AM/Prabhupada 1076 - ወደ ሞት አፋፍ ስንደርስ ወይ ወደ እዚህ ዓለም የመመለስ እድል አለን ወይንም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ዓለም የመሸጋገር እድል አለን፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

ወደ ሞት አፋፍ ስንደርስ ወይ ወደ እዚህ ዓለም የመመለስ እድል አለን ወይንም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ዓለም የመሸጋገር እድል አለን፡፡
- Prabhupāda 1076


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

የተለያዩ "ብሀቫዎች" አሉ፡፡ ይህ ቁሳዊው ዓለም እራሱ "ብሀቫ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም ቀደም ብሎ ተገልጿል፡፡ ይህ ቁሳዊው ትእይንተ ዓለም አንዱ የዓብዩ ጌታ ሀይል መግለጫ ነው፡፡ ቪሽኑ ፑራና ተብሎ በሚታወቀው የቬዲክ ስነፅሁፍ ውስጥ መላው የዓብዩ ጌታ ሀይሎች ተጠቃለው ተጠቅሰዋል፡፡ "ቪሽኑ ሻክቲ ፓራ ፕሮክታ ሼትራ ግያክህያ ታትሀ ፓር አቪድያ ካርማ ሳምግናንያ ትርቲያ ሻክቲር ኢሽያቴ" (ቼቻ፡ ማድህያ 6.154)

መላው የዓብዩ ጌታ ሀይላት "ፓራስያ ሻክቲር ቪቪድሃይቫ ሽሩያቴ" (ቼቻ፡ ማድህያ 13.65) ዓብዩ የመላእክት ጌታ የተለያዩ ሀይላት እና በቁጥር ሊተመን የማይችል ልዩ ልዩ ሀይላት አሉት፡፡ እነዚህንም ሀይላት ልንረዳቸው እንኳን አንችልም፡፡ ብሆንም ግን ታላላቅ የተማሩ ባህታውያን እና ነፍሳቸው ከዓለማዊ ኑሮ ነፃ የሆኑ ሁሉ ይህንን ሲያጠኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህንም ሀይላት በሶስት ከፋፍለው መድበዋቸዋል፡፡ እነዚህም በሶስት ርእሶች ስም ተመድበዋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መላ የዓብዩ ጌታ ሀይላት "ቪሽኑ ሻክቲ" ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም ሀይላት የዓብዩ ጌታ ቪሽኑ የተለያዩ ሀይላት ናቸው፡፡ እነዚህም ሀይላት "ፓራ" የበላይ ወይንም መንፈሳዊ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ “ክሼትራ ግያክህያ ታትሀ ፓራ” እንዲሁም ነዋሪ ፍጥረታት “ክሼትራ ግያ” እነዚህ ሁሉ በላቀው የዓብዩ ጌታ ግሩፕ ውስጥ ተመድበው ይገኛሉ፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ተገልፆ ይገኛል፡፡ ቀደም ብለንም ገልፀነዋል፡፡ ሌሎቹ ሀይላት ደግሞ የቁሳዊው ዓለም ሀይላት ናቸው፡፡ “ትሪትያ ካርማ ሳምግናንያ” (ቼቻ፡ ማድህያ 6.154) ይህም የቁሳዊው ዓለም ሀይል በድንቁርና ወገን የተመደበ ነው፡፡ የቁሳዊ ሀይል የሚባለውም ይህ ነው፡፡ ይህም ሀይል “ብሀገቨድ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ በሞት አፋፍ ላይ ስንደረስ ወይ ወደ እዚህ ቁሳዊው ዓለም እንመለሳለን ወይንም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ዓለም እንመለሳለን፡፡ ይህ ነው መመርያው፡፡ ብሀገቨድ ጊታም እንደዚህ ይላል፡፡ "ያም ያም ቫፒ ስማራን ብሀቫም ትያጃትዪ አንቴ ካሌቫራም" "ታም ታም ኤቫይቲ ኮንቴያ ሳዳ ታድ ብሀቫ ብሀቪታሀ" (ብጊ፡ 8.6)

ማሰብን ለማቆም የማንችል ነገር ነው፡፡ የምናስበውም ወይ ዓለማዊ ወይንም ደግሞ መንፈሳዊ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ታድያ ይህንን ሀሳብ እንዴት አድርገን ለበጐ ለማዘዋወር እንችላለን? ይህ በዓለማዊ አስተሳሰብ የተመሰጠውን ሀሳብ እንዴት አድረገን ወደ መንፈሳዊ አስተሳሰብ እንዲሰመጥ ለማድረግ እንችላለን? ይህንንም የመንፈሳዊ ሀሳብን ለማፍለቅ የቬዲክ ስነፅፉፎች ተዘጋጅገውልን ቀርበውልናል፡፡ ለምሳሌ ዓለማዊ ነገሮችን ለማሰብ ብዙ ዓለማዊ መፅሀፎች ይገኛሉ፡፡ ጋዜጣዎች፣ መጋዚኖች፣ ልብ ወለዶች፣ ታሪኮች፣ እና የተለያዩ ህትመቶች ይገኛሉ፡፡ በርካታ ዓለማዊ ህትመቶች ይገኛሉ፡፡ ሰለዚህ ሀሳባችን ሁልግዜ በእነዚህ ፅሁፎች እንደተመሰጠ ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ ሀሳባችንን በመንፈሳዊ መንገድ ለመመሰጥ ከፈለግን ይህንን የማንበብ አዝማሚያችንን ወደ ቬዲክ ስነጽሁፎች ማሻገር ይኖርብናል፡፡ በዚህም ምክንያት እነዚህ የተማሩት ባህታውያን ብዙ የቬዲክ ስነፅሁፎች ትተውልናል፡፡ እነዚህም እንደ “ፑራናዎችን“ የመሰሉ ናቸው፡፡ ፑራናዎች ታሪኮች አይደሉም፡፡ ነገር ግን ታሪካዊ ምዝገባዎች ናቸው፡፡ በቼታንያ ቻሪታምሪታ ውስጥ እንደሚከተለው የተገለፀ ጥቅስ አለ፡፡ ”አናዲ ባሂርሙክሀ ጂቫ ክርሽና ብሁሊ ጌላ አታኤቫ ክርሽና ቬዳ ፑራና ኮይላ“ (ቼቻ፡ 20.117) እነዚህም ሁሉ ውስን እና ዓብዩ ጌታን የዘነጉ ነፍሳት ሁሉ ከዓብዩ ጌታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ረስተዋል፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ በሚገኘውም የዓለማዊ ደስታ እና እንቅስቃሴ ላይ ተመስጠው ይገኛሉ፡፡ ይህንንም አስተሳሰባቸውን ወደ መንፈሳዊ መንገድ ለመምራት ባህታዊው ክርሽና ድቫይፓያና ቭያስ የተለያዩ የቬዲክ ስነፅሁፎችን ፅፎ አዘጋጅቶ አቅርቦልናል፡፡ ይህንንም የቬዲክ ስነጽሁፍ ሲያዘጋጅ መላ ቬዳዎችን በአራተ ዘርፍ ከፋፍሏቸው ነው፡፡ እነዚህንም አራት ቬዳዎች "ፑራና" ተብለው በሚታወቁት ውስጥ ዘረዘራቸው፡፡ ከዚያም ቬዳን ለመረዳት ለሚያዳግታቸው "ስትሪ፣ ሱድራ፣ ቫይሻ" ተብለው ለሚታወቁት "መሀብሀራትን" ፅፎ አዘጋጀ፡፡ በዚህም በመሀብሀራት መጽሀፍ ውስጥ ብሀገቨድ ጊታን አካተተ፡፡ ከዚያም በኃላ መላውን የቬዲክ ስነፅሁፍ በቬዳንታ ሱትራ ውስጥ አጠቃሎት ይገኛል፡፡ ይህንንም ቬዳንታ ሱትራ ለወደፊት መመርያ እንዲሆን የእራሱን ገለፃ በመስጠት "ሽሪማድ ብሀገቨታም" ተብሎ የሚታወቀውን ስነፅሁፍ አዘጋጀ፡፡