AM/Prabhupada 0674 - ምን ያህል መብላት እንደሚያስፈልጋችሁ አዋቂ ሁኑ፡፡ ይህም በጤንነት ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጋችሁን ያህል ብቻ ነው፡፡

Revision as of 07:23, 23 June 2015 by Visnu Murti (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0674 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1969 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid URL, must be MP3

Lecture on BG 6.16-24 -- Los Angeles, February 17, 1969

አገልጋይ፡ ፕራብሁፓድ፡ ምን ያህል መተኛት እና ምን ያህል መብላት እንዳለብን እራሳችን ለይተን ማወቅ እንችላለን? አንዳንድ ሙከራ እና ለመቀነስ እየሞከርን ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙውን ግዜ እራሳችንን እናሞኛለን፡፡ እንዲህም እንላለን “ይህንን ያህል ምግብ ያስፈልገኛል፡፡" ወይንም ደግሞ "እኔ ሰባት ወይንም ስምንት ሰዓት ያህል መተኛት ያስፈልገኛል፡፡” ነገር ግን ምክንያት እያደረግን ነው ያለነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ምግብ ለመውሰድ ውሳኔ ማድረግ? ጥያቄህ ምንድን ነው?

አገልጋይ፡ የእኛ የራሳችን ማመዛዘን ያሰፈልገዋልን? ምን ያህል መተኛት ወይንም መብላት እንደሚያስፈልገን እራሳችን ማመን እንችላለን?

ፕራብሁፓድ፡ በእርግጥ ያ እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡ ማመዛዘን የግድ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን አነስ ያለ ምግብ በመውሰድ ስህተት ብታደርግ ያ ስህተት መጥፎ አይደለም፡፡ (ሳቅ) እንደገና ለመጨመር እራስህን አታስገድድ፡፡ ለምሳሌ ይገባኛል ከምተለው ምግብ በታች ወስደህ ይሆናል፡፡ ይህ አይነቱ ስህተት መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሚገባህ በላይ ምግብ የምትወስድ ከሆነ ያ ጥሩ አይደለም፡፡ ስለዚህ ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡ የማመዛዘንህም ስህተት አለ ብለህ የምታምን ከሆነ ደግሞ አነስ ያለ ምግብ በመውሰድ ስህተት ብታደርግ ይሻልሀል፡፡ ከሚፈለገው በላይም በመውሰድ ስህተት አታድርግ፡፡ ይህም የማመዛዘን እርገጠኛነት ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ አንድ ሰው ምን ያህል ገላውን ብቁ ለማድረግ መብላት እንዳለበት አዋቂ መሆን አለበት፡፡ ይህ በሁሉም ዘንድ ያለ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን ብዙ ስህተት አይታይም፡፡