AM/Prabhupada 1059 - እያንዳንዱ ፍጡር ከአብዩ የመላእክት ጌታ ጋር የተወሰነ ዓይነት ግኑኝነት አለው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

Everyone has got a Particular Relationship with the Lord - Prabhupāda 1059


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

አንድ ሰው የአብዩ ጌታ አገልጋይ ሆኖ በትሁት መንፈስ ሲያገለግል በቀጥታ ከአብዩ ጌታ ጋር ግኑኝነት እንደአለው የታወቀ ነው፡፡ ይህ ርእስም በጣም ጥልቅ የሆነ የትምህርት አይነት ነው፡፡ በአጭሩ ለመግለፅ ግን ..... አንድ ትሁት የጌታ አገልጋይ ከታላቁ ሽሪ ክርሽና ጋር በአምስት አይነት ደረጃ ግኑኝነቱን ሊያዳብር ይችላል፡፡ አንድ አገልጋይ ንቃቱ ባልዳበረ ደረጃ ላይ ሆኖ የሚያገለግል ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ አገልጋይ ንቁ በሆነ ደረጃ በትሁት ልቦና የሚያገለግል ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ አገልጋይ የአብዩ አምላክ ጓደኛ ሆኖ ለማገልገል ይችላል፡፡ አንድ አገልጋይ የአብዩ ጌታ ወላጅ ሆኖ ለማገልገል ይችላል፡፡ አንድ አገልጋይ በጋብቻ ፍቅር በተመሰረተ ግኑኝነት አብዩ ጌታን ለማገልገል ይችላል፡፡ አርጁና ከጌታ ጋር የነበረው ግኑኝነት በጓደኝነት ደረጃ ነበር፡፡ አብዩ ጌታ የትሁት አገልጋዩ ጓደኛ ለመሆን ይችላል፡፡ በእርግጥም በዚህ አይነት ጓደኝነት እና በዚህ ቁሳዊ ዓለም ዉሰጥ በሚገኘው ጓደኝነት ... ከምድር እስከ ሰማይ የሚያክል ወይንም ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ይህ ከጌታ ጋር ያለው የአርጁና ጓደኝነት በመንፈሳዊ አቅዋም በጣም የላቀ ነው፡፡ ይህም ማለት ሁሉም ፍጡር ይህንን የመሰለ ግኑኝነት ከጌታ ጋር አለው ማለት አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ፍጡር ከአብዩ ጌታ ጋር የተወሰነ ዘለዓለማዊ የሆነ ግኑኝነት አለው፡፡ ይህም የተወሰነው ከጌታ ጋር ያለን ግኑኝነታችን ሊነቃቃ የሚችለው የትሁት መንፈሳዊ አገልግሎታችንን በማዳበር ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ያለንበት ደረጃ ደግሞ ጌታን መዘንጋት ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር ያለንን ዘለአለማዊ ግንኙነትም ረስተናል፡፡ በብዙ ቢልዮን እና ትሪልዮን የሚቆጠሩት ነፍሳቶች ከጌታ ጋር የተወሰነ ዘለአለማዊ ግኑኝነት አላቸው፡፡ ይህም "ስቫሩፕ" ይባላል፡፡ በቅን ልቦና መንፈሳዊ አገለግሎትም ይህ ስቫሩፕ ሊነቃቃ ይችላል፡፡ ይህም ደረጃ የስቫሩፕ ሲድሂ ወይንም ጥራት ያለው ወይንም እንከን የሌለው የግኑኝነት ደረጃ ይባላል፡፡ አርጁና ትሁት አገልጋይ ነበረ፡፡ ከጌታም ጋር የነበረው ግንኙነት በጓደኝነት ደረጃ ነበር፡፡ አርጁና እንዴት የብሀገቨድ ጊታን መልእክት ተቀብሎ እንደነበረ መረዳት አለብን፡፡ መልእክቱንም ሲቀበል የነበረው ባህርይ በብሀገቨድ ጊታ በአስረኛው ምዕራፍ በደንብ ተገልጿል፡፡ እንዲህም ብሎ ተገልጿል፡፡ "አርጁና ኡቫቻ፡ ፓራም ብራህማ ፓራም ድሃማ ፓቪትራም ፓራማም ብሃቫን" "ፑሩሻም ሳስቫታም ዲቭያም አዲ ዴቫም አጃም ቪብሁም " (ብጊ፡ 10 12) "አሁስ ትቫም ርሳያህ ሳርቬ ዴቫርሲር ናራዳስ ታትሀ" "አሲቶ ዴቫሎ ቭያሳህ ስቫያም ቻይቫ ብራቪሲ ሜ" (ብጊ፡10 13) "ሳርቫም ኤታድ ርታም ማንዬ ያን ማም ቫዳሲ ኬሻቫ" "ናሂቴ ብሃጋቫን ቭያክቲም ቪዱር ዴቫ ና ዳናቫህ" (ብጊ፡10 14) አርጁና ብሀገቨድ ጊታን ከአብዩ ጌታ በጥሞና ካዳመጠ በኋላ እንዲህ አለ፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽናን እንደ ታላቁ ብራህማን አድርጐ ተቀብሎታል፡፡ "ብራህማን" እያንዳንዱ ፍጡር ብራህማን የተብሎ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን አብዩ የመላእክት ጌታ እንደ ታላቁ ብራህማን ወይንም እንደ ታላቁ ፍጡር ሆኖ ይታወቃል፡፡ "ፓራም ድሀማ" ማለት ደግሞ የሁሉም ፍጥረታት መጠለያ ማለት ነው፡፡ "ፓቪትራም" ማለት ደግሞ ከቁሳዊ እና ከዓለማዊ የተበከለ ይዘት ሁሉ ንፁህ የሆነ ማለት ነው፡፡ አብዩ ጌታ "ፑሩሻ" ተብሎም ይጠራል፡፡ ፑሩሻም ማለት ከሁሉም በላይ የሆነ ደስተኛ ማለት ነው፡፡ "ሻሽቫታም" ማለት ደግሞ ከሁሉም ፍጥረታት ቀዳማዊ የሆነ ወይንም የመጀመሪያው ሰው ማለት ነው፡፡ "ዲቭያም" ማለት ደግሞ መንፈሳዊ መልዓክ ወይንም የመላእክት ሁሉ አብይ ጌታ ማለት ነው፡፡ "አጃም" ማለት ደግሞ ፍፁም ያልተወለደ ማለት ሲሆን "ቪብሁም" ማለት ደግሞ የሁሉም ታላቅ ማለት ነው፡፡ አርጁና ለጌታ ክርሽና የቅርብ ጓደኛው ስለሆነ እንደጓደኝነቱ ለማወደስ ወይንም ለመደለል ፈልጐ ነው በማለት አንድ ሰው ሊያስብ ይችላል፡፡ ነገር ግን የብሀገቨድ ጊታ አንባቢዎች ይህ አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርባቸው አርጁና በሚቀጥለው የብሀገቨድ ጊታ ጥቅስ ላይ በማሰረጃ ሲያረጋግጥ ይገኛል፡፡ በዚህም ጥቅስ ላይ ይህ ግምገማ የተመሰረተው በሌሎች ባለስልጣኖችም ጭምር ነው፡፡ በዚህም ጥቅስ ላይ ክርሽና አብዩ የአምላክ አካል ስለመሆኑ የተገለፀዉ በእራሱ (አርጁና) ብቻ ሳይሆን በሌሎች የቬዲክ ባለሥልጣኖችምጭምር ሁሉ ነዉ፡፡ እነዚህም እንደ ናራዳ አሲታ ዴቫላ ቭያሳዴቭ ወዘተ የመሳሰሉት ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ እነዚህም በባህርያቸው እና በማንነታቸው የገነኑ ታላላቅ የቬዲክ ስነፅሁፍ መምህራን ናቸው፡፡ በመላ "አቻርያዎችም" (በተግባር እና መምሳሌ የሚያስተምሩ) ተቀባይነት ያላቸው ናቸው፡፡ ሰለዚህም አርጁና ለጌታ ክርሽና የገለጽክልኝን ሁሉ በሙሉ ልቦናዬ ፍፁም እውነት እንደመሆናቸው ተቀብያቸዋለሁ ብሎ ገለፀ፡፡