AM/Prabhupada 0126 - ይህም ለመንፈሳዊ አባቴ ደስታ ብዬ የማደርገው ነው፡፡



Lecture on BG 4.18 -- Delhi, November 3, 1973

ሴት ድቮቲ:እንዲህ ብለህ ነበር :“አንድ ሰራ ለክርሽና ስንሰራ” “ይህ ስራ ክራሽናን እንደሚያስደስት መሞከር አለበት ብለህናል:ይህ ሙከራ ምንድን?”

ፕራብሁፓድ:የመንፈሳዊ አባት ከተደሰተ:ክርሽና ተደሰተ ማለት ነው:ይህንንም በቀን በቀን ትዘምራላችሁ: “ያስያ ፕራሳዶ ብሃጋቫት ፕራሳዶ ያስያፕራሳዳ ና ጋቲ ኩቶ ፒ” የመንፈሳዊ አባት ከተደሰተ:ክርሽናም ተደሰተ ማለት ነው:ይህ ነው ሙከራው: እርሱም ካልተደሰተ ግን:ሌላ ምርጫ የለውም:ይህም ለመረዳት አያዳግትም: ለምሳሌ በቢሮ ውስጥ የሚሰራ ሰው:ሃላፊው ዋና ክሌርኩ:ወይንም ሱፐር ኢንቴንደንቱ ወይንም የክፍሉ ሃላፊ ነው: ሁሉም እየሰሩ:ሱፐር ኢንቴንደንቱ ከተደሰተ: ወይንም ዋና ክሌርኩ ከተደሰተ:አስተዳዳሪ ዳይሬክተሩም ይደሰታል ማለት ነው: ይህም ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም:ለእናንተም ሃላፊያችሁ:የክርሽና ተወካይ መደሰት አለበት: “ያስያ ፕራሳዳ ብሃጋቫት ፕራሳዶ ያስያ” ስለዚህ በመንፈሳዊ አባት መመራት ያሰፈልጋል: ክርሽና እንደ መንፈሳዊ አባት መመሪያ ሁኖ ይመጣል:ይህም በቼይታንያ ቻሪታምሪታ ተጠቅሷል: “ጉሩ ክርሽና ክሪፓያ:ጉሩ ክርሽና ክሪፓያ” ስለዚህ ”ጉሩ ክርፓ“ የጉሩ ምርቃት የክርሽና ምርቃት ነው: እንደዚሁም ሁሉ ሁለቱም በደስታ ከረኩ:መንገዳችንም ግልጽ ነው ማለት ነው: “ጉሩ ክርሽና ክርፓያ ፓያ ብሃክቲ ላታ ቢጅ” (ቼቻ ማድህያ 19 151) እንዲህም ከሆነ የክርሽና አገልግሎታችን የተሳካ ይሆናል: ይህንን ጥቅስ በ “ጉሩ ቫስታካ” መዝሙር አላስተዋላችሁትምን? “ያስያ ፕራሳዳ ብሃጋቫት ፕራሳዶ ያስያፕራሳዳን ና ጋቲህ ኩቶ ፒ” ልክ እንደዚህ እንቅስቃሴያችን:ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው:የእኔን መንፈሳዊ አባት ለማስደሰት ነው: እርሱም እና ቼይታንያ ማሃፕራብሁ:ይህ እንቅስቃሴ በአለም ላይ እንዲስፋፋ ተመኝተው ነበር: ስለዚህም ብዙዎቹን የእኔን መንፈሳዊ ወንድሞች:አዘዛቸው እና ትምህርቱን እንዲያስፋፉ ተመኘ: አንዳንዶቹንም የመንፈስ ወንድሞቼን ወደ ውጭ አገር እንዲያስተምሩ ተልከው ነበር: ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ስለአልተሳካላቸው:ተመልሰው ወደ አገር ተመልሰው መጡ: ስለዚህም እኔ ”በዚህ በእርጅና ግዜዬም ልሞክር“ ብዬ አሰብኩኝ የነበረኝም ፍላጎት:የመንፈሳዊ አባቴን:ምኞት ለሟሟላት ብቻ ነበር: እናንተም እያገዛችሁኝ ነው:አሁን ታድያ ውጤቱ እያማረልን ነው: ይህም “ያስያ ፕራሳዳ ብሃጋቫት ፕራሳዳ” ነው: በትጋት እና በሙሉ ልቦና:በመንፈሳዊ አባታችን ተመርተን: አገልግሎታችንን ከሰጠን: ይህ የክርሽናን መደሰት ያመጣል:ክርሽናም ወደ ፊት እንድንገፋ ይረዳናል: