AM/Prabhupada 0092 - ስሜቶቻችንን ሁሉ ክርሽናን ለማስደሰት ማለማመድ አለብን፡፡



Lecture on BG 2.20-25 -- Seattle, October 14, 1968

በዚህ ቁሳዊ ዓለም የሚገኙ ሁሉ በስሜታዊ ደስታ መሯሯጥ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ ይህም በከፍተኛ ፕላኔቶችም ሆነ በ ዝቅተኛ ፕላኔቶችም ጭምር ያለ ነገር ነው፡፡ በእንስሶችም ነገስታት እንደምናየው፡ የስሜታዊ ደስታን ለማርካት ትግሉ የቀጠለ ነው፡፡ የሰው ልጅም እንዲሁ በዚሁ ስሜታዊ ደስታ ተጠምዶ ይታያል፡፡ ይህ የሰው ዘር ምንድን ነው? እኛ ሰው እንደመሆናችን፡የሰለጠንን መሆን ይገባናል፡፡ ለመሆኑ ምን እያደረግን ነው? እንደ እንስሶቹ፡ ሰንበላ፡ ሰንተኛ፡ እና በወሲብ ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ ይህም ሁሉ ውሻም ጭምር የሚያደረገው ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ በዚህ ቁሳዊ ትእይንተ ዓለም ውስጥ፡ ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛም ፕላኔቶች ውስጥም ቢሆን፡ ይህ የስሜታዊን ደስታ ለማርካት ያለው ሩጫ፡ ወሰኑን የያዘ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ የስሜታዊ ደስታ ሩጫ የማይታየው፡ በመንፈሳዊ ዓለም ብቻ ነው፡፡ በዚህም መንፈሳዊ ዓለም የሁሉም አንደበት የክርሽናን ፍላጐት እና ደስታን ለማርካት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ሁሉም የራሱን ስሜቶች ለማርካት ሲሯሯጥ ይታያል፡፡ ይህም የቁሳዊ ዓለም ህግጋት ነው፡፡ ይህም የዓለማዊ ኑሮ ነው፡፡ ስሜታችሁን ለማርካት እስከተሯሯጣችሁ ድረስ፡ በቁሳዊ ኑሮ እንደተጠመዳችሁ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ እራሳችሁን ደግሞ ከዚህ ወጥመድ አውጥታችሁ፡ የክርሽናን ፍላጐት እና ስሜቶች ለማስፋፋት መጣር ስትጀምሩ፡ ይህ መንፈሳዊ ኑሮአችሁ ነው፡፡ ይህም ቀላል የሆነ ልምምድ ነው፡፡ እራሳችንን ለማስደሰት ከመሞከር፡ ይልቅ፡ አብዩ ክርሽናን ማስደሰት ነው፡፡ "ርሺኬና ርሺኬሻ ሴቫናም" (ቼ ቻ 19 170) ይህም ብሀክቲ ይባላል፡፡ ሁላችን ስሜቶች አሉን፡፡ እነዚህም መደሰት የሚሹ ናቸው፡፡ ስሜቶች በደስታ መርካት ይሻሉ፡፡ ያለንም ምርጫ፡ ወይ የእራሳችንን ስሜት ማርካት ወይንም የማንን ስሜት ማርካት እንደሚገባን አናውቅ ይሆናል፡፡ ይህ ውስን የሆነ ነፍስ የክርሽናን ስሜት በማስደሰት ብቻ የእራሱንም ስሜት በቅልጥፍና እንደሚያስደስት አያውቅም፡፡ ምሳሌውም፡ ልክ ፈሳሽ ውሀን ወደ አትክልቱ ስር አስጠግተን እንደማጠጣት ማለት ነው፡፡ ሌላው ምሳሌ ደግሞ፡ እነዚህ ጣቶች የስጋዊ ገላዬ ወገኖች ናቸው፡፡ የምንገበውንም እህል ወደ ሆድ በማቅረብ፡ ጣቶቻችን በቅልጥፍና ለማርካት እንችላለን፡፡ በሁላችንም ዘንድ፡ ይህ ሚስጢር የተዘነጋ ሁኖ ይገኛል፡፡ በዓለማዊ ኑሮ ላይ እያለን፡ የራስ ስሜቶቻችንን በማርካት ደስታ እናገኛለን ብለን እናስባለን፡፡ የክርሽና ንቃት ማለት የራስ ስሜቶቻችንን ለማርካት ጥረት ማድረግ እናቁም ማለት ነው፡፡ የክርሽናንም ስሜቶች ለማርካት ጥረት በማድረግ፡ የራስ ስሜታችሁ ሁሉ በቅልጥፍና ሊረኩ ይችላሉ፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት ሚስጢራዊ እውቀት ነው፡፡ ተቀናቃኝ ወገኖች፡ “ለምን ክርሽናን ለማርካት እገደዳለሁ?” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ “ለምንስ ቀን እና ሌሊት ለክርሽና መድከም ያስፈልገኛል? የካርሚ ኑሮ መኖከር ይሻለኛል፡፡” ብለው ያስባሉ፡፡ ለምሳሌ እናንተን ሌት እና ቀን ለክርሽና ስትደክሙ ሲያዩ፡ “እነዚህ ምን አይነት ሞኞች ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡” “እኛ በጣም አዋቂዎች ነን፡፡ ለእራሳችንም የስሜታዊ ደስታ ቀን እና ሌሊት ስንሰራ እንገኛለን፡፡” ብለው ያስባሉ፡፡ “ለምን እነዚህ ሰዎች ለክርሽና ሁሌ ሲሰሩ የገኛሉ?" ብለው ያስባሉ፡፡ በዓለማዊ ሰዎች እና በመንፈሳዊ ሰዎች መሀከል ያለው ልዩነት ይኅው ነው፡፡ የመንፈሳውያን ትጋት ሁሌ ቀን እና ሌሊት፡ ያለ ማቆም ክርሽናን ለማገለገል ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ኑሮ ነው፡፡ ዓለማዊ ሰዎች ደግሞ የተመሳሰለ ትጋት አላቸው ነገር ግን ጥረታቸው ሁሉ የራሳቸውን ስሜት ለማርካት ነው፡፡ የዓለማዊ እና የመንፈሳዊ ሕይወት ልዩነቱ ይህ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር፡ የሚረዳን፡ ስሜቶቻችንን በመጠቀም እንዴት ክርሽናን ለማስደሰት ጥረት ማድረግ እንዳለብን በማስተማር ነው፡፡ ከዚህም በፊት በሺህ እና በሚልዮን በሚቆጠሩ ትውልዶቻችን፡ የግል ስጋዊ ስሜቶቻችንን ለማርካት ጥረት ስናደርግ ከርመናል፡፡ አሁን በጥሞና የምንጠይቃችሁም፡ ይህንን አንድ ሕይወት የክርሽናን ስሜቶች ለማስደሰት እንድትጥሩ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ ከዚህ በፊት በብዙ ትውልዶቻችን፡ ስሜቶቻችንን ስናስደስት ቆይተናል፡፡ አሁን ይህችን ህይወት እንጠቀምባት፡፡ በዚህ ህይወት፡ ቢያንስ ቢያንስ ይህችኑን ሕይወት፡ ይህን ቅዱስ ተግባር እንሞክር፡፡ በዚህም ተሸናፊዎች ልንሆን አንችልም፡፡ ስሜቶቻችንን ባለማስደሰት እንኳን የማይመቸን ቢሆንም እንኳን፡ የሚያመልጠን ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ የአብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽናን ስሜቶች ግን ለማስደሰት ሞክሩ፡፡ በዚህም መንፈስ ሁሉም ነገር የተስተካከለ ይሆናል፡፡