AM/Prabhupada 0634 - ክርሽና በዚህ በዓማዊ ምትሀት ፈፅሞ ሊጠቃ አይችልም፡፡

Revision as of 08:14, 23 June 2015 by Visnu Murti (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0634 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1973 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Lecture on BG 2.28 -- London, August 30, 1973

ስለዚህ ቭያሳዴቭ ይህንን ለማየት ቻለ “አፓሽያት ፑሩሻም ፑርናም” ይህንንም አየ። ይህም ልክ ከደመና በላይ እንደሚበር አይሮፕላን ይመሰላል፡፡ ፀሀይ በደመና አትጠቃም፡፡ ምንም እንኳን ከአይሮፕላኑ በታች የምናየው ከፍተኛ ስፋት ያለው ደመና ቢኖርም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማያ ክርሽናን ልታጠቃ አትችልም፡፡ ስለዚህ ብሀገቨድ ጊታ እንዲ ብሎ ይገልጽልናል፡፡“ዳይቪሂ ኤሻ ጉናማዪ ማማ ማያ” ማማ ማያ (ብጊ፡ 7.14) ክርሽና እንዲህ ይላል “የእኔ የምትሀት ሀይል” ክርሽና በዚህ የምትሀት ሀይል ሊጠቃ አይችልም፡፡ ይህም እንደ ፀሀይ ሊመሰል ይችላል፡፡ ነገር ግን የማያቫዲ ፈላስፋዎች ክርሽናን የሰው ቅርፅ የሌለው የፍፁም እውነት አካል ነው ብለው ይሰብካሉ፡፡ በዚህ ዓለም ሰለሚመጣውም የፍጹም እውነት ትውልድ ያምናሉ ነገር ግን ፍልስፍናቸው በመጨረሻ ፍፁም እውነት የሰው ፎርም የሌለው ነው ብለው ነው፡፡ ልክ እንደ ሰው ሆኖ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ ሲመጣም የማያን ገላ ይዞ ይመጣል ብለው ይሰብካሉ፡፡ ይህም የማያቫዲ ፍልስፍና ነው፡፡ እንዲህም ይላሉ፡፡ “ክርሽና እንደ አብዩ አምላክ ልንቀበለው እንችላለን፡፡ ነገር ግን የቁሳዊ ገላን ተቀብሏል፡፡” በዚህም ዓይነት አብዩ የመላእክት ጌታን ከተራ ነፍሳት ጋር ሊያወዳድሩት ይፈልጋሉ፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ የተወገዘ ነው፡፡ እንዲህም ተብሏል፡፡ “አቫጃናንቲ ማም ዱድሀ ማኑሺም ታኑም አሽሪታም (ብጊ፡ 9.11) ክርሽና በዋናው ቅርፁ ሰለሚመጣ ይህም በሁለት እጅ ፎርሙ ይህም በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥም ተገልጿል፡፡ ”የሰው ልጅ የተፈጠረው በአብዩ አምላክ ምስል ነው፡፡“ ሰለዚህ አብዩ አምላክ ሁለት እጆች አሉት፡፡ የአብዩ ጌታ የቪሽኑ 4 እጆች ፎርም የአብዩ ጌታ ዋነኛው ፎርም አይደለም፡፡ የቪሽኑ ፎርም የሳንካርሻና ሁለተኛ ፎርሙ ነው፡፡ ሰለዚህ ክርሽና በማያ በፍፁም ተጠቅቶ አይታወቅም፡፡ ይህ ነው ድምደማው፡፡