AM/Prabhupada 0019 - የምትሰሙትን ሁሉ ለሌሎች ማስተላለፍ ይገባችኋል፡፡
Jagannatha Deities Installation Srimad-Bhagavatam 1.2.13-14 -- San Francisco, March 23, 1967
ለምሳሌ: እኔን ለማወቅ ወይንም ስለ እኔ ለማወቅ ብትፈልጉ: ጓደኛዬን ለመጠየቅ ትችላላችሁ: "ስዋሚጂ እንዴት ነው?" እርሱም አንድ ነገር ሊላችሁ ይችላል: ወይንም ሌሎች ሊነግሩአችሁ ይችላሉ:: ነገር ግን ስለ እኔ እራሴ ብነግራችሁ ግን "እኔ እንዲህ ነኝ: እንዲህ ሁኛለሁ" ብዬ ብነግራችሁ ግን: ይህ ትክክል ይሆናል:: ይህ ትክክል ይሆናል:: እንደዚሁም ሁሉ: አምላክን ለማወቅም ከፈለጋችሁ: ወይ መገመት ወይ ብቻችሁን አተኩራችሁ ማሰብ አይገባችሁም:: ይህ ይሚቻል አይደለም:: ይህም የምንረዳባቸው የተፈጥሮ ስሜት አካሎ ቻችን ፍፁም የሆኑ ስለአልሆኑ ነው:: እና መንገዱ ምንድን ነው? መንገዱም ከክርሽና ከራሱ መስማት ነው: ክርሽና በደግነቱ ወደ ምድር ብሃገቫድ ጊታን ለመናገር መጥቷል: “ሽሮታቭያህ” እኛም መስማት ብቻ ነው የሚገባን: “ሽሮታቭያህ እና ኪርቲታቭያስ ቻ” በጥሞና ብታዳምጡ እና:የክርሽናን የንቃት ትምህርት ክፍሎች ገብታችሁ ብታዳምጡ: ወጥታችሁ ብትረሱ ግን: ይህ ጥሩ አይሆንም: መርሳት እንድትሻሻሉ አይረዳችሁም: እና “ኪርቲታቭያስ ቻ” ማለት ምንድን ነው? “የሰማችሁትን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ አለባችሁ” ይህ የተሳካ ያደርጋችኋል: ስለዚህም “ባክ ቱ ጎድሄድ (ወደ አምላክ)” የሚባል መጽሄት አዘጋጅተናል:: ተማሪዎቹም ያዳመጡትን ሁሉ: እንዲያስቡበት እና እንዲጽፉ: ተመርተዋል: “ኪርቲታቭያሽ” መስማት ብቻ አይደለም: አንአንድ ግዜ እንዲህ እንላለን:“ለብዙ ሚሊዮን አመታት ሰምቼአለሁ ነገርግን ልረዳው አልቻልኩም” ይህም የሰማነውን ነገር ሁሉ ስለማንደግማው እና ለሌላ ሰው ስለማናካፍለው ነው: የሰማነውን መድገም ያስፈልገናል:“ኪሪታቭያስ ቻ ሽሮታቭያ ኪርታቭያስ ቻ ድህዬያህ” እሱንስ የማናስበው ከሆነ:እንዴት መፃፍ እና: እንዴት ስለእርሱ መናገርስ እንችላለን? ስለ ክርሽና ስትሰሙ:ማሰብ ትጀምራላችሁ: ከዚያም ስለ እርሱ መናገር ትችላላችሁ: አለበለዛ ግን አይቻልም: ስለዚህ እንዲህ ተብሏል: “ሽሮታቭያህ ኪርቲታቭያሽ ቻ ድህዬና እና ፑጅያስ ቻ” መስገድም ይገባናል:ለዚህም የክርሽና ደይቲ (ምስል)ያስፈልገናል: ስለ ክርሽና:ማሰብ:መናገር:መስማት:መስገድ: ያስፈልገናል:“ፑጅያስ ቻ” ታዲያ ይህ የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው? አይደለም!“ኒትያዳ” ሁልግዜ መሆን አለበት: “ኒትያዳ” ይሄ ነው መንገዱ: ይህንን መንደድ ይተከተለ ሁሉ: በአለም ላይ የሚገኘውን እውነት ለመረዳት ይችላል: ይህም የ“ሽሪማድ ብሃጋቫታም” መጽሃፍ በግልጽ የተጠቀሰ መልእክት ነው: