AM/Prabhupada 0084 - የክርሽና ትሁት አገልጋይ ሁኑ፡፡

Revision as of 13:26, 2 January 2017 by Zoran (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 French Pages with Videos Category:Prabhupada 0084 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1972 Category:AM-Quotes - Le...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Lecture on BG 2.22 -- Hyderabad, November 26, 1972

የምናቀርበው ሀሳብ ቢኖር የሚያስፈልጋችሁን እውቀት ከሽሪ ክርሽና ውሰዱ ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና ዓብዩ የመንግስተ ሰማያት ጌታ እና ፍፁም የሆነው አምላክ ነው፡፡ ሻስትራ ወይንም የቬዲክ ስነፅሁፎችን እንቀበላለን የምንለው ሊወደቅ የማይችል ፍፁም እውነት ስለሆነ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ስህተትም አይገኝበትም፡፡ በላሞቹ በረት በኩል እየተራመድኩ ሳልፍ እንዳየሁትም የተከመረ የላሞች እበት ነበረ፡፡ ለተከታዮቼም በዚያን ግዜ እንዲህ በማለት ማስረዳት ጀመርኩ፡፡ እዚህ ውስጥ የተከማቸ የሰው ሰገራ ቢሆን ኖሮ ማንም ሰው ወደእዚህ ሊመጣ አይችልም ነበረ፡፡ ማንም ሰው ቢሆን፡፡ ነገር ግን የላሞች እበት በመሆኑ እና ተከምሮ የሚታይ የላም እበት በመሆኑ በደስታ በአጠገቡ እየተራመድን ስናልፍ እንገኛለን፡፡ በቬዲክ ስነጽሁፎችም ውስጥ የላሞች እበት ንፁህ ነው ተብሎ ተፅፏል፡፡ ይህ የሻስትራ እውቀት ነው፡፡ ለመከራከር ትሞክሩም ይሆናል፡፡ “እንዴት ንፁህ ሆነ? የእንስሳ ሰገራ አይደለምን?" ቢሆንም ግን ቬዳዎች የገለፁት በመሆኑ የተሰጠው እውቀት ትክክል ሆኖ ይገኛል፡፡ በክርክር ግን እንዴት ይህ የእንስሳ ሰገራ ንፁህ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ ቢሆንም ግን የላም እበት ንፁህ ነው፡፡ ስለዚህ የቬዲክ እውቀት ትክክለኛ ነው፡፡ እውቀትንም ከቬዳ የምንወስድ ከሆነ በምርምር እና በእውቀት ፍለጋ ብዙውን ግዜያችንን አናባክንም፡፡ ምርምር በጣም የምንወድ ሰዎች ነን፡፡ ቢሆንም ግን ሁሉም ነገር በቬዳ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ለምን ግዜያችሁን ታባክናላችሁ? ቬዲክ እውቀት ማለት እንዲህ ነው፡፡ ቬዲክ እውቀት ማለት በዓብዩ ጌታ የተገለፀልን እውቀት ማለት ነው፡፡ ይህም ቬዲክ እውቀት ወይንም ”አፖሩሴያ“ ተብሎ ይታወቃል፡፡ የቬዲክ እውቀት በእንደኔ ተራ ሰው የተነገረ አይደለም፡፡ ይህንንም የቬዲክ እውቀት ልክ እንደቀረበልን የምንቀበለው ከሆነ ይህም ማለት ልክ በሽሪ ክርሽና ወይንም በእርሱ ተወካይ እንደቀረበልን የምንቀበለው ከሆነ መንፈሳዊ ንቃት ይኖረናል፡፡ ምክንያቱም ተወካዩ ወይም መንፈሳዊ አባቱ ክርሽና ያልተናገረውን ነገር አይናገርም፡፡ ስለዚህ በምድር የክርሽና ተወካይ ነው እንለዋለን፡፡ በክርሽና ንቃት የዳበሩ ሁሉ የክርሽና ተወካዮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በክርሽና ንቃት የዳበረ ሰው ሁሉ ስሜት የማይሰጥ ነገርን አይናገርም፡፡ ይህም ማለት ክርሽና ከሚያስተምረው ውጪ አያስተምርም፡፡ ይህ ነው ልዩነቱ፡፡ ሌሎች ተንኮለኞች ግን ክርሽና ከተናገረው ውጪ ስሜት የማይሰጥ ርእስ ላይ ገለፃ ይሰጣሉ፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ ”ማን ማና ብሀቫ ማድ ብሃክቶ ማድ ያጂ ማም ናማስኩሩ“ (ብጊ፡ 18.65) ነገር ግን ተንኮለኛው አዋቂ ነኝ ባይ እንዲህ ይላል፡፡ ”አይደለም ይህ የሚያወራው ስለ ክርሽና አይደለም፡፡ ስለሌላ ነገር ነው፡፡“ ታድያ ይህንን ከየት አምጥተውት ነው? ክርሽና በቀጥታ እና በግልፅ እየነገረን ነው፡፡ ”ማን ማና ብሀቫ ማድ ብሀክቶ ማድ ያጂ ማም ናማስኩሩ" (ብጊ፡ 18.65) ታድያ በግልፅ ከተነገረው መሸሽ ለምን ያስፈልጋል? ሽሪ ክርሽና ከተናገረው ውጪ መናገርስ ለምን ያስፈልጋል? ስም ባንጠቅስም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ምሁር ነን ብለው የሚቀርቡ ብዙ ተንኮለኞች አሉ፡፡ የሽሪ ክርሽናን መልእክትንም አሳስተው ሲተረጉሙ ይታያሉ፡፡ ምንም እንኳን ብሀገቨድ ጊታ ከሕንድ አገር የመነጨ ቅዱስ መፅሀፍ ቢሆንም ብዙዎች ሰዎች በትክክል ሳይመሩበት ቆይተዋል፡፡ ይህም በእነዚህ በተኮለኞች ምሁር ነን ብለው በሚቀርቡት ምክንያት ነው፡፡ ምክንያቱም መልእክቱን እንዳሻቸው አሳስተው በመተርጎማቸው ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ይህንኑ ብሀገቨድ ጊታ ልክ በሽሪ ክርሽና እንደተዘመረው አድረገን አቅርበነዋል፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ “ሳርቫ ድሀርማ ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሸረናም ቭራጃ” (ብጊ፡ 18.66) እኛም የምንሰጠው መክእክት “በክርሽና ንቃት መዳበር ይገባችኋል” የሚል ነው፡፡ የሽሪ ክርሽና ትሁት አገልጋዮች ሁኑ፡፡ አክብሮታችሁንም ሁሉ አቅርቡለት፡፡ ለሌሎች አክብሮታችንን ማቅረብ ግዳጃችን ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የሁሉም በላይ ስላልሆንን ነው፡፡ አንድ አገልግሎት ለማግኘትም ሌላውን ማወደስ ያስፈልገናል። ምንም እንኳን ጥሩ ደረጃ ላይ ያለን ብንሆንም እንኳን ሌሎችን ማወደስ ግዴታችን ነው፡፡ ምንም እንኳን የአገሩ ፕሬዚደንት ብንሆንም የአገሩን ህዝብ ማወደስ ያስፈልጋል፡፡ “እባካችሁ እኔን ምረጡኝ፡፡” “ከመረጣችሁኝ ብዙ ነገር ላደርግላችሁ እችላለሁ፡፡” ስለዚህ ሌሎችን ማወደስ ግዴታችን ነው፡፡ ይህም ያለ ሀቅ ነው፡፡ በደረጃ ትልቅ ሰው ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ቢሆንም ግን ሌሎችን ማወደስ አስፈላጊ ነው፡፡ ታድያ ሌሎች ጌታዎችን የምትቀበሉ ከሆነ ለምን ሽሪ ክርሽናንስ አትቀበሉም? እርሱ የሁሉም ዓብይ ጌታ ነው፡፡ ችግሩስ ምን ላይ ነው? ችግሩ ግን ከክርሽና በቀር ሌሎች በሺ የሚቆጠሩ ጌታዎችን እንቀበላለን የሚል ፍልስፍና ይዘናል፡፡ “ከክርሽና በቀር በሺህ የሚቆጠሩ መምህራንን እከተላለሁ፡፡” ይህ ነው የእኛ ውሳኔ፡፡ ታድያ እንዴት አድርጋችሁ ደስተኛ ለመሆን ትችላላችሁ? ይህ ደስታ ሊገኝ የሚችለው ሽሪ ክርሽና በመቀበል ብቻ ነው፡፡ “ብሆክታራም ያግያ ታፓሻም ሳርቫ ሎካ ማሄሽቫራም ሱህርዳም ሳርቫ ብሁታናም ግያትቫ ማም ሻንቱም ርቻቲ” (ብጊ፡ 5.29) የሻንቲ ወይም የሰላም ስርዓቱ ይህ ነው፡፡ ክርሽና እንደገለፀውም የሁሉም ነገር ተደሳች እርሱ ነው እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ እኛ ተደሳቾች አይደለንም፡፡ ፕሬዚደንት ወይንም ሴክረታሪ ትሆኑ ይሆናል፡፡ ወይንም ሌላ ማእረግ ያላችሁ ልትሆኑ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሁሉም ነገር የደስታ ተቀባዮች አይደላችሁም፡፡ ደስታ ሊሰጠው የሚገባውም ግን ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ይህንንም በትክክል መረዳት ያስፈልገናል፡፡ ለምሳሌ አሁን እንደመጣሁ አንድራ ለሚባለው የበጐ አድራጎት ድርጅት የደብዳቤ መልስ እየፃፍኩኝ ነበር፡፡ ይህስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሽሪ ክርሽና ካልተደሰት ምን ማድረግ ይችላል? ገንዘብን በማሰባሰብ ብቻ ችግሩን የሚያቃልሉ ይመስላችኋል? ይህ የማይቻል ነው፡፡ በተፈጥሮ ፍቃድ ግን ዝናብ ሲመጣ ጥቅሙን ለማግኘት ትችላላችሁ፡፡ የዚህም የዝናብ መምጣት የሚወሰነው በሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ገና ለገና ገንዘብ አዋጣችሁ እና ዝናብ ይመጣል ለማለት አይቻልም፡፡