AM/Prabhupada 0003 - ወንድም እንደ ሴት ነው፡፡



Lecture on SB 6.1.64-65 -- Vrndavana, September 1, 1975

[ሽ ባ 6 1 64] "ታም ኤቫ ቶሳያም አሳ ፒትርዬናርትሄና ያቫታ ግራምዬር ማኖራሜይህ ካሜህ ፕራሲዴታ ያትሃ ታትሃ" ሴትየዋን ካየም በኋላ: በስሜታዊ ፍላጎቱ: ሁል ግዜ: ለሃያ አራት ሰአት በሃሳብ ተሰምጦ ተቀመጠ:: "ካሜይስ ቴይስ ቴይር ህርታ ግናና" [ብ ጊ 7 20] አንድ ሰው: በስሜታዊ ፍላጎቱ ብጥልቅ ከሰመጠ: አዋቂነቱን ሊያጠፋ ይችላል:: ይህም መላ አለም: በዚህ በስሜታዊ ጥልቅ ፍላጎት ምክንያት: በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል:: ይህም አለማዊ ምድር ይባላል:: እንዲሁም እኔም እናንተም: ሁላችንም: የጥብቅ ስሜታዊ ፍላጎት: ኖሮን እንገኛለን:: አንዳንድ ግዜ: የኔ ፍላጎቶች ካልተሟሉ: የእናንተም ፍላጎቶች ላይሟሉ ይችላሉ:: በዚህም ምክንያት: እኔ የእናንተ ጠላት: እናንተም የእኔ ጠላት ልትሆኑ ትችላላችሁ:: የእናንተንም መበልፀግ በምቀኝነት ምክንያት: ማየት አልችልም:: እናንተም የእኔን መበልፀግ በጥሩ ልቦና ለማየት ያዳግታችኋል:: ይህም: የአለማዊ ምድር ኑሮ ነው:: ምቀኝነት: ስሜታዊ ፍላጎቶች: "ካማ: ክሮድሃ: ሎብሃ: ሞሃ: ማትሳርያ" ይህ: የዓለማኦዊ ኑሮ: መሰረት ነው:: እንዲሁም እንዲህ ሆነ:: ልምምድ: ይወስድ የነበረው: "ብራህመና" (ቈስ) ለመሆን ነበር:: "ሻሞ ዳማ" ነገር ግን: ትምህርቱ ተደናቀፈ:: ይህም የተፈጠረው በሴት ልጅ ሃሳብ በመሰመጡ ነው:: ስለዚህም: በቬዲክ ህብረተሰብ ስልጣኔ: የሴት ልጅ ለመንፈሳዊ ኑሮ ብልጽግና: እንቅፋት ልትሆን ትችላለች:: የቬዲክ ህብረተሰብ ስልጣኔ የተመሰረተው: እንዴት የሴት ልጅን ያለአግባብ መቅረብን በማስወገድ ነው:: የሴት ልጅ ብቻ: የሴት ልጅ ናት ብለንም ማሰብ የለብንም:: ወንድም እንደ ሴት ሊሆን ይችላል:: የሴት ልጅን ግን ዝቅ አድርጋችሁ እና የወንድ ልጅን ከፍ አድርጋችሁ ማየት አይገባችሁም:: የሴት ልጅ በፍጥረቷ ታስደስታለች: ወንድ ልጅ ደግሞ ይደሰታል:: ይሄ ስሜት የረከሰ ስሜት ነው:: የሴት ልጅን ለስሜታዊ ደስታዬ ብዬ ባያት: ይሄ የወንድ ልጅ ጠባይ ነው:: ሴት ልጅም: ወንድን ለስሜታዊ ደስታዋ ብታይ: ይህ እንደ ወንድ ልጅ ጠባይ ሁኖ ይታያል:: ሴት ልጅ ማለት አስደሳች ስትሆን ወንድ ልጅ ደግሞ ተደሳች ማለት ነው:: እንዲሁም ሁሉ: ሴትም ሆነች ወንድ ልጅ: የመደሰት ስሜት እና አዝማሚታ ያለው ሁሉ እንደወንድ ነው የሚቆጠረው:: (ፑሩሻ) በዚህ ምድር ላይ: ሁለቱም ፆታዎች እንደ ሴት ልጅ: አምላክን ለማስደሰት ብቻ ነው የተፈጠሩት:: ይሁን እንጂ: ሁለቱም ፆታዎች የአምላክን ደረጃ በመያዝ: እንዴት መደሰት እንደሚችሉ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ:: የአምላክንም ደረጃ (ፑሩሻ) አርቴፊሽያሊ ይዘን እንገኛለን:: በመንፈሳዊ መሰረተ ትምህርት ግን: ሁላችንም የአምላክ"ፕራክርቲ" (እንደሴት አስደሳች እና አገልጋይ) ነን:: ይህ በአለም ላይ የሚገኘው "ወንድ እና ሴት" ግን: የጊዝያዊ የውጪ ሽፋን ነው::