AM/Prabhupada 0458 - የሀሬ ክርሽና መዝሙርን መዘመር - ይህም ክርሽናን በምላሳችን እንደመንካት ነው፡፡

Revision as of 03:31, 24 June 2015 by Visnu Murti (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0458 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1977 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Lecture on SB 7.9.6 -- Mayapur, February 26, 1977

ፕራብሁፓድ፡ ጌታ ናራሽንግሀዴቫም የፕራህላድን ጭንቅላት በእጁ እንደዳበሰው ልክ እንደዚህም ዓይነት በረከት ሊመጣላችሁ ይችላል፡፡ ይሄስ በረከት ምንድን ነው? እንዴትስ ሊመጣ ይችላል? ናራሺንግሀ ዴቭ በአጠገባችን የለም፡፡ ክርሽናም በአጠገባችን የለም፡፡ አይደለም እርሱ በአጠገባችን አለ፡፡ “ይህስ እንዴት ይሆናል?" ናሜ ሩፔ ካሊ ካሌ ክርሽና አቫታራ (ቼቻ፡ አዲ 17.22) ክርሽና በስሙ በአጠገባችን አለ፡፡ ክርሽና ይህም የክርሽና ቅዱስ ስም ወይንም ሀሬ ክርሽና ከክርሽና እራሱ የተለየ ሆኖ አይገኝም፡፡ ፍፁም ክርሽና ነው፡፡ ክርሽና የክርሽና ሙርቲ የክርሽና ስም እና ክርሽና እራሱ እያንዳንዳቸው አንድ ዓይነት ሆነው ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት ልዩነትም የላቸውም፡፡ በዚህ ዘመን ቅዱስ ስምን መዘመር ብቻ ነው የሚያስፈልገን፡፡ ኪርታናድ ኤቫ ክርሽናስያ ሙክታ ሳንጋሀ ፓራም ቭራጄት፡፡ (ሽብ፡ 12.3.51) የክርሽናን ስም በቀላሉ በመዘመር ብቻ ናማ ቺንታመኒ ክርሽና ቼይታንያ ራሳ ቪግራሀ ፑርናህ ሹድሆ ኒትያ ሙክታሀ (ቼቻ ማድህያ 17.133) የክርሽና ቅዱስ ስም ከክርሽና የተለየ ነው ብላችሁ ፈጽሞ እንዳታዩ፡፡ ፑርናም (ኢሾፓኒሻድ መነሻ ጥቅስ)(ሙሉ) ነው፡፡ ፑርናህ ፑርናም አዳሀ ፑርናም ኢዳም (ኢሾፓኒሻድ መነሻ ጥቅስ) ሁሉም ነገር ፑርና ነው፡፡ ፑርና ማለት”ሙሉ“ ማለት ነው፡፡ ይህንንም ሙሉነት በኢሾፓኒሻድ መጽሀፋችን ውስጥ ሙሉ በሉሙ ለመግለጽ ሞክረናል፡፡ እንዳንበባችሁትም ሁሉ ከክርሽና ቅዱስ ስም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አድርጉ፡፡ ልክ ፕራላድ መሀራጅ እንደአገኘው በረከት እናንተም ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡ ይህም የንርሺንግሀ ዴቭ መዳፍ በቀጥታ እንደሚነካችሁ በመቁጠር ነው፡፡ ምንም ልዩነትም አይኖርም፡፡ የሀሬ ክርሽናንም ቅዱስ ስም በዘመራችሁም ግዝ ሁልግዜ እንዲህ ብላችሁ አስቡ፡፡ ክርሽናን በምላሳችሁ እንደነካችሁት አድርጋችሁ ማወቅ አለባችሁ፡፡ ከዚይም በኋላ ልክ እንደ ፕራላድ መሀራጅ አንድ አይነት በረከት እንደምታገኙ የታወቀ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡

አገልጋዮች ....ጃያ