለው ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ መፅሀፉን ይገዙት ይሆናል። ተመልክተውም ይህ ምንድነው ብለው ይጠይቁ ይሆናል፡፡ “የተፃፈ የሳንስክሪት ጥቅሶች ወይንም የሚጣል ወረቀት” ብለው ሊያዩት ይችላሉ፡፡ አያችሁ? ለምሳሌ ይህ ጋዜጣ ለእኛ እንደሚጣል ወረቀት ሆኖ ይታየናል፡፡ ምንም ግድ አይሰጠንም፡፡ ነገር ግን እነርሱ በጥንቃቄ በደረታቸው ላይ አስቀምጠውት ይገኛሉ፡፡ “ኦ ይህ በጣም ጥሩ ነው፡፡” (ሳቅ) ጋዜጣ በምእራባውያን አገር በጣም የተፈለገ ነው፡፡ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ነግሮኝ ነበረ፡፡ አንድ የክርስትያን ቄስ ወደ ሸፊልድ ክርስትናን ለማስተማር ሂዶ ነበረ፡፡ ሸፊልድ የት ነው? እንግሊዝ አገር ነው? "ጌታ እየሱስ ክርቶስ ያድናችኋል እያለም መስበክ ጀመረ፡፡“ ይህም ለሰራተኞች ለወዛደሮች ወዘተ ነበረ፡፡ ”ጌታ እየሱስ ክርስቶስንም መጠለያ የማታደርጉት ከሆነ ወደ ሲኦል ትሄዳላችሁ፡፡” ብሎ ነገራቸው፡፡ በመጀመሪያም ደረጃ የጠየቁት “ማነው እየሱስ ክርስቶስ? ቁጥሩስ ምንድን ነው?" ይህም ማለት እየሱስ ክርስቶስ ከሰራተኞቹ አንዱ ነው ብለው ስለገመቱ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰራተኛ ቁጥር ነበረው፡፡ (ሳቅ) ሰለዚህ ቁጥሩ ምንድን ነው ብለው ጠየቁ፡፡ እንዲህም ቄሱ መልስ ሰጠ፡፡ ”አይደለም፡፡ ክራይስት የአብዩ አምላክ ልጅ ነው፡፡ ቁጥርም የለውም፡፡ እዚህም የሚሰራ አይደለም፡፡“ ብሎ ነገራቸው፡፡ ከዚያም እንዲህ ብለው ጠየቁት፡፡ ”ሲኦል ማለት ምንድን ነው?" እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፡፡ “ሲኦል የረጠበ እና የጨለመ ወዘተ” ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህም ግዜ እነርሱም እራሳቸው በተቆፈረ ማይን ውስጥ ሰለሚሰሩ ዝም አሉ፡፡ ማይንም ሁልግዜ የጨለመ እና የረጠበ ነው፡፡ (ሳቅ) (ፕራብሁፓድም ሳቀ) ይህስ ሲኦል እና ይህ ማይን የሚባለውስ ልዩነቱ ምንድን ነው? እነርሱም ዝም ብለው ነበረ፡፡ ነገር ግን ቄሱ እንዲህ ብሎ ሲነግራቸው “በሲኦል ጋዜጣ የለም፡፡” ብሎ ሲነግራቸው “ኦ ኖ ይህ በጣም የሚያስከፋ ነው፡፡” ብለው መለሱ፡፡ ጋዜጣ በሲኦል የለም፡፡ (ፕራብሁፓድ ሳቀ) እንደዚሁም በአገራችሁ ብዙ ጋዜጣዎች ይታተማሉ፡፡ የታሰሩ ብዙ ጋዜጣዎችን ለህዝብ በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ፡፡