AM/Prabhupada 0013 - ሀያ አራት ሰዓት ሙሉ በስራ መሰማራት፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 2.49-51 -- New York, April 5, 1966

"ዮጋሃ ካርማሱ ኮሻላም" "ኮሻላም" ማለት የማታለል (የትሪክ) ሙያ ማለት ነው: ሁለት ሰዎች ይሰሩ ነበር: አንዱ ሰው ባለ ሙያ ሲሆን ሌላው ሰው ደግሞ ባለ ሙያ አልነበረም: አንዳንድ ግዜ: ማሸናቸው ተበላሽቶ ይሆናል: ሙያ የሌለው ሰውም ሙሉ ቀን እና ሌሊት ማሽኑን ለመጠገን ይሞክራል: ባለሙያተኛው ግን: መጥቶ ያየውና: በአንድ ግዜ ብልሽቱ ምን እንደሆነ ያውቀዋል: የኤሌትሪክ ክሩንም ወዲህ ወድያ አዘዋውሮ: ማሽኑ በአንድ ግዜ እንዲሰራ ያደርገዋል: ድርም: ድርም: ድርም: ድርም: "አያችሁ?" አንዳንድ ግዜ የኛም ቴፕ ሬኮርደር ይበላሽብናል: በዚህን ግዜም ሚስተር ካርል ወይንም ሌላ ሰው መጥቶ ይሰራልናል: እንደዚሁም ሁሉ ሁሉም ነገር ባለ ሙያ ያስፈልገዋል:: "ካርማ" ካርማ ማለት ስራ ማለት ነው:: ሁላችንም መስራት አለብን:: ያለ ስራ: ይህ ገላችን እና ነፍሳችን እንኳን መንቀሳቀስ አይችልም:: አንዳንድ ግዜም ሰው ያልተግባባው ነገር አለ:: ለመንፈሳዊ ንቃት ስራ መስራት አያስፈልግም ብሎ የሚያምን አለ:: ይህም ስህተት ነው: እንዲያውም በመንፈሳዊ ኑሮ አንድ ሰው ለረጅም ግዜ መስራት አለበት:: አለማዊ ኑሮ ውስጥ ያሉ ሰዎች: የሚሰሩት ለተውሰነ ሰአት ይሆናል:: የሚስሩትም ለ 8 ሰአት በቀን ነው:: በመንፈሳዊ አለም ያሉ ሰዎች ግን: ለ 24 ሰአትም ሊሰሩ ይችላሉ:: ይህ ነው የመንፈሳዊ ስራ እና: የአለማዊ ኑሮ ስራ:: በአለማዊ ኑሮ ላይ: ሰው የሚያስበው ስለ ገላው ጥቅም ብቻ ነው:: ስለዚህም 8 ሰአት ሰርቶ ይደክመዋል:: ለመንፈሳዊ አላማ ግን: ከ 24 ሰአት በላይም መስራት እንመኛለን:: ይሁን እንጂ ከ 24 ሰአት በላይ በእጃችን የለም:: ቢሆንም ረጅም ሰአት ሰርተን ድካም አይሰማንም:: ይህ ነው እኔ በተግባር ያየሁት:: እኔ ሁል ግዜ በስራ ላይ ነኝ:: ወይ በማንበብ: ወይ በመፃፍ: ለ 24 ሰአት ወይ በማንበብ ወይ በመፃፍ: ሲርበኝ ብቻ: ምግብ ለመብላት አቋርጣለሁ: የእንቅልፍ ድካም ሲሰማኝም: ወደ አልጋዬ እሄዳለሁ:: አለበለዛ ግን ድካም አይሰማኝም:: ይህንንም እንደማደርግ: ሚስተር ፖልን መጠየቅ ትችላላችሁ: ይህንንም በማድረግ: ደስታ ይሰማኛል: ድካምም አይሰማኝም:: እንደዚሁም ሁሉ: አንድ ሰው የመንፈሳዊ አንደበት ሲኖረው: ድካም አይሰማውም: እንዲየውም ወደ እንቅልፍ ለመሄድ ይጠላል:: ወደ እንቅልፍ ከመሄዱም እንዲህ ብሎ ያስባል: "ይህ እንቅልፍ አሁን ሊረብሸኝ መጣ" መንፈሳዊ ሰው የእንቅልፍ ሰአቱን ለመቀነስ ይፈልጋል:: እንዲህ ብለንም እንፀልያለን: "ቫንዴ ሩፓ ሳናታኖ ራግሁ ዩጎ ሽሪ ጂቫ ጎፓላኮ" ሰድስቶቹ ጎስዋሚዎች: በጌታ ቼይታንያ: የመንፈሳዊ ትምህርቶችን እንዲወያዩ ተመድበው ነበር:: ስለዚህም በጣም ትልቅ በሆነ ቁጥር የሚመደብ መፃህፍቶች ጽፈዋል:: እና እንቅልፍ ተኝተው ይሆን ብላችሁ ትገረማላችሁ:: ይተኙት የነበረውም ለአንድ ሰአት ተኩል ብቻ ነበር:: ያንንም አንዳንድ ግዜ አያገኙም ነበር::