AM/Prabhupada 0144 - ይህ ማያ ተብሎ ይታወቃል፡፡
Sri Isopanisad, Mantra 2-4 -- Los Angeles, May 6, 1970
”ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉናይህ ካርማኒ ሳርቫሻሃ አሃንካራ ቪሙድሃትማ ካርታሃም ኢቲ ማንያቴ“ (ብጊ 3 27)
ለድቮቲዎች ክርሽና እራሱ ሃላፊነት የወስዳል: ለተራው ነፍሳቶች ግን ማያ ሃላፊነቱን ወስዳለች: ማያ የክርሽና ወኪል ናት: ልክ ጥሩ የአገር ዜጎች በመንግስት ጥሩ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ሁሉ: ወሮበሎቹ ደግሞ በመንግስት ወኪል በእስርቤቱ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል: በወሮበሎች ተቆጣጣሪዎች አስተዳደር:እነርሱም በእንክብካቤ ላይ ይገኛሉ: በእስር ቤትም እስረኞችን በደንብ ይንከባከቧቸዋል: ምግብ ይቀርብላቸዋል:ከታመሙም ይታከማሉ: ሁሉም አይነት እንክብካቤ አለ:ነገር ግን በቅጣት ላይ እያሉ ነው: እንደዚሁም በዚህ አለም ላይ:እንክብካቤ አለ:ነገር ግን በቅጣትም ላይ እያለን ነው: ይህን ብታደርጉ:ጥፊ ይሰጣችኋል:ይህን ብታደርጉ ደግሞ:ካልቾ ይሰጣችኋል: ይህን ብታደርጉ ደግሞ ይህ ይገጥማችኋል:ይህ እየተካሄደ ነው:ይህም የሶስቱ አይነት መከራዎች ይባላሉ: ግን በማያ ምትሃት:ይህ ጥፊ:ካልቾ እና አመድ መሆን:ጥሩ ነገር ይመስለናል: አያችሁ? ይህ ማያ ይባላል: ነገር ግን ወደ ክርሽና ንቃት ስትመለሱ ደግሞ ክርሽና ሃላፊነቱን ይወስዳል: ”አሃም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሻዪስያሚ ማ ሹቻሃ“ (ብጊ 18 66) ለክርሽና ልቦናችሁን እንደሰጣችሁ:ክርሽና ”እኔ እንከባከባችኋለሁ” ይላል: ከሃጥያታዊ ቅጣት ሁሉ አድናችኋለሁ ይላል: በህይወታችን ብዙ የተከመረ ሀጥያቶች አሉን:ይህም ከዚህ አለም ብዙ ትውልዶች የተከማቸ ነው: ነገር ግን ለክርሽና ሙሉ ልቦናችሁን እንደሰጣችሁት:ክርሽና ሃላፊነቱን ይወስዳል: እርሱም እንዴት ሃጥያታችን መስተካከል እንደሚገባው ያስተዳድረዋል: “አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ማ ሹቻሃ” ክርሽና እንዲህ አለ “አትጠራጠር” እንዲህ ከአሰባችሁ:“እኔ ብዙ ሃጥያት ሰርቻለሁ:እንዴት ክርሽና ሊያድነኝ ይችላል?” አይደለም:“ክርሽና አብይ ሃይል ያለው ነው” ሊያድናችሁ ይችላል: የእናንተ ሃላፊነት ለእርሱ ልቦናችሁን መስጠት ብቻ ነው:ያለ ምንም ጥርጥር: ህይወታችሁን ለእርሱ ማገልገያ አድርጉ:እንደዚህም ልትድኑ ትችላላችሁ: