AM/Prabhupada 0063 - ታላቅ የምርዳንጋ ከበሮ ተጫዋች መሆን ይገባኛል፡፡
Arrival Lecture -- Dallas, March 3, 1975
እዚህ የሚከናወነውን ሁኔታ እያየሁኝ:በጣም ተደስቻለሁ: ትምህርት ማለት የክርሽና ንቃት ማለት ነው: ይህ ነው ትምህርት ማለት: ክርሽና ታላቁ ጌታችን መሆኑን ብቻ እንኳን ብናውቅ: እርሱ ታላቅ:ነው:እኛም የእርሱ ታዛዥ ነን:ያለን ሃላፊነት እርሱን ማገልገል ብቻ ነው: እነዚህን ሁለት ቃሎች ብቻ ብንረዳ:ህይወታችን የተሳካ ሊሆን ይችላል: ክርሽናን እንዴት ልንሰግድለት እንደሚገባን:እንዴት ለማስደሰት እንደምንችል:ያህል እንኳን ብንማር: እንዴት ልናለብሰው እንደሚገባን:እንዴት እንደምንመግበው ብንማር: እንዴትስ በጌጣ ጌጥ እና በአበባ እንደምናሸበርቀው:እንዴት እንደምንሰግድለት:ብንማር: እንዴት ስሙን እንደምንዘምር:ሁሉ ብናስብ: ያለ ምንም ሌላ ትምህርት ቤት ሳንገባ:በዚህ ህዋ ውስጥ:እንከን የሌለው ሰው ለመሆን ትችላላችሁ: ይህ የክርሽና ንቃት ነው:ኤ ቢ ሲ ዲ ትምህርት አያስፈልገውም: የሚያስፈልገው:የአእምሮአችንን አስተሳሰብ መቀየር ብቻ ነው: እነዚህም ልጆች ከመጀመሪያው ህይወታቸው መማር ከጀመሩ:ህይወታቸው የቀና ይሆናል: እኛም በልጅነታችን እንደዚህ ለመማር: በወላጆቻችን እድል ተሰጥቶናል: ብዙ መንፈሳዊያን ባህታዊዎች አባታችን ቤት ይመጡ ነበር: አባቴ ቫይሽናቫ ነበረ:እኔንም ቫይሽናቫ እንድሆን ይመኝልኝ ነበረ: አባቴም መነፈሳዊ ሰው ቤታችን በመጣ ቁጥር:እንዲህ ብሎ ይጠይቃቸው ነበር: ”እባካችሁ ልጄ ጥሩ የራድሃራኒ አገልጋይ እንዲሆን መርቁልኝ“ ይላቸው ነበር: ፀሎቱም ይህ ብቻ ነበረ:ለሌላ ነገር ፍጹም አልፀለየም: እንዴት ምርዳንጋ (ከበሮ) መጫወት እንደምችልም አስተምሮኝ ነበር: እናቴ ግን ትቃወመው ነበረ: በዚያን ግዜ ሁለት አስተማሪዎች ነበሩኝ:አንዱ ኤ ቢ ሲ ዲ ለማስተማር ሲሆን ሌላው ደግሞ ምርዳንጋ ለማስተማር ነበር: አንዱ አስተማሪ ምርዳንጋ ሲያስተምረኝ:ሌላው ደግሞ እድሉ እስከሚደርስ ይጠብቅ ነበረ: እናቴም እንዲህ ብላ ትቆጣ ነበረ:”ምንድነው ይሄ?ከበሮ ታስተምረዋለህ?“ ይህን ምርዳንጋ (ከበሮ) ተምሮ ልጁ ምን ሊሆን ነው? ምናላልባትም አባቴ ትልቅ የምርዳንጋ ተጫዋች እንድሆን ፈልጎ ይሆናል:(ሣቅ) እንደዚሁም ሁሉ እኔ የአባቴ ብዙ ውለታ ከፋይ ነኝ: ይህንንም የፃፍኩትን የክርሽና መጽሃፍ በእርሱ ስም አሳትሜዋለሁ: ይህንን ነበረ አባቴ የፈለገው:የብሃገቫታ እና የሽሪማድ ብሃገቨታም ሰባኪ እና አስተማሪ እንድሆን በጣም ይፈልግ ነበረ: የምርዳንጋም ተጫዋች እና የራድሃራኒ አገልጋይ እንድሆን ፍላጎቱ ነበረ: እንደዚሁም ሁሉም ወላጆች እንዲህ ማሰብ አለባቸው: አለበላዛ ግን አባት እና እናት ለመሆን መመኘት አያስፈልግም:ይህም የቅዱስ መፃህፍቶች (ሻስትራ) ትእዛዝ ነው: ይህም በሽሪማድ ብሃገቨታም በ5ኛው ምእራፍ ተጠቅሷል: ”ፒታ ና ሳ ስያት ጃናኒ ና ሳ ስያድ ጉሩር ና ሳ ስያት ስቫ ጃኖ ና ሳ ስያት“ እንዲህም ብሎ ውሳኔው ደግሞ:”ና ሞቻዬድ ያህ ሳሙፔታ ምርትዩም“ አንድ መንፈሳዊ መምህር ተማሪውን ለማዳን ካልቻለ: በድንገት ለሚመጣው ለአደገኛው ሞት:ሊያዘጋጀው ካልቻለ:ጉሩ ወይንም መንፈሳዊ መምህር ሊሆን አይገባውም: አንድ ሰው አባትም ወይንም እናት ለመሆን አይገባውም:ይህም ለሞት ሊያዘጋጇቸው ካልቻሉ ነው: እንዲሁም ጓደኛ፣ ዘመድ:ወይንም አባት መሆን አይገባውም: አንዱ ሰው ሌላውን ከዚህ ከሞት አፋፍ ሊድንበት የሚችለውን ትምህርት ካልቻለ:ዝምድናው ፋይዳ የለውም: ይህም ትምህርት በመላው አለም የተፈለገ ነው: ይህም መንገዱ በጣም ቀላል ነው: አንድ ሰው የክርሽናን ንቃት በማዳበር ብቻ:እስርስር ከሚያደርገው:ትውልድ:ሞት: እርጅና እና ህመም:መገላገል ይችላል: