AM/Prabhupada 1060 - ብሀገቨድ ጊታን መረዳት ያለብን በጥሩ ልቦና እና በመልካም መንፈስ ጌታን በማገልገል ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 1059
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 1061 Go-next.png

Unless One Receives this Bhagavad-gita in a Submissive Spirit... - Prabhupāda 1060


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

"ሳርቫም ኤታድ ርታም ማንዬ" (ብጊ፡10 14) “የገለጽክልኝ ሁሉ ፍጹም እውነት እንደመሆኑ በሙሉ ልቦና ተቀብየዋለሁ” የአንተን ታላቅነት ወይንም የመላእክት ሁሉ አብይነትን በቀላሉ ለመረዳት ያዳግታል፡፡ በታላላቆቹ የአንተ አብዩ አምላክ ተወካዮች (ደሚጎዶች) እንኳን በጥልቅ ልትታወቅ አትችልም፡፡ የአንተ የአብዩ አምላክ ተወካዮች (ደሚጎዶች) እንኳን በጥልቅ ሊያውቁህ አይችሉም፡፡ ይህም ማለት የጌታን ሙሉ ባህርይ ከሰው በላይ የሆኑ ታላላቅ የአምላክ ተወካዮች እንኳን በጥልቅ ሊረዱት አይችሉም፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን እንዴት የሰው ዘር የአምላክ ትሁት አገልጋይ ሳይሆን የጌታ ክርሽናን ማንነት ሊረዳ ይችላል? ስለዚህ ብሀገቨድ ጊታን መረዳት ያለብን በጥሩ ልቦና እና በመልካም መንፈስ ጌታን በማገልገል ነው፡፡ አንድ ሰው ክርሽና እንደ ሰው ሆኖ ምድር ላይ በመምጣቱ ከሰው ጋር እኩል እንደሆነ አድርጐ መገመት አይገባውም፡፡ ክርሽናንም እንደ ተራ የሰው ፍጡር አድርጐ ማሰብ ወይንም እንደ ሌላ ታዋቂ ሰው አድርጐ ማሰብ አግባብ አይደለም፡፡ ጌታ ክርሽና አብዩ የአምላክ አካል ነው፡፡ ቢያንስ መልእክቱን በብሀገቨድ ጊታ እንደተዘረዘረው ወይንም አርጁና ገልጾ እንደተነተነው መቀበል ይኖርብናል፡፡ አርጁናም ብሀገቨድ ጊታን ከሚገልፀው ጌታ ለመረዳት የሚጥር ነበረ፡፡ ጌታ ሽሪ ክርሽና የመላእክት ሁሉ ጌታ ሰለመሆኑ ተረድተን መቀበል ይኖርብናል፡፡ ተረድተንም በትሁት መንፈስ በጥሞና መከታተል ይኖርብናል፡፡ አንድ ሰው ብሀገቨድ ጊታን በትሁት መንፈስ የማያዳምጥ ከሆነ ብሀገቨድ ጊታን ለመረዳት በጣም አዳጋች ይሆንበታል፡፡ ብሀገቨድ ጊታም ሚስጥር ሆኖ መልእክቱ ላይፈታለት ይችላል፡፡ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ የተጠቀሰውስ መልእክት ምን እንደሆነ መመርመር እንችላለን፡፡ የብሀገቨድ ጊታ ዓላማ የሰውን ልጅ ከቁሳዊ አለም ኑሮ እና ከድንቁርና ለማውጣት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ እያንዳንዱ ሰው በተለያየ ችግር ውስጥ ሰምጦ ይገኛል፡፡ አርጁናም በኩሩክ ሼትራ ጦርነት ሜዳ ላይ ቁሞ የመዋጋት ሀሳብ መከፈል እና ውጊያውን የመቀጠል ችግር ነበረበት፡፡ ቢሆንም ግን አርጁና ለጌታ ክርሽና ሙሉ ልቦናውን በመስጠቱ ይህ ብሀገቨድ ጊታ ለመዘመር በቃ፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ኑሮ ምክንያት አርጁናም ብቻ ሳይሆን ሁላችንም በብዙ አይነት ስጋት እና ጭንቀት ላይ እንገኛለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ ነፍሳችን በዚህ ጊዜያዊ ዓለም ውስጥ (አሳት) ተጠምዳለች፡፡ ቢሆንም ግን ነፍሳችን ጊዜያዊ አይደለችም፡፡ የእኛ ፍጥረት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ቢሆንም ግን በእዚህ በጊዜያዊው ቁሳዊው ዓለም ተጠምደን እንገኛለን፡፡ "አሳት" ማለት በዘለዓለማዊነት የማይኖር ማለት ነው፡፡ በብዙ ሚልዮን ከሚቆጠሩ ሰዎች መሀከል ስለ የእራሳቸው ማንነት የሚጠይቁ እና ... ...ለምን እዚህ የማይመች ዓለም ላይ መጥተው ለስቃይ እንደበቁ የሚያሰላስሉ የሰው ፍጡራን በጣም ትንሽ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ለምን እንዲህ አስቸጋሪ ኑሮ ውስጥ እንደወደቀ መጠየቅ አለበት፡፡ "ለምንድነው የምሰቃየው?“ ”እነዚህንም ስቃዮች ማቆም እፈልጋለሁ፡፡“ ”እነዚህንም ስቃዮች ለማቆም ብዙ ሙከራ አድርጌ ነበረ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ከንቱ ሆኖ ይታያል፡፡“ አንድ ሰው እንደዚህ ዓይነት አንደበት የሌለው ከሆነ ፍፁም ትክክለኛ አንደበት አለው ለማለት ያዳግታል፡፡ የሰው ልጅ ሕይወት የሚጀምረው እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች በአንደበታችን ሲያድሩ ነው፡፡ በብራህማ ሱትራ ይህ አይነቱ ጥያቄ ”ብራህማ ጂግናሳ“ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ”አታትሆ ብራህማ ጂግናሳ“ ማናቸውም የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ጌታን ለማወቅ በጥያቄ ያልተመሰረተ ከሆነ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ከንቱ ሆኖ ይገኛል፡፡ ይህንን የመሰለ ጥያቄዎች በአንደበቱ ካላደረ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዓለም ላይ እነዚህን የሚጠይቁ እና የሚያሰላስሉ ሰዎች ለምን በስቃይ እንደምንገኝ ከየት ወደዚህ ዓለም እንደመጣን ከሞት በኋላስ ወዴት እንደምንሄድ እነዚህ አይነት ጥያቄቆች በአንደበታችን ሲያድሩ ወይንም በአዋቂው ሰው አንደበት ሲያድሩ እነዚህ ሰዎች የዚህ የብሀገቨድ ጊታን መልእክት ለመረዳት ትክክለኛ እና ብቁ ተማሪዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ሰው ”ሽራድሀቫን“ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ማለት ለአብዩ ጌታ ጥልቅ የሆነ አክብሮት እንዲኖረው ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ አርጁናም ይህንን የመሰለ ትክክለኛ የአንደበት ምሳሌ ነበረው፡፡