AM/Prabhupada 0006 - ሁሉም ሰው አብዩ አምላክ ነው - የሞኞች ገነት
Lecture on SB 1.15.49 -- Los Angeles, December 26, 1973
ሁሉም ሰው ትእቢት አለው:: "እኔ አውቃለሁ: ሁሉን ነገር አውቃለሁ" ብለን እናስባለን:: በዚህም ምክንያት መንፈሳዊ አስተማሪ አያስፈልገንም ብለን እናስባለን:: "ጉሩ" ወይንም የመንፈሳዊ አስተማሪያችንን ግን መቅረብ ያለብን መንገድ ግን እንዲህ ነው: ሙሉ ልቦናችንን በመስጠት: "በልቤ ብዙ የማይረባ ቁሻሻ ነገር ብቻ ነው የማውቀው:: አሁን አንተ ትምህርቱን ስጠኝ::" ይሄ ትሁት አቀራረብ ይባላል:: ልክ አርጁና እንደተናገረው:: "ሺሽያስ ቴ አሃም ሻድሂ ማም ፕራፓናም" [ብጊ 2 7] በአርጁና እና በጌታ ክርሽና መሃከል ክርክር ሲፈጠር: ክርክሩም መፍትሄ ካላገኘ: ያን ግዜ አርጁና ለክርሸና በትህትና ቀረበ:: አርጁናም እንዲህ ይል ነበር:: "ውድ ክርሽና ሆይ: እስከ አሁን እንደ ጓደኞች ስንነጋገር ነበር: ከአሁን በኋላ ግን: አንተን እንደ መንፈሳዊ አባቴ ተቀብዬሃለሁ:: ሀላፊነቴም ምን እንደሆነም አስተምረኝ:: ይህም "ብሃገቨድ ጊታ ነው::" በዚህም መንገድ መማር ይገባናል:: "ታድ ቪግናናርትሃም ሳ ጉሩም ኤቫ አብሂጋቼት" [ም ዩ 1 2 12] ይህም የቬዲክ መመሪያ: የህይወታችን ዋጋ ምን እንደሆነ ልንረዳው ያገለግለናል:: እንዴትስ ነው የሚለዋወጠው? ከአንድ ገላስ ወደ ሌላው ገላስ ነፍሳችን እንዴት ብላ ነው የምትሸጋገረው? እኔስ ምንድን ነኝ? እኔ ይህ ገላ ነኝ ወይንስ ከዚህ ገላ አልፎ ተርፎ ሌላ ህልውና አለኝ? እነዚህ ጥያቄዎች መጠየቅ አለባቸው:: ይህም የሰው ልጅ ዋናው ተግባር ነው:: "አትሃትሆ ብራህማ ጂግናሳ" ይህ ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ነው:: በዚህ "ካሊ ዩጋ" በተባለው የብጥብጥ ግዜ ግን: ያል ምንም እውቀት: ያለ ምንም ጥያቄ: ያለ መንፈሳዊ አስተማሪ: ያለ ምንም መጽሃፍ: ሁሉም ሰው እንደ አምላክ መሆን ይፈልጋል:: ይኅው ነው:: ይህ ሁሉ እየተካሄደ ነው:: ይህ የሞኞች ገነት ነው:: ይህ ምንም ሊረዳን አይችልም:: ስለ ቪዱርም ታሪክ ስሙ:: እሱም ቢሆን: [ሸ ባ 1 15 49] ቪዱሮ ፒ ፓሪትያጅያ ፕራብሃሴ ዴሃም አትማናሃ ክርሸናቬሼና ታክ ቺታሃ ፒትርብሂህ ስቫ ክሳያም ያዮ እርሱም: "የምናገረውም ስለ ቪዱር ነው:" ቪዱር ያማራጃ ነበረ:: (የሲኦል ጌታ) አንድ የመንፈሳዊ ሰው: የቅጣት ፍርድ እንዲፈረድበት ቀረበ:: (ሲኦል ውስጥ) ይህም መንፈሳዊ ሰው ያመራጅን እንዲህ ብሎ ጠየቀው:: በህይወቴ ውስጥ ምን አይነት ሃጥያት እንደሰራሁ ትዝ አይለኝም:: ለምን ይሆን እዚህ ድረስ ለፍርድ የመጣሁት ብሎም ጠየቀ:: ያመራጅም እንዲህ አለ:: "አታስታውስም እንጂ: በልጅነትህ አንዲት ጉንዳን አንስተህ በመርፌ ፊንጢጣዋ ላይ ወጋሃት እና ለመሞት በቃች::" በዚህም ምክንያት ለፍርድ ቀርበሃል:: እስቲ ይህንን ተመልከቱ:: በልጅነቱ እና: በአላዋቂነቱ ይህንን ሃጥያት በመስራቱ ለፍርድ ቀረበ:: እኛ ደግሞ በዚህ ዘመን: ከሃይማኖት ህግ በመውጣት "አትግደል" እየተባለ: በብዙ የሺህ የሚቆጠሩ የእንስሳ መግደያ ድርጅቶችን አቋቁመናል:: ይህም ትርጉም የሌለውን ቲዮሪ "እንስሳ ነፍስ የለውም" በሚል ሀሰታዊ አስተሳሰብ ይዘን ነው:: ይህንንም ቀልድ እዩት:: ይህም እየተካሄደ ነው:: እኛ በሰላም ለመኖር እንሻለን::