AM/Prabhupada 1080 - በብሀገቨድ ጊታ እንደተደመደመው አንድ የሆነው ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና የአንድ የተወሰነ ሕብረተሰብ አምላክ ብቻ አይደለም፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

በብሀገቨድ ጊታ እንደተደመደመው አንድ የሆነው ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና የአንድ የተወሰነ ሕብረተሰብ አምላክ ብቻ አይደለም፡፡
- Prabhupāda 1080


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ይህንንም ዓብዩ ጌታ በብሀገቨድ ጊታ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በግልፅ ተናግሮታል፡፡ “አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሻዪስያሚ ማ ሱቻሀ” (ብጊ፡ 18 66) ዓብዩ ጌታ አለገልጋዮቹ ስህተት ሁሉ ሀላፊነት ይወስዳል፡፡ በትሁት ልቦናው ለዓብዩ ጌታ ልቡን ለሰጠ አገልጋይ ሁሉ ዓብዩ ጌታ ልቡን ለማፅዳት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡ ይህም ከሀጥያት ሁሉ ነፃ ለማድረግ ነው፡፡ “ማላ ኒርሞቻናም ፑምሳም ጃላ ስናናም ዲኔ ዲኔ“ ”ሳክርድ ጊታምርታ ስናናም ሳምሳራ ማላ ናሻናም“ (ጊታ ማሀትምያ 3) አንድ ሰው በቀን በቀን ገላውን በውሀ በመታጠብ እራሱን ንፁህ ለማድረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ብሀገቨድ ጊታን በመሰለ የመንፈሳዊ የጋንጀስ ወንዝ ውሀ የታጠበ ሰው ደግሞ በቁሳዊው ዓለም የተበከለው ዓለማዊው ቆሻሻ አንደበቱ ሁሉ ይወድማል፡፡ ”ጊጋ ሱ ጊታ ካርታቭያ ኪም አንዬህ ሻስትራ ቪስታሬይህ“ ”ያ ስቫያም ፓድማናብሀስያ ሙክሀ ፓድማድ ቪኒህርታ“ (ጊታ ማሃትምያ 4) ምክንያቱም የብሀገቨድ ጊታ መልእክት የተነገረው በዓብዩ የመላእክት ጌታ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ዘር ሁሉ መልእክቱን መረዳት ይገባዋል፡፡ ሰዎች ሌሎችን የቬዲክ ስነፅሁፎች ሁሉ ለማንበብ እድል አይኖራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህንን የብሀገቨድ ጊታ መልእክት በጥሞና እና በተደጋጋሚ ሊያዳምጡ ይገባል፡፡ ”ጊታ ሱ ጊታ ካርታቭያ“ ይህንንም ለማድረግ የተመቻቸ ነገሮችን መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ”ጊታ ሱ ጊታ ካርታቭያ ኪም አንዬህ ሻስትራ ቪስታሬይህ“ ምክንያቱም በአሁኑ ግዜ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች የተጠመዱ ሆነው ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሀሳባቸውን በሙሉ ወደ ቬዲክ ስነፅሁፎች ለማዘዋወር ያዳግታቸው ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይህ አንድ ስነፅሁፍ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህ መፅሀፍ የቬዲክ ስነፅሁፎች ሁሉ ዋነኛው እና የጠራውን መልእክት የያዘ ስለሆነ ነው፡፡ በተለይ በዓብዩ የመላእክት ጌታ እራሱ የተነገረ መልእክት ስለመሆኑ ነው፡፡ ”ብሀራትምርታ ሳርቫስቫም ቪሽኑ ቫክትራድ ቪኒህስርታም“ ”ጊታ ጋንጐዳካም ፒትቫ ፑናር ጃንማ ና ቪድያቴ“ (ጊታ ማሀትምያ፡ 5) እንደተገለፀውም አንድ የጋንጀስን ቅዱስ የወንዝ ውሀ የጠጣ ሰው ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ነፃ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት ብሀገቨድ ጊታን የመሰለ ቅዱስ መፅሀፍን የተከታተለ ሰው ይቅርና ማለት ነው፡፡ ብሀገቨድ ጊታ ከመሀብሀራት መፅሀፍ ምዕራው ውስጥ በመገኘት ጣፋጭ መልእክትን ይዞ የቀረበ ነው፡፡ የተነገረውም በዓብዩ ጌታ በቪሽኑ ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ ክርሽና ዋነኛው ቪሽኑ ነው፡፡ ”ቪሽኑ ቫክትራድ ቪኒህስርታም“ መልእክቱ የፈለቀውም ከዓብዩ የመላእክት ጌታ ቅዱስ አፍ ነው፡፡ ”ጋንጎ ዳካም“ የጋንጀስ ወንዝ ደግሞ የመነጨችው የሎተስ እፅዋት ከመሰለው የጌታ እግር ነው፡፡ ብሀገቨድ ጊታ ደግሞ የመነጨው ከዓብዩ ጌታ ቅዱስ አፍ ነው፡፡ በእርግጥ በዓብዩ ጌታ እግር እና አፍ መሀከል ምንም ልዩነት የለም፡፡ ቢሆንም ግን በገለልተኛ ዓይን ስናየው ብሀገቨድ ጊታ ከጋንጀስ ቅዱስ ውሀ በላይ አስፈላጊነት እንዳለው መረዳት እንችላለን፡፡ ”ሳርቮፓኒሳዶ ጋቮ ዶግድሀ ጎፓላ ናንዳና“ ”ፓርትሆ ቫትሳሀ ሱ ድሂር ብሆክታ ዱግድሀም ጊታምርታም ማሀት“ (ጊታ መሀትምያ 6) የጊታ ኡፓኒሳድ እንደ ላም ይመሰላል፡፡ ዓብዩ ጌታም እንደ እረኝነቱ ላሚቱን እንደሚያልባት የታወቀ ነው፡፡ ”ሳርቮ ፓኒሳዶ“ የቬዲክ ኡፓኒሳድ መልእክቶችም እንደ ላም ተመስለዋል፡፡ ዓብዩ ጌታም እንደ እረኝነቱ ይህችን ላሚቷን ሲያልባት ይገኛል፡፡ እንዲሁም “ፓርትሆ ቫትሳሀ” አርጁና እንደ ጥጃ ይቆጠራል፡፡ እንዲሁም “ሱ ድሂር ብሆክታ” የተማሩ መምህራን እና ንፁህ የጌታ አገልጋዮች ደግሞ ይህንን ወተት የሚወስዱ ናቸው፡፡ “ሱድሂር ብሆክታ ዱግድሀም ጊታምርታም ማሀት” ይህ ጣፋጭ የብሀገቨድ ጊታ ወተት የተዘጋቸው ለምሁራን ትሁት የጌታ አገልጋዮች ነው፡፡ “ኤካም ሻስትራም ዴቫኪ ፑትራ ጊታም ኤኮ ዴቮ ዴቫኪ ፑትራ ኤቫ” “ኤኮ ማንትራስ ታስያ ናማኒ ያኒ ካርማፒ ኤካም ታስያ ዴቫስያ ሴቫ” (ጊታ መሀትምያ 7) ስለዚህ መላ ዓለም የዚህን የብሀገቨድ ጊታ መልእክት እንዲማር ያስፈልጋል፡፡ “ኤቫም ሻስትራም ዴቫኪ ፑትራ ጊታም” “በዓለም ላይ አንድ የጋራ የሆነ ቅዱስ መፅሀፍ አለ፡፡” ይህም በምድር ላይ ለሚገኙ ሰዎች በሙሉ የቀረበ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ መፅሀፍ ብሀገቨድ ጊታ ነው፡፡ “ዴቮ ዴቫኪ ፑትራ ኤቫ” ለመላው የሰው ልጅ ሕብረተሰብ አንድ ዓብይ ጌታ ብቻ ነው ያለው፡፡ ይህም ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ”ኤኮ ማንትራስ ታስያ ናማኒ“ እንደዚህም ሁሉ ለመላ ዓለም አንድ ማህሌት ወይንም ማንትራ ወይንም ፀሎት አለ፡፡ ይህም ማህሌት የዓብዩ ጌታን ቅዱስ ስም መዘመር ነው፡፡ ሀሬ ክርሽና፣ ሀሬ ክርሽና፣ ክርሽና ክርሽና፣ ሀሬ ሀሬ፣ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ፣ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ፡፡ ”ኤኮ ማንትራስ ታስያ ናማኒ ያኒ ካርማፒ ኤካም ታስያ ዴቫስያ ሴቫ“ እንደዚሁም ሁሉ አንድ ስራ ብቻ መኖር አለበት፡፡ ይህም ስራ ዓብዩ ጌታን ማገልገል ነው፡፡ ሕብረተሰቡ ብሀገቨድ ጊታን የተማረ ከሆነ የህዝቡ ፍላጐት የሚሆነው አንድ ሀይማኖት ብቻ እንዲኖረው ነው፡፡ አንድ አምላክ፣ አንድ ቅዱስ መፅሀፍ፣ አንድ ስራ ወይንም የተመሳሰለ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ማለት ነው፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተጠቃሎ ተገልጿል፡፡ ይህም አንድ ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ክርሽና የአንድ የተለየ ሕብረተሰብ አምላክ አይደለም፡፡ ቅዱስ ስሙ ክርሽና እንደሚያመለክተን ክርሽና ማለት ቀደም ብለን እንደገለፅነው ክርሽና ማለት ከፍተኛውን ደስታ የሚሰጥ ማለት ነው፡፡