AM/Prabhupada 0022 - ክርሽና አልተራበም፡፡: Difference between revisions
m (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->") |
(No difference)
|
Latest revision as of 06:06, 29 November 2017
Lecture on SB 1.8.18 -- Chicago, July 4, 1974
ክርሽና እንዲህ አለ "የእኔ አገልጋዮች በፍቅር" ዮሜ ባሃክትያ ፕራያቻቲ ክርሽና የተራበ አይደለም: ክርሽና ወደ እናንተ የምታቀርቡለትን ሊበላ የሚመጣው ስለራበው አይደለም: አይደለyም: እርሱ የተራበ አይደለም: እርሱ ሙሉ በሙሉ የተሟላ ነው: በመንፈሳዊ አለም ውስጥም: እየተስተናገደ ነው: "ላክሽሚ ሳሃስራ ሻታ ሳምብህራማ ሴቭያማናም" እርሱም በ100 እና በ1000 የሚሆ ኑ የሃብት ማላእክቶች: እየተስተናገደ ነው: ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው: ምክንያቱም ክርሽናን በጣም የምታፈቅሩ ከሆነ: እዚህ ድረስ መጥቶ ያቀረበላችሁትን ሊቀበል ይችላል: "ፓትራም ፑሽፓም" የመጨረሻ የድሃ ደሃ ብንሆን እንኳን : ክርሽና በፍቅርና በአቅማችን የሰበሰብንለትን ይቀበላል: ትንሽ ቅጠላ ቅጠል: ትንሽ ውሃ: ትንሽ አበባ: በፍቅር ያቀረብንለትን: ይቀበለናል: ከየትም አለም ሆነን: የሚቀርብ ነገር አዘጋጅተን ለክርሽና ማቅረብ እንችላለን: "ክርሽና: በድህነቴ: ምንም ጥሩ ተገር እማቀርብለህ የለም: ስለዚህ ይህንን በርኁሩህነትህ ተቅበለኝ" ክርሽናም ይቀበላል: ክርሽናም እንዲህ ብሏል: "ታድ አሃም አሸናሚ" "እበላለሁ" ስለዚህ ዋናው ነገር "ብሃክቲ" ወይንም በፍቅር የቀረበ መሆን አለበት: እዚህም እንዲህ ተብሏል: "አላክስያም" ክርሽና በአይናችን በቀላሉ ሊታየን አይችልም: አማላክ በቀላሉ አይታይም: ነገር ግን በርኅሩኁነቱ: እዚህ አለም ላይ: በአያናቸን እንድናየው መጥቶ ነበር:: አለበለዛ ግን ክርሽና በዚህ ምድር ላይ በቀላሉ አይታየንም: እኛ የክርሽና ወገን እና ቅንጣፊ ነን: የክርሽና ወገንና ቅንጣፊ ሁሉም በምድር ላይ ያሉ ነዋሪ ነፍሶች ሁሉ: እርስ በእርስ ግን አንተያይም: እናንተ እኔን ልታዩ አትችሉም: እኔም እናንተን ለማየት አልችልም: "አይ አያሃለሁ" ልትሉ ትችላላችሁ: ነገር ግን ምንድን ነው የምታዩት? የምታዩትም ገላዬን ነው እንጂ ነፍሴን አይደለም: ታድያ ነፍስ ከገላ ስትወጣ: ለምንድነው አባቴ ሄደ ብለን የምናለቅሰው? አባታችንስ ወዴት ሄደ? እዚያው ተጋድሞስ እያየነው አይደለምን? እና ያያችሁትስ ምንድን ነው? ያያችሁት የአባታችሁን የሞተ ገላ ነው እንጂ አባታችሁን አይደለም:: እንደዚሁም በአጠገባችሁ ያለውን የክርሽናን ወገን (የሰውን ነፍስ) ለማየት ካልቻላችሁ: እንዴትስ ክርሽናን ለማየት ትችላላችሁ? ስለዚህም ሻስትራ እንዲህ ይላል "አታህ ሽሪ ክርሽና ናማዲና ብሃቬድ ግራህያም ኢንድሪያህ" (ቼ ቻ ማድህያ 17 136) እንዚህ አለማዊ አይናችን: ክርሽናን ማየት አይችልም: የክርሽናንም ቅዱስ ስም ለመስማት አንችልም "ናማዲ" “ናማ” ማለት ስም ማለት ነው:“ናማ” ማለት ስም: ፎርም: አይነት እና ያለፉ ታሪኮችን ያጠቃልላል: እነዚህ ነገሮች በዚህ በአለማዊ አይኖቻችን አይተን ልንረዳቸው የምንችል አይደለም: ነገር ግን በመንፈሳዊነት ንጹሕ ከሆኑ: “ሴቮኑኬ ሂ ጂህቫዱ” በፍቅር አጋልግሎታችን የጠሩ አይኖች ከሆኑ ግን: ክርሽናን ሁል ግዜ እና የትም ቦታ ለማየት ትችላላችሁ: ነገር ግን ለተራ ሰው “አላክሻም” በቀላሉ ሊታይ አይችልም: ክርሽና ሁሉም ቦታ አለ: አማላክ ሁሉ ቦታ አለ: “አንዳንታራ ስትሃ ፓራማኑ ቻያንታራ ስትሃም: ሶአላክሻም ሳርቫ ብሁታናም” ክርሽና ከውስጥም ከውጪም ይሁን እንጂ: ክርሽናን ለማየት የሚችል መንፈሳዊ አይን ከሌለ:ክርሽናን ለማየት አንችልም: እንደዚሁም ሁሉ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር: የተቋቋመው አይናችሁን ከፍቶ እንዴት ክርሽናን ለማየት ለመቻል እንድትበቁ ነው: እንዲሁም ክርሽናን ለማየት ከበቃችሁ “አናንታ ባሂህ” ህይዋታችሁ የተሳካ ሁኗል ማለት ነው: ስለዚህም ሻስትራ እንዲህ ይላል "አንታር ባሂር" "አንታር ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታህ ኪም ናንታር ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታህ ኪም" ሁሉም ሰው ፍጹም እና እንከን የሌለው መሆን ይፈልጋል: ነገር ግን ሰው እንከን የለሽ ሆነ ለማለት የምንችለው: ክርሽናን ከውስጣችንም ሆነ ከውጪ:የማየት ችሎታ ሲኖረን:እንከን የለሽ ሆንን ማለት ነው: