AM/Prabhupada 0228 - እንዴት ሞትን ለመቋቋም እንደምትችሉ ተረዱ፡፡

Revision as of 13:01, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 2.15 -- London, August 21, 1973

ይህ የሚያደርጉት ኮንፈረንስ የተባበሩት መንግስታት የሳይንሳዊ ሂደት የትምህርት ስርዓቶች ፍልስፍና ወዘተ ሁሉ ዓላማው በዚህ ዓለም ላይ እንዴት ደስተኛ ሆነን እንደምኖር ሊረዳን የታቀደ ነው፡፡ “ግራሃ ቭራታናም” ዋናው ዓላማ በዚህ ዓለም እንዴት ደስተኛ ሊያደርገን እንደሚችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚቻል አይደለም፡፡ እነዚህ ተንኮለኞች ይህንን በተገቢው ሊረዱት አይችሉም፡፡ ደስተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ ወደ ክርሽና መምጣት ይኖርባችኋል፡፡ “ማም ኡፔትያ ቱ ኮንቴያ ዱክሀላያም አሻሽቫታም ናፕኑቫንቲ (ብጊ፡ 8 15) ክርሽና እንዲህ ብሎናል ”አንድ ሰው ወደ እኔ ቢመጣ ተመለሶ እንደገና እዚህ መከራ ወደሞላበት ዓለም ለስቃይ አይመጣም፡፡“ “ዱክሀላያም” ይህ ቁሳዊ ዓለም በክርሽና ”ዱክሀላያም“ ተብሎ ተገልጿል፡፡ ”አላያም“ ማለት ቦታ ማለት ነው፡፡ ”ዱክሀ“ ማለት ደግሞ ስቃይ ወይንም ጭንቀት ማለት ነው፡፡ እዚህ ዓለም ውስጥ ሁሉም ነገር አስጨናቂ ነው፡፡ ነገር ግን በሞኝነታችን እና በማያ አእምሮአችን ተሸፍኖ ይኅው ጭንቀት ደስታ ነው ብለን እንቀበለዋለን፡፡ ይህ ማያ ወይንም ምትሀት ነው፡፡ ይህ ደስታ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ሙሉ ቀን እና ሌሊት ሲሰራ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም በመጨረሻ እንዲህ የሚል ወረቀት ሰለሚያገኝ ነው ”በአብዩ አማላክ እናምናለን ይህንን ወረቀት ውሰድ አንድ መቶ ዶላር አታለልኩህ” አይደለምን? “በአምላክ እናምናለን ደሞዝ ልከፍልህ ቃል ገብቻለሁ ይህንን ወረቀት ውሰድ” ”አንድ ሳንቲምም ላያወጣ ይችላል ነገር ግን ላዩ ላያ አንድ መቶ ዶላር ተብሎ ተፅፎበታል“ እኔም እንዲህ እያልኩ አስባለሁ፡፡ “አሁን ይህንን ወረቀት አግኝቻለሁ” ይኅው ነው፡፡ አታላዮች እና ተታላዮች፡፡ ይህ እየተካሄደ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዓለም ደስታ እና ጭንቀት መረበሽ አይገባንም፡፡ ይህ የእኛ ዓላማ እንዲሆን ይገባል፡፡ ዋናው ዓላማችን ይህንን የክርሽናን ንቃት እንቅስቃሴ እንዴት እንደምናከናውን መሆን ይገባዋል፡፡ እንዴት እንደምናከናውነው፡፡ ቼታንያ መሀፕራብሁም ቀላል የሆነ ፎርሙላ ወይንም ስርዓት ሰጥቶናል፡፡ “ሀሬር ናማ ሀሬር ናማ ሀሬር ናማይቫ ኬቫላም ከላዉ ናስቲ ኤቫ ናስቲ ኤቫ ናስቲ ኤቫ ጋቲር አንያታሀ” :(ቼቻ አዲ17 21) በዚህ በካሊ በተባለው ዘመን ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሆነ አውስተሪቲ እና ፔናንስ ማድረግ ይከብዳል፡፡ በቀላሉ ግን የክርሽናን ስም ሀሬ ክርሽና ሰም መዘመር ቀላል ነው፡፡ ይህንንም እንኳን በየግዜው ለማድረግ ሲከብደን ይታያል፡፡ ምን ዓይነት እድለ ቢሶች ነን? ይህ ነው የዚህ ካሊ ዩጋ ተብሎ የታወቀው ዘመን ሁኔታ፡፡ “ማንዳ ሱማንዳ ማታዮ ማንዳ ብሀጋ ኡፓድሩታሀ” (ሽብ፡ 1 1 10) እነዚህ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ “ማንዳ” ማለት መጥፎ ማለት ነው፡፡ "ሱማንዳ ማታያ“ አንድ ነገር ለማሻሻል ሲፈልጉ ደግሞ ሌላ ተንኮለኛ መንፈሳዊ መምህር ነኝ ባይ ጉሩ መሀራጅ መከተል ይጀምራሉ፡፡ ”ማንዳ ሱማንዳ ማታያሀ“ ወይንም ምንም ስልጣን የሌለውን ድርጅት ይቀበላሉ፡፡ ”ይህ ቆንጆ ነው“ ብለው ይቀበላሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መጥፎ መንፈስ ይዘዋል፡፡ የሚቀበሉትም ድርጅት ደግሞ መጥፎ የሆነውን ነው፡፡ ለምን? እድለ ቢስነታቸው ነው፡፡ ”ማንዳ ሱማንዳ ማታዮ ማንዳ ብሀጋህ“ (ሽብ፡ 1 1 10) ”ማንዳ ብሀጋህ“ ማለት እድለ ቢስ ማለት ነው፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ ”ኡፓድሩታሀ“ ሁሌ በጭንቀት የሚኖር፡፡ በታክስ በዝናብ በምግብ ማጣት እና በብዙ የተለያዩ ነገሮች፡፡ ይህ የካሊ ዩጋ ዘመን ደረጃ ነው፡፡ ሰለዚህም ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎናል፡፡ በቬዲክ ስነጽሁፎች ውስጥ እንደተገለፀው በዚህ በካሊ ዩጋ ዘመን የዮጋ ልምምድ ትልቅ ሀሳብ ውስጥ መግባት ትላልቅ መስዋእት ማቅረብ ወይንም በጣም ውድ የሆኑ ቤተ መቅደሶችን በመስራት ሙርቲዎችን ለማምለክ በጣም አዳጋች እንደሆነ ተገልፆልናል፡፡ በቀለሉ ግን ”ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሀሬ ሀሬ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ“ በማለት ለመዘመር እንችላለን፡፡ ቀስ በቀስም እንዴት ሞትን መቋቋም እንደምንችል ለመረዳት እንበቃለን፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡