AM/Prabhupada 0173 - የሁሉም ጓደኞች ለመሆን እንሻለን፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 1.7.6 -- Vrndavana, April 23, 1975

ስለዚህ:ሰለ ክርሽና:እውቀት መውሰድ ያለብን ወይ ከብሃገቫድ ጊታ ወይ ከሽሪማድ ብሃገቨታም ነው: “ክርሽኔ ፓራማ ፑሩሼ ብሃክቲር ኡትፓድያቴ” ሽሪማድ ብሃገቨታም ከሰማችሁ: በእርግጥ:የመሰረታዊው የክርሽና መመሪያ ካልተረዳችሁ: ያም በሽሪማድ ብሃገቨታም ውስጥ ተጠቅሷል:ወደ መጀመሪያው ላይ: “ድሃርማህ ፕሮጂታሃ ካይታቫ አትራ ፓራሞ ኒርማትሳራናም” ((ሽብ 1 1 2) በዚህም በሽሪማድ ብሃገቨታም:ይህ በሰው የተፈጠረው ሃይማኖት ሁሉ ተወግዟል: መልእክቱም ለፓራማሃምሳዎች ነው “ኒርማትሳራናም” “ኒርማትሳራ” ማለት:ምቀኝነት የሌለው ሰው ማለት ነው: የኛም ምቀኝነት የሚጀምረው ከክርሽና ነው:ክርሽናን አንቀበልም: እንዲህም ይላሉ:“ለምን ክርሽና ብቻ አብይ ይሆናል?ሌሎችም አሉ” ይህ ምቀኝነት ነው:እንደዚህም ምቀኝነታችን የሚጀምረው ከክርሽና ነው: ከዚህም ወደ ብዙ ቦታ:ወደ ተለያዩ መንገዶች ተስፋፍቷል: በእኛ ተራ ኑሮ ላይም ምቀኝነት አለን: በጓደኞቻችን:በአባቶቻችን:በልጆቻችን:ምቀኝነት አለን:ሌላው ይቅርና: ንግድ ሰዎች:አገር:ህብረተሰብ:ማህበር:የተለያየ ምቀኝነት አለ:“ማትሳራታ” “ለምን እሱ መሄድ አለበት?” እኔ እመቀይበታለሁ:ይህ ሁሉ አለማዊ ነው: አንድ ሰው ክርሽናን ሲረዳ ግን:ምቀኝነት አይኖረውም:በክርሽና ንቃት የዳበረ ይሆናል: የሁሉም ጓደኛ ለመሆን ይፈልጋል:“ሱህርዳህ ሳርቫ ብሁታናም” ይህ ክርሽና ንቃተ ማህበር ማለትም:የሁሉም ጓደኞች መሆን እንፈልጋለን ማለት ነው: ያለ ክርሽና ንቃት በአለማዊ ስቃይ ላይ ስለሚገኙም:በር ለበር እየሄድን እናስተምራለን: ከተማ ለከተማ:ሰፈር ለሰፈር:አውራጃ ለአውራጃ:ይህንን ክርሽና ንቃትን ለማስተማር:እንሄዳለን: በክርሽናም በረከት:አዋቂ የሆነውን ህብረተሰብ ለመሳብ በቅተናል: እንደዚሁም ምቀኘነት የሌለውን ስርአት ብንከተል:እንበለጽጋለን: ምቀኝነት የእንስሳ ባህርይ:የውሻ እና የአሳማ ባህርይ ነው: የሰው ልጅ ”ፓራ ዱክሃ ዱክሂ“ አዛኝ መሆን አለበት: የሌሎችን ስቃይ አይቶ በጣም ማዘን ይገባዋል: በዚህ አለም የክርሽናን ንቃት ፍለጋ:በመሰቃየት ላይ ነው: የእኛም ተግባር ይህን የክርሽና ንቃታቸውን መቀስቀስ ነው:መላ አለምም ደስታኛ ይሆናል: ”አናርትሃ ኡፓሳማም ሳክሳድ ብሃክቲ ዮጋም አድሆክሳጄ ሎካስያ አጃንታሃ“ ሰዎችም ስለዚህ እውቀት የላቸውም:ስለዚህም ይህንን እንቅስቃሴ ወደ ፊት መግፋት አለብን: ”ሎካስያጃን ቪድቫምስ ቻክሬ ሳትቫታ ሳምሂታም“ (ሽብ 1 7 6) ሌላው የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን ስም ”ብሃገቨት ድሃርማ“ ነው: ብሃገቫት ድሃርማ:ይህን ከተቀበልን:መላ የሰው ልጅ ህብረተሰብ ደስታኛ ይሆናል:አመሰግናለሁ: