AM/Prabhupada 0045 - እውቀት “ግኔያም” ይባላል፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

The Object of Knowledge is Called Jneyam -
Prabhupāda 0045


Lecture on BG 13.1-2 -- Paris, August 10, 1973

ፕራክርቲም ፑሩሻም ቻይቫ ሼትራም ሼትራ ግያም ኤቫቻ ኤታድ ቬዲቱም ኢቻሚ ግያነም ግኔያም ቻ ኬሻቫ (ብጊ 13 1) ልዩ የሰው ልጅ ተሰጥኦ ማለት ይህ ነው፡፡ ይህም የሰው ልጅ ተፈጥሮን የመረዳት አቅሙ ነው፡፡ ይህም ይህንን ትእይንተ ዓለም እና ማን የተፈጥሮ ዓብዩ ተደሳች እንደሆነ ማወቅን ነው፡፡ ሰለዚህም እውቀት የሰው ልጅ በሰፊው ለመነጋገር ይችላል፡፡ የእውቀት ወይንም በሳንስክቲት ቋንቋ "የግኔያም" መድረሻው ምን እንደሆነ ያውቃል፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ ሶስት ነገሮችን እናገኛለን፡፡ "ግኔያም ግያታ እና ግያና" እውቀቱን ለማግኘት የሚጥረው ሰው "ግያታ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ እውቀቱ እራሱ "ግኔያም" ተብሎ ይታወቃል፡፡ እውቀት የመቅሰሙ ስርዓት ደግሞ "ግያን" ወይንም እውቅና ተብሎ ይታወቃል፡፡ እውቀትን በተናገርን ቁጥር ሶስት ነገሮች ይገኛሉ፡፡ እውቀት እውቀት ፈላጊው ሰው እና እውቀቱን ለመቅሰም የሚደረገው ስርዓት ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹም ዓለማዊ ሳይንቲስቶች ለማወቅ ጥረት የሚያደርጉት "ፕራክርቲን" ወይንም ተፈጥሮን ለመረዳት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን "ፑሩሻን" ወይንም የተፈጥሮ ዓብዩ ተደሳች ማን እንደሆነ እውቀቱ የላቸውም፡፡ "ፕራክርቲ" ማለት አስደሳች ማለት ሲሆን "ፑሩሻ" ማለት ደግሞ ተደሳች ማለት ነው፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽና ተደሳች ነው፡፡ እርሱ ዓብዩ ዋነኛ ተደሳች ነው፡፡ ይህም በአርጁና ተመስክሮለታል፡፡ "ፑሩሻም ሻሽቨታም" "አንተ ዋነኛው እና ዓብዩ ተደሳች ነህ፡፡ ፑሩሻም" ሽሪ ክርሽና ተደሳች ሲሆን እኛ የእርሱ ቅንጣፊ ነዋሪ አካላት ወይንም ነፍሳት ደግሞ አስደሳቾች ነን፡፡ ይህችም መላ ተፈጥሮ "ፕራክርቲ" ሽሪ ክርሽና እንዲደሰትባት የተፈጠረች ናት፡፡ ይህ ነው የሽሪ ክርሽና ደረጃ፡፡ እኛም በዚህ ምድር ላይ እራሳችንን እንደ ተደሳች ወይንም እንደ ፑሩሻ አድረገን የምናየው ሁሉ ፑሩሻ ሳንሆን ፕራክርቲ ወይንም አስደሳች ሆነን እንገኛለን፡፡ የእኛ ደረጃ ዓብዩ አማላክን ማሰደሰት ሲሆን በስህተት ግን በዚህ ምድር ላይ እራሳችንን እንደ ፑሩሻ ወይንም ተደሳች አድረገን አቅርበን እንገኛለን፡፡ ይህም ማለት ፕራክርቲ ወይንም በምድር ላይ የሚገኙ ህያው ነፍሳት እራሳቸውን ፑሩሻ ወይንም ተደሳች አድርገው ሲቀርቡ ይህ ዓለማዊ ደረጃ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ ሴት ልጅ እራሷን እንደ ወንድ ልጅ አድርጋ ብታቀርብ ይህ ከተፈጥሮ ውጪ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ነዋሪ ፍጥረታት ሁሉ በተፈጥሮ ዓብዩ አምላክን ማሰደሰት ሲገባቸው ከተፈጥሮ ውጪ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በፊት የተለያየ ምሳሌዎች እንደሰጠነው ጣቶቻችን ጣፋጭ ምግቦችን ሲያነሱ ይገኛሉ ቢሆንም ግን ጣቶቻችን የምግቡ ተደሳቾች አይደሉም ጣቶቻችን ሆድ የተባለውን ትክክለኛውን ተደሳች ሲያገለግሉ ይገኛሉ፡፡ ይህም ጣፋጩን ምግብ በማንሳት እና ወደ አፍ ውስጥ በመክተት ነው፡፡ ይህም ምግብ ወደ ሆድ ወይንም ወደ ዋነኛው ተደሳች ውስጥ ሲገባ ሌሎች ፕራክርቲዎች ሲደሰቱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም የገላዎቻችን ወገኖች ሁሉ በመርካት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ የምግቡ ዋነኛው ተደሳች ሆድ ነው እንጂ ሌሎች የገላችን ወገኖች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በሂቶፓኒሻድ ውስጥ አንድ ታሪክ ተነግሯል፡፡ የኤሶብ አጫጭር ታሪኮችም የተተረጎሙት ከዚሁ የቬዲክ ሂቶፓዴሽ ነው፡፡ በዚህም ስነፅሁፍ ውስጥ ሰለ "ኡዳሬንድሪያናም" ተገልጿል፡፡ "ኡዳራ" ኡዳራ ማለት ሆድ ማለት ሲሆን "ኢንድሪያ" ማለት ደግሞ ሰሜት ማለት ነው፡፡ እዚህም ሰለ "ኡዳሬንድሪያናም" ታሪክ ተገልጿል፡፡ ሰሜቶች ሁሉ በአንድነት በስብሰባ ላይ ለመገኘት ወሰኑ፡፡ እንደዚህም በማለት ስብሰባቸውን ጀመሩ "እኛ ሁላችንም የስራ ሰሜቶች ነን" (ከጎን - ለምንድነው ክፍት የሆነው?) "እኛ ሁላችንም በስራ ላይ ተሰማርተን እንገኛለን" እግርም እንዲህ አለ "እኔ በእርግጥ ሙሉ ቀን ስራመድ እገኛለሁ" እጅም እንዲህ አለ "አዎን እኔም ሙሉ ቀን ገላ ባዘዘኝ ቁጥር ስሰራ እገኛለሁ" "እዚህ ና እና ይህንን ምግብ ብድግ አድርግ" ምግብ ለመስራት እቃዎችን አቀርባለሁ፡፡ ምግብንም ስሰራ እገኛለሁ፡፡ ከዚያም ዓይኖች እንዲህ ይላሉ፡፡ "እኔም ሙሉ ቀን ስመለከት እገኛለሁ" በዚህም በንገድ እያንዳንዱ የገላ ወገኖች ሁሉ አድማ በመምታት ላይ ተገኙ፡፡ እንዲህም ደመደሙ "ሆድ ቁጭ ብሎ በመብላት ለሚደሰተው እኛ ለምንድን ነው ይህንን ያህል በመልፋት ላይ የምንገኘው?" እኛ ሁላችንም በመልፋት ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ሆድ ግን ሁሌ በመመገብ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ሀሳብ የተመረኮዘ አድማ ለመምታት በቁ፡፡ ይህም ልክ እንደ ካፒታሊስቶች እና እንደ ወዝአደሩ አድማ ይመሰላል፡፡ ወዝ አደሩ አድማ በመምታት ላይ ሲገኝ ሰራው ሁሉ ይቆማል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መላው የገላ አካላት አድማ ለመምታት በቁ፡፡ ከሁለት ከሶስት ቀን በኋላም በስብሰባ ላይ እንደገና ሲወያዩ እርስ በእርሳቸው እንደዚህ በማለት ለመወያየት በቁ፡፡ "ለምንድነው አለ ወትሮዋችን በመዳከም ላይ የበቃነው?" "አሁን ለመስራት እንኳን በጣም እያዳገተን ነው፡፡" እግርም እንዲህ አለ፡፡ "በእርግጥ እኔም ድካም እየተሰማኝ ነው" እጅም እንዲሁ በድካም ላይ እንደአለ ተናገረ፡፡ ታድያ የዚህ መነሾው ምንድን ነው? ከዚያም ሆድ እንዲህ አለ "የዚህም መነሾው እኔ ባለመመገቤ ነው" ስለዚህ እናንተ ጠንካራ ለመሆን ከፈለጋችሁ እናንተ እኔን መመገብ አለባችሁ፡፡ አለበለዛ ድካም ይመጣል፡፡ ተደሳች እኔ ነኝ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፡፡ የእናንተ ሀላፊነት ለእኔ ደስታ ምግብ ማቀረብ ነው፡፡ ያ ነው የእናንተ ደረጃ፡፡ እንደዚሁም ለመረዳት በቁ፡፡ "አዎን በእርግጥ እኛ በቀጥታ በምግቡ ለመደሰት አንችልም፡፡ ይህ የሚቻል ነገር አይደለም" ደስታንም ልናገኝ የምንችለው ለሆድ አሳልፈን ካቀረብን ብቻ ነው፡፡ አንድ ጣፋጭ ራስጉላ ጣቶች ቢያነሱ በቀጥታ ሊደሰቱ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ጣቶች ለአፍ አቅርበው ከዚያም ወደ ሆድ ተተላልፎ ሲሄድ ሀይል ሊገኝ ይችላል፡፡ በዚህም ስርዓት ጣቶች ብቻ ሳይሆኑ የሚደሰቱት ዓይኖችም እና ሌሎች የገላችን ወገኖች ሁሉ ሲረኩ እና ሀይልም ሲያገኙ ይታያሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ዋናው ተደሳች አብዩ ሽሪ ክርሽና ሆኖ ይገኛል፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ ብሆክታራም ያግያ ታፓሻም ሳርቫ ሎካ ማሄሽቫራም ሱህርዳ ሳርቫ ብሁታናም ግያትቫ ማም ሻንቲም ርቻቲ (ብጊ 5 29)