AM/Prabhupada 0055 - በማዳመጥ ብቻ ክርሽናን ለመንካት ይቻላል፡፡

Revision as of 10:14, 19 April 2015 by Rishab (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0055 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1972 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Lecture on BG 2.18 -- Hyderabad, November 23, 1972

የጌታ ቼያታንያ መሀፕራብሁ ትንቢት እንዲህ ነበር፡፡ “በዚህ ዓለም ላይ በሚገኙት በየእያንዳንዱ ከተማ እና መንደር ውስጥ” የሃሬ ክርሽና ቅዱስ ስም እና የጌታ ቼታንያ ስም መወደስ ይጀመራል“ ይህም አሁን እይተካሄደ ነው:ይህም አለም የሃሬ ክርሽናን ንቃት እና እንቅስቃሴን ለማዳበር ትልቅ ሜዳ ነው: ይህ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ነው:ጌታ ቼይታንያም ይህንን አደራ የጣለው ለህንዶች ነበር: ቤናጋል ውስጥም ስለተወለደ:ሃላፊነቱ ለቤንጋሊዎች ብቻም አልነበረም የተሰጠው:ለቤንጋሊዎች ብቻም አላለም: እንዲህ ነበር ያለው:”ብሃራታ ብሁሚቴ ማኑሽያ ጃናማ ሆይላ ያራ (ቼቻ 9 41) “በዚህ ቅዱስ አገር:ብሃራትቫርሽ በተባለው:እንደ ሰው ልጅ ሁኖ:የተወለደ ሁሉ:” ህይወቱን በመንፈሳዊ ኑሮ እንከን የለሽ ማድረግ አለበት “ “ጃንማ ሳርትሃካ ካሪ” እርሳችንን ብቁ ሳናደርግ ለሌላ ሰው መስበክ አንችልም: እኔ እራሴን ብቁ ካላደረግሁ:መስበክ እና ማስተማር አልችልም:አንድ ሰው ለዚህ ብቁ መሆን አለበት: ይህም አስቸጋሪ አይደለም:ከታላላቅ ባህታውያን:ከመንፈሳዊ ሰዎች እና:ከራሱ አምላክ ጭምር:ብዙ መመሪያዎች ተሰጥተውናል: ህይወታችንን በመንፈሳዊነት ብቁ ለማድረግም አያስቸግርም:ችግሩ እኛ ተግባሩን እየገደፍን ስለምንገኝ ብቻ ነው: ይህ የእኛ እድለቢስነት ነው:”ማንዳህ ሱማንዳ ማታዮ ማንዳ ብሃጋህ“ (ሽብ1 1 10) ይህም እንደተገለጸው:እኛ:”ማንዳ ማንዳማታህ“ ስለ ሆንን ነው:ያልሆነ ሎጂክ እና ሥልጣን የሌለው ”ኢዝም“ እየተቀበልን ግዜያችንን እናባክናለን: ትክክለኛ መመሪያውን ግን ከሻስትራ ቅዱስ መጽሃፍቶች ነው መውሰድ ያለብን: ከዚያም አዋቂ ሰዎች እንሆናለን:”ሱሜድሃሳሃ“ ”ያግንያህ ሳንኪርታና ፕራዬር ያጃንቲ ሂ ሱ ሜድሃሳሃ“ (ሽ ብ 11 5 32)ይህም የአጭር መንገድ መመሪያ ነው: የህብረተሰቡ አዋቂ ሰዎች:በዚህ በሳንኪርታና እንቅስቃሴ ውስጥ ይሳተፋሉ:ይህም የመንፈሳዊ ብልጽግናቸውን ከፍ ለማድረግ ነው: ይህም እርግጥ ነው:ሳይንቲፊክ እና ስልጣን ያለው አመራር ነው:ስለዚህ መተው አይገባንም: ይህንን የሃሬ ክርሽናን ዝማሬ ወደ ልብ እና ነፍሳችሁ እንዲሁም ወደየቦታው ውሰዱት: ”ኒያሚታሃ ስማራኔ ናካላሃ“ ይህንንም ለማድረግ ህግ እና መቆጣጠሪያ ስርአት የለውም: ይህም “በዚህ ሰአት ወይንም በዚያን ሰአት ዘምር:ወይንም እዚህ ጋ ወይንም እዚ ጋ ዘምር” የሚባል ነገር የለም: ምክርያቱም ይህ መመሪያ የተሰጠው:በአለም ላይ ላለን ሁሉ ለወደቅን እና በኑሮ ለተወሰንን ነፍሳት ነው:ስለዚህ ምንም የሚያስቸግር ህግጋቶች የሉትም: “ናምናም አካሪ ባሁዳ ኒጃ ሳርቫ ሻክቲስ ታትራ ፒታ ኒያሚታህ ስማራኔ ና ካላሃ” ይህ ቅዱስ ስም:የክርሽና ቅዱስ ስም:ልክ እንደ ክርሽና ሃይል ያለው ነው: በክርሽና እና በቅዱስ ስሙ ምንም ልዩነት የለም:ሁለቱም ፍጹም ሃይል ያላቸው ነው: ስለዚህም በክርሽና ስም: በክርሽና ፎርም:ምንም አይነት ልዩነት የለም: የክርሽና አይነቶች:የክርሽና ባልደረቦች:የክርሽና ድርጊቶች:ከክርሽና የመጡ ነገሮች ሁሉ ከክርሽና ተለይተው አይታዩም: ስለ ክርሽና ስትሰሙ:ክርሽናን በማዳመጥ እንደነካችሁት በገንዘብ አለባችሁ: የክርሽናንም ደይቲ የምታዩ ከሆነ ክርሽናን በቀጥታ እያያችሁት ነው:ምክንያቱም ክርሽና ፍጹም ነው: አገልግሎታችሁን በየትም ቦታ ላይ ሊቀበል ይችላል:ምክንያቱም እርሱ ፍጹም ሰለሆነ ነው: “ኢሻቫሽያ ኢዳም ሳርቫም (ኢሾ 1) የእርሱ ሃይል: “ፓራስያ ብራህማናህ ሻክቲስ ታትሄዳም አክሂላም ጃጋት” ሁሉም ነገር የክርሽና ሃይል ነው: በትንሽም እውቀት ቢሆን ከክርሽና ሃይል ጋር ከተገናኘን:ከክርሽና ጋር በቀጥታ ተገናኘን ማለት ነው: ይህ ነው ስርአቱ: ከክርሽና ጋር በተገናኛችሁ ቁጥር:በክርሽና ንቃት ተሰማርታችኋል ማለት ነው: በዚህም አማካኝነት የመንፈሳዊ ንጹህነትን ታገኛላችሁ: ልክ ብረትን እሳት ውስጥ ስትከቱት: ብረቱ መሞቅ ይጀምርና:መጨረሻ ላይም ቀይ እና በጣም የሚያቃጥል ይሆናል: ቀይ እና በጣም የሚያቃጥልም ሲሆን:ብረት መሆኑ ቀርቶ እሳት ሆነ ማለት ነው: እንደዚሁም ሁሉ:እራሳችሁን በክርሽና ንቃት ሁል ግዜ ስታውሉት:በክርሽና ንቃት በደንብ የዳበራችሁ ትሆናላችሁ: ይህ ነው ስርአቱ:በዚህም መንገድ:ሁሉም ነገር የመንፈሳዊ ንፅህና ያገኛል: እንደዚሁም የመንፈሳዊ ኑሮዋችሁ ይዳብራል:ህይወታችሁም የተሳካ ይሆናል: