AM/Prabhupada 0032 - ለመናገር የምፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ በመፅሀፍቶቼ ተነግረዋል፡፡



Arrival Speech -- May 17, 1977, Vrndavana

ፕራብሁፓዳ:“ለመናገር እያዳገተኝ ነው” በጣም ድክመትም እየተሰማኝ ነው: ወደ ሌላ ቦታም መሄድ ነበረብኝ:ወደ ቻንዲጋርህ ፕሮግራም: ነገር ግን ድክመት ስለሚሰማኝ ሰርዤዋለሁ: የጤናዬ ጉዳይ በጣም እየወደቀ ነው: ስለዚህም ወደ ቭርንዳቫና መምጣት ወስኛለሁ: ሞትም ከመጣ እዚህ ቢመጣ ይሻለኛል: ከዚህ ሌላ ለማለትም የሚያስፈልግ ነገር አይኖርም: መናገር የሚያስፈልገኝን ሁሉ: በመጽሃፎቼ ተናግሬአቸዋለሁ: አሁን እናንተ ተረድታችሁት:የእናንተን እርምጃ ቀጥሉ: እኔ እዚህ ምድር ላይ ኖርኩም አልኖርኩም ምንም ለውጥ አያመጣም: ክርሽና ለዘለአለም ነዋሪ እንደመሆኑም: እንደዚሁም ነፍስ ለዘለአለም ነዋሪ ናት: ነገር ግን: “ኪርቲር ያስያ ሳ ጂቫቲ” አንድ አማላክን በደንብ ያገለገለ ሰው ለዘለአለም ነዋሪ ነው: እናንተም እንዴት ክርሽናን እንደምታገለግሉ ተምራችኋል: እንዲሁም ከክርሽና ጋር ለዘለአለም እንኖራለን: ህይወታችን ዘለአለማዊ ናት: “ና ሃንያቴ ሃንያማኔ ሻሪሬ” (ብጊ 2 20) ይህ ገላ ለጊዜው ቢጠፋ: ምንም ችግር የለውም: ገላ ጠፊ ወይንም ሟች ነው: "ታትሃ ዴሃንታራ ፕራፕቲህ“ (ብ ጊ 2 13) ስለዚህ:ክርሽናን እያገለገላችሁ ለዘልአለም ኑሩ: በጣም አመሰግናለሁ: አገልጋዮች ”ጃያ“