AM/Prabhupada 0036 - የሕይወታችን ዓላማ፡፡



Lecture on BG 2.1-11 -- Johannesburg, October 17, 1975

ይህም አለማዊ ኑሮአችን: እንቆቅልሽ ሁኖ ግራ ሲያጋባን: ምን ማድረግ እና: ምን አለማድረግ እንዳለብን ለመረዳት ሲያዳግተን: በዚያንም ግዜ ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) መቅረብ አለብን: ይህን ትእዛዝ ነው እዚህ የምናየው: "ፕርቻሚትቫም ድሃርማ ሳሙድሃ ቼታሃ" ኑሮ ግራ ሲያጋባን: የትኛው ሃይማኖታዊ እና ሃይማኖታዊ ያልሆነውን መለየት ያዳግተናል: ያለንንም ደረጃ በአግባቡ አንጠቀምበትም: ይህም እንዲህ ይባላል: "ካርፓንያ ዶሻፓሃታ ስቫብሃቫ (ብጊ 2 7) በዚህም ግዜ ጉሩ ያስፈልገናል: ይህ ነው የቬዲክ ቅዱስ መጻህፍት ትእዛዝ: "ታድ ቪግናናርግሃም ሳ ጉሩም ኤቫብሂጋቼት ሽሮትሪያም ብራህማ ኒስትሃም" (ሙኡ 1 2 12) ይህ ነው ሃላፊነት ማለት: ይህ ነው ሥልጣኔ ማለት: በህይወታችን ብዙ አይነት ፍዳዎች ያጋጥሙናል: ይህ በተፈጥሮ ያለ ነው:: ይህም አለም በተለያዩ ችግሮች የተሞላ ነው:: "ፓዳም ፓዳም ያድ ቪፓዳም" (ሽብ 10 14 58) አለማዊ ህይወት ላይ: በየእርምጃችን አደጋ ሊያጋጥመን ይችላል ማለት ነው: ይህ የአለማዊ ህይወት መሰረቱ ነው: ስለዚህም ከጉሩ መመሪያ መውሰድ አለብን:: ከአስተማሪው: ከመንፈሳዊ አባታችን: በህይወታችን ላይ እንዴት በቀና እንደምንራመድ መማር አለብን: ይህም በኋላ በደንብ ይገለጻል:: የህይወታችን መድረሻ አላማ: ቢያንስ በዚህ በያዝነው የሰው ልጅ ህይወታችን: እንዴት ማድረግ እንደሚገባን በአርያን ስልጣኔ: ተገልጾልናል:: የህይወታችን መድረሻ አላማ: የነፍሳችን መሰረታዊ ደረጃ ምን እንደሆነን መረዳት ነው:: "ማነኝ እኔ?“ ምንድን ነኝ?” እኔ (ነፍሴ)ምን እንደሆንኩኝ የማላቅ ከሆነ ግን:እኔም ከድመቶች እና ከውሾች አልሻልም ማለት ነው: ውሾች እና ድመቶች የነፍሳቸው ሚና ምን እንደሆነ አያውቁም:የሚያስቡትም ገላቸው እንደሆኑ ነው እንጂ ነፍሳቸው ምን እንደሆነች አያውቁም: ይህ ሁሉ ይተነተናል:ስለዚህ በህይወታችን ኑሮ እንቆቅልሽ ሁኖ ግር የሚለን ደረጃ ላይ ስንደረስ: (በመሰረቱ ሁላችንም በህይወት እንቆቅልሽ ላይ ነው ያለነው): ስለዚህ ወደ ትክክለኛውን ጉሩ ለትምህርት መቅረብ አለብን: አሁን እንደምናየው:አርጁና ክርሽናን ቀርቦታል:አንደኛ ደረጃ ጉሩ:እርሱም የአንደኛ ደረጃ መምህር ነው: ዋናው ጉሩ ማለት ታላቁ ጌታ አምላካችን ነው:እርሱም የሁሉም ጉሩ ነው:“ፓራም ጉሩ” እንደዚሁም ሁሉ ማንም ሰው ክርሽናን በትክክል የሚወክል ከሆነ:እርሱም ጉሩ ነው ይባላል: ይህም በአራተኛው ምዕራፍ ተገልጿል: “ኤቫም ፓራማፓራ ፕራፕታም ኢማም ራጃርሳዮ ቪዱህ” (ብጊ4 2) ክርሽናም በምሳሌ አስረድቶናል:ይህም ወዴት ልቦናችንን ለመስጠት እንደሚገባን እና: ማንን እንደ ጉሩ መቀበል እንዳለብን ሁሉ በምዕራፎቹ ተገልጿል: ክርሽና እዚህ አለ:(በብሃጋቫድ ጊታ ቅዱስ መጽሃፍ)ስለዚህ ክርሽናን ተቀብላችሁ መከተል አለባችሁ ወይንም የእርሱን ተወካይ ጉሩን መከተል ነው: በዚህም ግዜ የህይወት እንቆቅልሻችሁ ሁሉ ይፈታል: አለበለዛ ግን ይህን መፍታት አዳጋች ነው:ምክንያቱም ጉሩ ብቻ ነው ምን ለእናንተ ጥሩ የሚሆነውን እና መጥፎ የሚሆነው ሊነግራችሁ የሚችለው: እንዲህም ብሎ ጠይቋል:“ያክ ሽሬያህ ስያን ኒሽቺታም ብሩሂ ታት (ብጊ 2 7)”ኒሽቺታም“ ምክር እና መመሪያ ከፈለጋችሁ:”ኒሽቺታም“ ጥርጥር እና ምትሃት የሌለው: ስህተት የሌለው እና ማታለል የማይገኝበት መመሪያ ”ኒሽቺታም“ ይባላል: ይህንንም ለማግኘት የምትችሉት ወይ ከክርሽና ወይ ከተወካዩ ነው: ትክክለኛ የሆነ መረጃ:እንከን ካለው ሰው ወይንም አታላይ ሰው ማግኘት አይቻልም: ይህም ሰው ትክክለኛ ትእዛዝን ሊሰጠን አይችልም: በአሁኒ ግዜ ጉሩ መሆን እንደ ፋሽን ሁኖአል: እነዚህም የዘመኑ ጉሩዎች:የራሳቸውን ግምገማ ይሰጣሉ:”እኔ እንደሚመስለኝ ከሆነ“ ”በእኔ አስተያየት“ ብለው ይናገራሉ: ይህ ጉሩ ሊሆን አይችልም:ጉሩ ማለት የሻስትራን የቅዱስ መጽሃፎችን ጥቅስ እየጠቀስ ማርጃ ማቅረብ አለበት: ”ያህ ሻስትራ ቪድሂም ኡትስርጅያ ቫርታቴ ካማ ካራታሃ“ (ብጊ16 23) ማንም ሰው ከሻስትራ ቅዱስ መፃህፍቶች ጥቅስ እያወጣ መረጃ የማያቀርብ ከሆነ: ”ና ሲዲሂም ሳ አቫፕኖቲ“ እንዲህ አይነት ሰው በማናቸውም ግዜ አገልግሎቱ የተሳካ ሊሆን አይችልም: ”ና ሱክሃም“ በዚህ አለም ላይም ምንም ደስታ ሊያገኝ አይችልም: “ና ፓራም ጋቲም” ወደ ከፍተኛው መንፈሳዊ አልሙን መተላለፍ ይቅርና:ይህ ነው የሻስትራ ትእዛዝ: