AM/Prabhupada 0070 - በጥሩ ሁኔታ አስተዳድሩ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Room Conversation -- April 22, 1977, Bombay

መመሪያችንን አጥብቃችሁ ያዙ:ጂቢሲም ነቃ ብሎ እንዲያገለግል አድርጉ: እንደዚህ ሁሉ ነገር በትክክል ሊሄድ ይችላል:እኔም እንኳን ባልኖርም: ይህንን አድርጉ:ይህ ነው የእኔ ትእዛዝ: ትንሽ ትምህርት ያስተማርኩትን ሁሉ ተከተሉ: ማንም ሰው ሊጎዳ አይችልም: ማያም ልትነካችሁ አትችልም: አሁን ክርሽና ሰጥቶናል:የገንዘብ እጥረትም ሊኖረን አይችልም: መጽሃፍ እያተማችሁ ሽጡ: ሁሉም ነገር አለን:በአለም ላይ ጥሩ ጠለላም አለን: ገቢዎችም አሉን:በመመሪያችንን ግን አጥብቃችሁ ያዙ:ተከተሉ: በድንገት ብሞት እንኳን:እናንተ ማስተዳደር ትችላላችሁ:ይኀው ነው: ይህንን ማየት እፈልጋለሁ:ድርጅታችንን በደንብ እያስተዳደራችሁ እንቅስቃሴያችንን ወደ ፊት ግፉ: አሁን አዘጋጁ:ወደ ኋላ እንዳትመለሱ: ጠንቀቅ ብላችሁ ያዙ: “አፓኒ አቻሪ ፕራብሁ ጂቬሪ ሺክሻያ”