AM/Prabhupada 0118 - መስበክ አስቸጋሪ ስራ አይደለም፡፡

Revision as of 17:33, 1 October 2020 by Elad (talk | contribs) (Text replacement - "(<!-- (BEGIN|END) NAVIGATION (.*?) -->\s*){2,15}" to "<!-- $2 NAVIGATION $3 -->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on SB 1.5.8-9 -- New Vrindaban, May 24, 1969

አምላክን ለማገልገል፡ የተማረከ ሰው በጣም እድለኛ ነው፡፡ “ባሁናም ጃንማናም አንቴ ግያናቫን ማም ፕራፓድያንቴ” (ብጊ 7 19) ለአምላክ አገልግሎት እጅ የሰጠ ሁሉ ተራ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ሰው፡ ከምሁራን፡ ከፈላስፋዎች፡ ከሁሉም ዮጊዎች እና ከካርሚዎች ሁሉ በላይ ነው፡፡ ይህ ለአምላክ ልቦናውን የሰጠ ሰው፡ አብይ ነው፡፡ ይህም የሚስጥራዊ ግምገማ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ በክርሽና ንቃተ ማህበራችን የምናስተምረው፡ ብሃገቨድ ጊታ ቅዱስ መጽሀፍን እንደ አለ፡ እያቀረብን ነው፡፡ ይህም በመፅሀፉ የተጠቀሰው ሂደት እንዴት ሙሉ ልቦናችንን ለክርሽና አምላክ ለመስጠት እንደምንችል ያስተምረናል፡፡ ስለዚህም በዚሁ ቅዱስ መጽሀፍ፡ ክርሽና ይህ ሚስጥራዊ እውቀት ነው ብሎ ጠቅሶታል፡ ምክንያቱም ማንም በቀላሉ ሊቀበለው ስለሚያዳግተው ነው፡፡ ተቀናቃኝ የሚደፍር ሰው፡ ይህንን ሙሉ ልቦናውን ለመስጠት ይችላል፡፡ አንዳንድ ግዜ ለመንፈሳዊ ስብከት ስንወጣ፡ ተቀናቃኞች ሲያጠቁን ይገኛሉ፡፡ ልክ ጌታ ኒትያናንዳ ፕራብሁ፡ በጃጋይ እና በማድሃይ እንደተጠቃ ሁሉ፡፡ እንደዚሁም ጌታ እየሱስ ክርስቶስም በመሰቀል ላይ ተሰቀለ፡ እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊ ሰባኪ ሁሌ ተቀናቃኝ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ክርሽና እንደዚህ አለ፡ ”እነዚህ የእኔን ትምህርት የሚመጣባቸውን አደጋ ደፍረው የሚያሰተምሩ ሁሉ፡ በእኔ በጣም ተወዳጅነት አላቸው፡፡“ እኔ በጣም በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡ ”ናቻ ታስማን ማኑስዬሹ ካሽቺን ሜ ፕሪያ ክርታማሃ“ (ብጊ8 69) ”ከእነዚህም አደጋ ደፍረው ይህንን ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት ከሚያሰተምሩት አገልጋዮቼ በላይ፡ ማንም ማንም ቢኖን የማፈቅረው የለም፡፡“ ስለዚህ ክርሽናን ለማስደሰት ከፈለግን፡ ይህንን ሊመጣ የሚችል አደጋ ደፍረን፡ ማሰተማር አለብን፡፡ የክርሽና መምህር ሁኑ፡፡ የእኔም መንፈሳዊ አባቴ ይህንኑ ሊመጣ የሚችል አደጋ ደፍሮ፡ በመስበክ ላይ ይገኝ ነበረ፡፡ በእርሱም መልካም አርአያ፡ ሁላችንም በስብከት ላይ ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ እናንተንም በዚሁ መንፈሳዊ ስብከት እንድትሰማሩ እያዘጋጀናችሁ እንገኛለን፡፡ ይህን የሰብከት ኃላፊነታችን፡ ምንም እንኳን ያልበለፀገ ቢሆንም፡ ያልበለፀገ ማለትም ለስብከት ገና ያልዳበረ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ይህ ልጅ፡ ለስብከት ቢላክ፡ ብዙ ትምህርት ገና ስለአልቀሰመ፡ ፈላስፋ ሊሆን አይችልም፡፡ ምሁር ሁኖ ለስብከት ሊቀርብም አይችልም፡ ነገር ግን እንደ አቅሙ ሊሰብክ ይችላል፡፡ ሊሰብክ ግን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእኛ ስብከት በቀላሉ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በየቤቱ እየሄድን፡ ”የማከብርህ ሰው ሆይ፡ እባክህ የአምላክን ቅዱስ ስም ሀሬ ክርሽና በማለት ዘምር“ ማለት እንችላለን፡፡ ትንሽ ደግሞ የተማረ አገልጋይ ከሆነ ደግሞ፡ ”እባክህ ይህንን የጌታ ቸይታንያን ትምህርት ተከታተል፡፡ በጣም ጥሩ ትምህርት ነው፡፡ ብዙ ጥቅምም ታገኝበታለህ፡፡“ ብሎ መሰበክ ይቻላል፡፡ እነዚህ ሶስት ወይንም አራት ቃላቶች፡ ጥሩ ሰባኪ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ታድያ ይህ አስቸጋሪ ነውን? አንድ አገልጋይ በጣም ያልተማረ ሊሆን ይችላል፡፡ ምሁር ላይሆን ይችላል፡፡ ፈላስፋ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በየቤቱ በር ሂዶ እያንኳኳ፡ እንዲህ ማለት ይችላል፡፡ ”የእኔ ጌታ፡ አንተ በጣም የተማርክ ሰው ትመስላለህ“ “ነገር ግን አሁን የምታደርገውን ቆም እያደረግህ፡ የአማላክን ቅዱስ ስም ሀሬ ክርሽናን በመዘመር፡ ህይወትህን አድሰው” ማለት እንችላለን፡፡