AM/Prabhupada 0120 - ለመረዳት የማይቻል ሚስጢራዊ ሀይል፡፡



Morning Walk At Cheviot Hills Golf Course -- May 17, 1973, Los Angeles

ፕራብሁፓድ፡ ተርጉመኀዋል ወይስ አልተረጎምከውም? ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ ሊታመን የማይችል ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ አዎን ሊታመን ያማይችል ወይንስ ሚስጢራዊ? ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ ሚስጢራዊ ሀይል፡፡ ፕራብሁፓድ፡ አዎን ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ ሽሪላ ፕራብሁፓዳ ሲያስተምረን የነበረውን እየሰበሰብኩ ነው፡፡ ይህም ስለ ተለያዩ ሊታመኑ የሚያዳግቱት ሀይላት “አቺንትያ ሻክቲ” ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ እዚህም እንደምናየው “አቺንትያ ሻክቲ” እየሰራ ነው፡፡ ፊታችን የምናያቸው ጉም እና ጭጋግ ናቸው፡፡ ጉም እና ጭጋግንም ለማባረር ምንም ሀይል የለንም፡፡ ስለእነዚህም ክስተት ትንተና ለመስጠት እንችል ይሆናል፡፡ ስለሚይዙትም ኬሚካሎች እና ሞለክዩሎች ገለፃ ለመስጠት እንችል ይሆናል፡፡ ቢሆንም ግን ከአካባቢያችን በቀላሉ ልናጠፋቸው የሚያስችል ምንም ሀይል የለንም፡፡ ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ እርግጥ ነው እንዴት ጭጋግ እንደተፈጠረ ሳንይንቲስቶች ለመግለፅ ይችላሉ፡፡ ፕራብሁፓድ፡ አዎን ያንን ለማድረግ ይችላሉ፡፡ እኛም ገለፃ ለመስጠት እንችላለን፡፡ ግን ገለፃው ምን ፋይዳ ይኖረዋል? እንዴት እንደተፈጠረ ለማወቅ ከቻሉ ለምን እንዴት እንደሚያጠፉት እንደሚችሉ ለማወቅ አይሞክሩም? ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ አዎን እንዴት እንደተፈጠረ ለማወቅ እንችላለን፡፡ ፕራብሁፓድ፡ እንዴት እንደተፈጠረ የምታወቅ ከሆነ እንዴት ልታጠፋው እንደምትችል ምርምር አታደርግም? ለምሳሌ ጥንት ጦርነት ይካሄድ በነበረበት ግዜ “ብራህማስትራ” የሚባል ጠላትን የሚያወድም መሳርያ ይጠቀሙ ነበር፡፡ “ብራህማስትራ” ማለትም ከመጠን ያለፈ ሙቀት ወይም እሳት ያለው የጦር መሳርያ ማለት ነው፡፡ በዚህም ግዜ በነበራቸው የሚስጢራዊ ሀይል ሀይሉን ወደ ውሀ ይቀይሩት ነበር፡፡ ከሙቀትም በኋላ ውሀን የመፍጠር ሀይል ነበራቸው፡፡ ስዋሩፕ ዳሞዳር፡ ይህም ልክ እንደ ወተት ይቆጠራል፡፡ ወተት ሲያዩት ነጭ ነው፡፡ ቢሆንም ግን መሰረቱ ውሀ ነው፡፡ ሳይንቲስቶች ወተት በውሀ ውስጥ ፕሮቲን የተከማቸበት ፈሳሽ ነው ብለው ገልፀውታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ይህ ጭጋግ ወይንም ጉም በዓየር ውስጥ የተከማቸ የውሀ አካል ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ አዎን ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ግን እሳትን በአካባቢው ብትፈጥር ይህ ጭጋግ መሰወር ይጀምራል፡፡ ውሀ በእሳት ሊጠፋ ይችላል፡፡ ስለዚህ ውሀን ለማጥፋት እሳትን መፍጠርን ያስፈልገናል፡፡ ይህንንም ለመፍጠር አይቻል ይሆናል፡፡ ፈንጂ ቦምብ ማፈንዳት ግን ትችላለህ፡፡ በዚህም ፈንጂ ቦምብ ሙቀት ይፈጠራል፡፡ ከዚህም ሙቀት በኋላ የአካባቢው ጭጋግ ወይንም ጉም ሊጠፋ ይችላል፡፡ ስለዚህ ሞክረው፡፡ (ሳቅ) ካራንድሀራ፡ እሱማ መሬትን ሊይጠፋ ይችላል፡፡ (ሳቅ) ፕራብሁፓድ፡ ሀሬ ክርሽና፡ ውሀ በእሳት እና በዓየር ወይንም በንፋስ ሊወገድ ይችላል፡፡ ሁሉም ሰው ይህንን ያውቃል፡፡ ይህንን ማድረግስ ትችላለህን? ይህ ሚስጢራዊ ሀይል ነው፡፡ የተፈለገውን ዓይነት ስሜት የማይሰጥ ንድፈ ሀሳብ ላይ ማውራት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ከተፈጥሮ ህግ ውጪ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ስለዚህ ይህ ሚስጢራዊ ሀይል አለው፡፡ እንደዚህም ሁሉ በተፈጥሮ ብዙ ሚስጢራዊ የሆኑ ክስተቶች አሉ፡፡ ይህም “አቺንትያ ሻክቲ” ይባላል። ምንም ማሰብ እንኳን አያስፈልግም፡፡ በተፈጥሮ አመቻቸት ፀሀይ ትወጣለች፡፡ ከዚያም በኋላ ጭጋግ እና ጉሙ ሁሉ በቅጽበት ይጠፋል፡፡ የፀሀይ ሙቀት ትንሽ ከፍ ሲል መላ ጭጋግ እና ጉም ሁሉ ይጠፋል፡፡ “ኒሀራም ኢቫ ብሀስካራሀ” ይህም ምሳሌ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልፆልናል፡፡ “ኒሀራ” ይህም ኒሀራ ተብሎ ተገልጿል፡፡ ይህም “ኒሀራ” “በብሀስካራ” ወይንም በፀሀይ ወዲያውኑ ይጠፋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው ለዓብዩ ጌታ በተፈጥሮ ያለውን የዓብዩ ጌታ የፍቅር አገልግሎት መንፈስን ለመቀስቀስ ይችላል፡፡ በዚህም መንገድ ያለውን ሀጥያት ሁሉ ለመደምሰስ ይችላል፡፡ “ኒሃራም ኢቫ ብሀስካራሀ” እንዲህማ ከሆነ ለምን የፀሀይን ስሪት ወይንም ቅንብር አጥንተህ ፀሀይን አትፈጥርም? ጭጋጉንም ለማጥፋት አንድ ፀሀይ ፍጠርና ወደ ጭጋግ ወይም ጉሙ አቅርበው፡፡ ነገር ግን የሳይንስ ንድፈ ሀሳብን ብቻ በማቅረብ እና ቃላትን አዛብቶ ማቀባበል ፋይዳ የለውም፡፡ ይህም ጥሩ አይደለም፡፡ ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ ሳይንቲስቶች ይህንን ምርምር ይሉታል፡፡ ምርምር ማለት ከዚህ ቀደም ያልታወቀውን ነገር በምርምር ለመረዳት መብቃት ማለት ነው። ፕራብሁፓድ፡ ይህ የእነሱ ምርምር ሞኝነታቸውን እና ቀጣፊነታቸውን እንዲቀበሉ እያደረጋቸው ነው፡፡ ይህ ምርምር የሚያደርጉት ለማን ነው? ማነው እውቀቱን የሌለው? እውቀቱን የሚሻ ከሌለ ምርምሩን አያደርጉትም ነበር፡፡ እውቀቱ እንደሌላቸው ስለሚያውቁ ግን ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም ተቀብለውታል ማለት ነው፡፡ በተፈጥሮ ብዙ ሚስጢራዊ ሀይላት አሉ፡፡ እነዚህም ሚስጢራዊ ሀይላት እንዴት እንደሚቀነባበሩ በቀላሉ የሚታወቅ አይደለም፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ልንገነዘበው የማንችለው ሀይል እንዳለ መረዳት ይገባናል፡፡ ይህም ሚስጢራዊ ሀይል እንዳለ ለመቀበል የምንችልበት መመሪያ እስከሌለን ድረስ ዓብዩ ጌታ ማን እንደሆን ልንረዳ አንችልም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አንድ በሚስጢራዊ ሀይሉ የገነነ ”ባላ ዮጊ“ ዓብዩ ጌታ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ እምነት ለሞኞች እና ለወስላቶች ነው፡፡ ነገር ግን በመንፈሳዊ እውቀት የዳበሩት ዓዋቂዎች ግን ይህንን ሊታመን የማይችል ሚስጢራዊ ሀይል በመመርመር የዓብዩ ጌታን ማንነት ይረዳሉ፡፡ ለምሳሌ እኛም የሽሪ ክርሽናን ዓብይ ጌታነት ተቀብለነዋል፡፡ የሽሪ ራም ዓብይ ጌታነት እና ሊታመን የማይችለው ሀይሉን ተቀብለነዋል፡፡ ይህ ግን በቀላሉ በመታለል አይደለም፡፡ ይህም አንድ ወስላታ ”እኔ የዓብዩ ጌታ ወልድ ነኝ“ በማለት ሊመጣ ይችላል፡፡ ሌላው ሞኝ እና ቀጣፊ ደግሞ በቀላሉ ይቀበለዋል፡፡ ለምሳሌ ”ራማክርሽና“ የተባለውን ሰው ፈጣሪ ነው በማለት የሚቀበሉት ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን በዓብዩ ጌታ ወልድ ውስጥ ሊታመን ወይንም ልንገነዘበው የማንችለው ሀይል እንዳለ ማየት ይገባናል፡፡ ለምሳሌ ሽሪ ክርሽና በልጅነቱ ተራራ በእጁ ለማንሳት በቃ፡፡ ይህ ሊታመን የማይቻል ሚስጢራዊ ሀይል ነው፡፡ ሽሪ ራማቻንድራ ተብሎ የሚታወቀው የዓብዩ ጌታ ወልድ በባህር ላይ ምሰሶ የሌለው ድልድይ ሰራ፡፡ የዚህም ድልድይ ድንጋይ ሁሉ በባህሩ ላይ መንሳፈፍ ጀመሩ፡፡ ሊታመን የማይችል ሚስጢራዊ ሀይል ማለት ይህ ነው፡፡ ይህንንም ሚስጢራዊ ሀይል ለማሳየት ስለማትችል ይህንን ዓይነት ታሪክ ስትሰማ ግን ”እነዚህማ አፈታሪኮች ናቸው“ በማለት ድምደማ ታደርጋለህ፡፡ ይህንንስ ምን ብለው ነው የሚጠሩት? ”ጥንታዊ እምነት ወይንም አፈ ታሪክ“ ታድያ እነዚህ ታላላቅ እና የገነኑ መንፈሳዊ መምህራን እንደ ቫልሚኪ፣ ቭያሳዴቫ የመሳሰሉት መምህራን ወይም አቻርያዎች ሁሉ አፈታሪክን በመፃፍ ግዜያቸውን አባከኑ ማለት ነውን? እነዚህ በጥልቅ የመንፈሳዊ እውቀትን የተማሩ እና የተረዱ መምህራን ናቸው፡፡ እነርሱም ይህንን ሚስጢራዊ ሀይል እንደ ጥንታዊ እምነት ወይም አፈታሪክ አድርገው በቀላሉ አልተረጐሙትም፡፡ ፍፁም እውነት እንደመሆኑ ግን ተቀብለው ይህንን በጥልቅ ተተንትኖ የተፃፈውን የዓብዩ ጌታን እውቀት ለሰው ልጅ አቅረበዋል፡፡ አንድ ግዜ ታላቅ የጫካ እሳት ይነድ ነበር፡፡ በዚህ ጫካ ውስጥ የነበሩት የሽሪ ክርሽና እረኛ ጓደኞች ሁሉ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ነበሩ፡፡ በዚህም ግዜ ራሳቸውን ለማዳን አቅም ስላልነበራቸው ወደ ሽሪ ክርሽና ለጠለላ ማምራት ጀመሩ፡፡ “ክርሽና ምን ማድረግ ይሻለናል?" በዚህም ግዜም ሽሪ ክርሽና ምንም ችግር እንደሌለ አረጋግጦላቸው መላ እሳቱን በመምጠጥ ለማጥፋት በቃ፡፡ ይህ የዓብዩ ጌታ ሚስጢራዊ ሀይል ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ ይህ ዓይነት ሚስጢራዊ ሀይል አለው፡፡ ”አይሽቫርያስያ ሳማግራስያ ቪርያስያ ያሻሳህ ሽሪያህ“ (ቪሽኑ ፑራና 6 5 47)ዓብዩ ጌታ እነዚህን የመሰሉ ድሎቶች ሙሉ በሙሉ የያዘ ነው፡፡ እኛም እንደዚሁ የሚስጢራዊ ሀይል ይዘን እንገኛለን፡፡ ነገር ግን የእኛ ሀይል በመጠኑ በጣም ያነሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ከምንገምተው ነገሮች በላይ በገላችን ውስጥ ብዙ ነገር እየተከናወነ ነው፡፡ መላውን ተረድተን ግን ለሌሎች ለማስረዳት አቅም የለንም፡፡ ሌላ ምሳሌ ለመስጠትም በጣቶቼ ላይ የሚገኙት ጥፍሮች በተመሳሳይ መንገድ ሲያድጉ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን በህመም ሊበላሽ ቢችሉም ጥፍሮቼ ማደጋቸውን አያቆሙም፡፡ ምን ዓይነት የተፈጥሮ ቅንብር እንዳላቸው ግን ለእኔ ሚስጢራዊ ነው፡፡ ጥፍሩ ግን ግዜው እና አስተዳደጉን አሳምሮ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ሁሉ ከገላ የሚመነጭ የዓብዩ ጌታ ሚስጢራዊ ሀይል ነው፡፡ የዓብዩ ጌታ ሚስጢራዊ ሀይል በዚህም መንገድ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ይህም ሀይል ለእኔም ሆነ ለህክምና ዶክተሮችም ሁሉ ሚስጢር ሁኖ ይገኛል፡፡ ይህም ለሁሉም ሰው ነው፡፡ ማንም ሰው ቢሆን ይህንን ተንትኖ ለማስረዳት ያዳግተዋል፡፡