AM/Prabhupada 0357 - ይህንን የዓብዩ ጌታ እምነት የሌለበትን ስልጣኔ ለመቋቋም አብዮት መፍጠር እፈልጋለሁ፡: Difference between revisions

(Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0357 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1973 Category:AM-Quotes - M...")
 
m (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
 
Line 7: Line 7:
[[Category:AM-Quotes - in USA, Los Angeles]]
[[Category:AM-Quotes - in USA, Los Angeles]]
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- BEGIN NAVIGATION BAR -- DO NOT EDIT OR REMOVE -->
{{1080 videos navigation - All Languages|Amharic|AM/Prabhupada 0356 - የምንናገረው ሁሉ በሀሳባዊ ግምታችን የተፈጠረ ሳይሆን ስልጣን ካላቸው ሻስትራዎች ወይንም ስነፅሁፎች ነው፡|0356|AM/Prabhupada 0361 - እነርሱ የእኔ ጉሮዎች “መምህራን” ናቸው እንጂ እኔ የእነርሱ ጉሩ አይደለሁም፡፡|0361}}
<!-- END NAVIGATION BAR -->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<div class="center">
<div class="center">
Line 19: Line 22:


<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<mp3player>http://vaniquotes.org/w/images/731211M2.LA_clip.mp3</mp3player>
<mp3player>https://s3.amazonaws.com/vanipedia/clip/731211M2.LA_clip.mp3</mp3player>
<!-- END AUDIO LINK -->
<!-- END AUDIO LINK -->



Latest revision as of 06:05, 29 November 2017



Morning Walk -- December 11, 1973, Los Angeles

ፕራብሁፓድ፡ ጤንነቴ በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን እየሞከርኩኝ እገኛለሁ፡፡ ይህን ነው የእኔ ፍላጎት፡፡ ይህንን አንድ ትልቅ እንቅስቃሴ ለመጀመር እፈልጋለሁ፡፡ ይህንን አብዩ የመላእክት ጌታ የሌለበትን ስልጣኔያቸውን ለመቋቋም እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ የጋለ ፍላጎት፡፡ ይህንንም ስርዓት ለማስተማር እና ለመመምራት በአሜሪካኖች መጀመር ጥሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም እነሱ በአሁኑ ግዜ የዓለም መሪዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ አሁን ግን እውነተኛ መሪዎች መሆን ይገባቸዋል፡፡ በዚህም መንገድ መላ ዓለም ደስተኛ ይሆናል። ለዚህም መመሪያ መስጠት እችላለሁ፡፡ የበላይ ሀላፊነት ያላቸው አሜሪካኖች ወደ እኔ ቢመጡ እንዴት የዓለም መሪዎች ለመሆን እንደሚችሉ መመሪያ ለመስጠት እችላለሁ፡፡ ይህም የሀሰተኛ መሪ ሳይሆን እውነተኛ እና ትክክለኛ መሪዎች ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አብዩ አምላክ በብዙ ነገር በረከት ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም እንቅስቃሴ የጀመረው ከአሜሪካ ነው፡፡ ይህንንም እንቅስቃሴ የጀመርኩት ከኒው ዮርክ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህንን እንቅስቃሴ መንግስት ሶስተር ብሎ መውሰድ ይገባዋል፡፡

ህርዳያናንዳ፡ አሜሪካ በጣም አስፈላጊ አገር ነው የምትለውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ህርዳያናንዳ፡ እንደምታስበው.....

ፕራብሁፓድ፡ ሰለዚህም ወደ አገራችሁ መጥቻለሁ

ህርዳያናንዳ፡ ምናልባት...

ፕራብሁፓድ፡ ምክንያቱም እናንተ በጣም አሰፈላጊዎች ናቸሁ፡፡ አሁን ማድረግ ያለብህ... በእኔ መመሪያ ስር ደግሞ ከአሁኑ በላይ የውሸት ሳይሆን የእውነት አስፈላጊዎች ማድረግ ይቻላል፡፡

ህርዳያናንዳ፡ እንደዚያ ከሆነ እዚሁ በመቅረት ስብከቴን መቀጠል ይገባኛል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ?

ህርዳያናንዳ፡ ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ እኔም እዚሁ በመቅረት ሩፓ ኑጋን በማገዝ መርዳት አለብኝ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህንን መላ ሕብረተሰብ ወደ አብዩ አምላክ ንቃት ቀይሩት፡፡ ምክንያቱም በኮንስቲቲውሽናቸው አውጀውታል፡፡ “በአብዩ አምላክ እናምናለን” አሁን ታድያ ይህንን ኮስተር ብለው መከታተል ይገባቸዋል፡፡ “አብዩ አምላክ” ማለት ምን ማለት ነው? "እምነት“ ማለትስ ምን ማለት ነው? ይህንን ስብከት ጀምሩ፡፡ ይህንንም በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በአብዩ አምላክ እናምናለን፡፡ ሰለዚህም መላ ሕይወታችንን መስዋዕት አድረገን እንገኛለን፡፡ ይህ ነው በአብዩ አምላክ እምነት ማለት፡፡ በየአገልግሎቱ ቤት ሲጃራ እያጨሱ በአብዩ አምላክ እናምናለን ማለት አይበቃም፡፡ ይህ ዓይነቱ እምነት አይፈለግም፡፡ ትክክለኛ እምነት ግን ያሰፈልጋል፡፡