AM/Prabhupada 0765 - ሁሉም ነገር በምድር ላይ የክርሽና እንደሆነ እና የግላችን የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ ፈፅሞ መረዳት ይኖርብናል፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

ሁሉም ነገር በምድር ላይ የክርሽና እንደሆነ እና የግላችን የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ ፈፅሞ መረዳት ይኖርብናል፡፡
- Prabhupāda 0765


Lecture on SB 1.13.11 -- Geneva, June 2, 1974

አኪንችና፡ አኪንችና ማለት ምንም ዓይነት ቁሳዊ የሆነ ነገርን ሀብትህ አታድርግ ማለት ነው፡፡ “አኪንችና ጐቻራ” ንግስት ኩንቲ ክርሽናን ልክ እንደተቀበለችው እንዲህ አለች፡፡ “ውድ ክርሽና ሆይ አንተ አኪንችና ጐቻራ ነህ፡፡” (ሽብ፡1 8 26) አንተም ልትታወቅ ይምትችለው ምንም የዓለማዊ ሀብት በሌለው ሰው ነው፡፡ "አንተ ግን ለእኛ ብዙ የቁሳዊ ሀብቶች ሰጥተህናል፡፡ ታድያ እኛ እንዴት አድርገንህ ልንረዳህ እንችላለን?" የንግስት ኩንቲም ቁጭት ይህ ነበረ፡፡ “በጭንቀት ላይ እያለን ሁልግዜ ከእኛው ጋራ ነበርክ” “አሁን ግን መላ ቤተ መንግስቱን እና ሁሉንም ነገር ሰጥተህናል፡፡” “አሁን ደግሞ ወደ ድዋርካ እየሄድክ ነው፡፡ ይህስ ምንድን ነው ክርሽና?" "እኛ አሁን የምንመኘው ወደ እዛው ወደ ጭንቀቱ ዓለም ብንሄድ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ የችግር ግዜያችን አንተ ሁልግዜ ከእኛ ጋር ስለምትሆን ነው፡፡” ”አኪንችና ጎቻራ“ ክርሽና አኪንችና ጎቻራ ነው፡፡ ይህንን የቁሳዊ እና ዓለማዊ ሕይወት ለመደሰት የሚፈልግ ሁሉ የክርሽና ንቃታቸውን ለማዳበር የማይቻል ሆነው ያገኙታል፡፡ ይህም ትልቁ ሚስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ አለ፡፡ “ኒሽኪንቻናስያ ብሀገቨድ ብሀጃኖን ሙክሀስያ” (ቼቻ፡ማድህያ 11.8) ብሀገቫድ ብሀጃን ይህም ድቮቲ (አገልጋይ) መሆነ እና በክርሽና ንቃት መዳበር፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ለ “ኒስኪንቻናስያ” በዚህ ዓለም ላይ ምንም ቁሳዊ ሀብት ለሌለው ሰው ነው፡፡ ይህም ማለት በድህነት የተጠቃ ማለት አይደለም፡፡ ማወቅ እና መረዳት ያለበት ግን “ምንም ነገር የእኔ ሀብት አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር ግን የክርሽና ሀብት ነው፡፡” ”እኔ በቀላሉ የእርሱ አገልጋይ ነኝ፡፡“ ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል፡፡ ይህም “አኪንችና” ተብሎ ይታወቃል፡፡ እንዲህ ማሰብ ግን አይገባኝም፡፡ “ክርሽናን ከፊት አስቀምጥ እና ሁሉን የቁሳዊ ሀብት እንደ ምኞቴ እይዛለሁ፡፡” ማለት ግን ማታለል ማለት ነው፡፡ ሁሉም ነገር የክርሽና ሀብት እንደሆነ እና ማናቸውም ነገሮች የእኛ እንዳልሆኑ ሙሉ በሙሉ የተረዳን ሰዎች መሆን አለብን፡፡ በዚህም ህልውናችን ክርሽና የእኛ “ሱህርዳ” ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት እርሱ ለእኛ ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡ እንዴት እንደሚጠቅመንም አስቦ ሁሉን ያዘጋጅልናል፡፡ ቴሻም ሳታታ ዩክታናም ብሀጃታም ፕሪቲ ፑርቫካም ዳዳሚ (ብጊ፡ 10.10) ፕሪቲ ፑርቫካም ማለት ትልቅ ውሳኔ በማድረግ ማለት ነው፡፡ “ክርሽና በዚህ ዓለም የምፈልገው ነገር ምንም የለም፡፡ የምፈልገው ግን አንተን ብቻ ነው፡፡“ ና ድሀናም ና ጃናም ና ሱንዳሪም ካቪታም ቫ ጃጋዲሻ (ቼቻ፡ አንትያ 20.29) ይህ የቼይታንያ መሀፕራብሁ ትምህርት ነው፡፡ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ይህንን ትምህርት ደጋግሞ አስተምሮታል፡፡ ”ኒስኪንቻናስያ ብሀጋቫድ ብሀጃና“ ብሀገቨድ ብሀጃና ማለት እርሱ እራሱ ኒስኪንቻና ይሆናል ማለት ነው፡፡ ክርሽና እራሱ ከሁሉ በላይ ሀብት ያለው ነበረ፡፡ ትያክትቫ ሱሬፕሲታሀ ሱዱስትያጃ ሱሬፕሲታ ራጅያ ላክስሚም (ሽብ፡ 11.5.34) ቼይታንያ መሀፕራብሁ በጣም ቆንጆ የሆነች ባለቤት ነበረችው፡፡ እርስዋም የሀብት አምላክ ነበረች፡፡ ቪሽኑ ፕሪያ ላክሽሚ ፕሪያ ነገር ግን ለዓለም ህዝብ ጥቅም ሲል ምንም እንኳን እርሱ ራሱ ክርሽና ቢሆንም በምሳሌ ሊያሳየን እና ሊያስተምረን በቃ፡፡ በ24 አመቱም የመነኩሴነት ስርዓትን ወሰደ፡፡