AM/Prabhupada 0578 - ክርሽና የተናገረውን ብቻ መድገም ይገባናል፡፡
Lecture on BG 2.19 -- London, August 25, 1973
ይህንንም መወለድ እና መሞት ማቆም ከፈለጋችሁ.... በቁሳዊ ዓለም የስሜታዊ ደስታ አትመሰጡ፡፡ ይህም ፍላጎታችሁ እንደገና በዚህ ቁሳዊ ዓለም እንድትወታተቡ ያደርጋችኋል፡፡ ኑናም ፕራማታሀ ኩሩቴ ቪካርማ ያድ ኢድሪያ ፕሪታያ አፕርኖቲ ና ሳድሁ ማንዬ ያታ አትማኖ ያም አሳን አፒ ክሌሻዳ አሳ ዴሀህ (ሽብ፡ 5.5.4) ”ምንም ችግር የለም፡፡ ይህ ቁሳዊ ገላ የሚኖረው ለጥቂት ዓመታት ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደሰት፡፡“ ብላችሁ አታስቡ፡፡ አዎን በእርግጥ ገላችን መሞቱ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ነፍሳችን እንደገና ሌላ ገላ ይዛ መወለድዋ አይቀርም። የቁሳዊ ዓለም የስሜታዊ ደስታ ፍላጎትም እሰከአለን ድረስ ነፍስ እንደገና ገላ ይዛ ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም መምጣቷ የማይቀር ነው፡፡ የቁሳዊ ስሜታዊ ደስታ ፍላጎት እስከአለን ድረስ ይህ የቁሳዊ ገላ ስሜቶችን ለማርካት ያስፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ክርሽና በቸርነቱ ወዶ ሳይሆን ሳይወድ ይህንን ገላ ይሰጠናል፡፡ ”እሺ አንተ ተንኮለኛ ይህንን ትፈልጋለህ? ይህንን ገላ ስጡት፡፡“ ”ይህ ተንኮለኛ ደግሞ ሰገራ መመገብ ይፈልጋል፡፡ እሺ የአሳማ ገላ ስጡት፡፡“ ይህ በተፈጥሮ ህግ የተከተለ ሂደት እየተካሄደ ነው፡፡ ይህም የብሀገቨድ ጊታ እውቀት ለሰው ልጅ ህብረተሰብ ፍፁም ሆኖ የተሟላ እውቀት ነው፡፡ ክርሽናም ይህ እውቀት ለሁሉም የሰው ልጅ ህብረተሰብ እንዲስፋፋ ምኞቱ ነው፡፡ ሳርቫ ሆኒሱ ኮንቴያ ሳምብሀቫንቲ ሙርታያህ (ብጊ፡ 14.4) ክርሽና የሁሉንም ዘር የሚሰጥ አባት ነው፡፡ አባትም ሁልግዜ ጥሩ የሚመኝ ነው፡፡ ”እነዚህ ተንኮለኞች እየተሰቃዩ ነው፡፡“ ፕራክርቲ ስትሀኒ ማናሀ ሳስትሀኒንድሪያኒ ፕራክርቲ ስትሀኒ ካርሳቲ (ብጊ፡ 15.7) እነዚህም ተንኮለኞች በ"ማናሀ" ወይንም በግምታዊ አስተሳሰብ እንዲሁም በስሜቶቻቸው ተደግፈው በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ በጣም በመታገል ይገኛሉ፡፡ ወደ እኔ ቢመለሱ ግን በደስታ ለመኖር ይችላሉ፡፡ ይህም በቭርንዳቫና ውስጥ ልክ እንደ ጓደኛዬ ወይንም እንደ ወዳጄ እንደ አባቴ እንደ እናቴ በመሆን ነው፡፡ “ስለዚህ ወደ እኔ እንዲመለሱ ጋብዟቸው፡፡” በዚህም ምክንያት ክርሽና ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም ይመጣል፡፡ ”ያዳ ያዳ ሂ ድሀርማስያ (ብጊ፡ 4.7) ምክንያቱም መላው የዓለም ህብረተሰብ በዚህ በተሳሳተ የስሜታዊ ደስታ ምተሀት ተጠምዶ ስለሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህም እዚህ መጥቶ ምክሩን ሲያቀርብልን ይገኛል፡፡ “ዳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጅያ” (ብጊ፡ 18.66) ”አንተ ተንኮለኛ ይህንን የዓለማዊ ስራህን አቁም፡፡ ገና ለገና በሳይንስ እርምጃ አደረግህ እና ሙሉ ትእቢት አይሰማህ፡፡“ ”እናንተ ሁሉ ተንኮለኞች ናችሁ፡፡ ይህንንም ስሜት የማይሰጥ ስራ አቁሙ፡፡ ወደ እኔም ተመለሱ፡፡ እኔም ሙሉ መጠለያ እሰጣችኋለሁ፡፡“ ይህ ክርሽና ነው። ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው፡፡ ይህም ሩህሩህ ተግባር በክርሽናም ትሁት አገልጋዮች ሲካሄድ እናየዋለን፡፡ ታላቅ ዮጊ ወይም ማጂክ ሰሪ አያስፈልግም፡፡ ይህ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ክርሽና የተናገረውን ብቻ ነው መድገም ያለብን፡፡ በዚህም ስርዓት የመንፈሳዊ አባት መሆን እንችላለን፡፡ ሌላ ስሜት የማይሰጥ ነገር መናገር አያስፈልገንም፡፡ ቼታንያ መሀፕራብሁም እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡፡ ”ያሬ ዴክሀ ታሬ ካሀ ክርሽና ኡፓዴሽ (ቼቻ፡ ማድህያ 7.128) የምታገኙትን ሰው በሙሉ ስለ ክርሽና በማስተማር ትእዛዙን ስጡ፡፡ በዚህም መንገድ መንፈሳዊ አባት ሁኑ፡፡ ይኅው ነው፡፡ ይህም በጣም ቀላል ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡