AM/Prabhupada 0217 - የዴቫሁቲ ደረጃ ልክ እንደ ፍጹም ጥሩ የሆነች ሴት ነው፡፡
Lecture on SB 3.28.1 -- Honolulu, June 1, 1975
ይህችም የማኑ ልጅ የሆነችው ልእልት ካራዳማ ሙኒ የተባለውን ባህታዊ ማገልገል ጀመረች፡፡ በሚቀመጥበትም የዮጋ አሽራም ወይንም ጎጆ ምንም ደህና ምግብ ወይንም የልእልቷ አገልጋዮች ሆነ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ልእልቷ በጣም ጎባጣ እና ቀጫጫ እየሆነች መጣች፡፡ ቀድሞ ግን በጣም ቆንጆ የሆነች የንጉስ ልጃገረድ ነበረች፡፡ ባህታዊው ካርዳማ ሙኒም እንዲህ በማለት ማሰብ ጀመረ፡፡ ”አባትዋ እርሷን ለእኔ ሰጥቶኝ ነበረ፡፡ ነገር ግን ጤንነትዋ እና ቁንጅናዋ እየወደቀ መጥቷል፡፡“ “ባል እንደመሆኔም ሁሉ ለእርስዋ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ፡፡” ባለውም የባህታዊ የዮጋ ሀይል አንድ ትልቅ እንደ አይሮፕላን የሚበር ከተማ ፈጠረ፡፡ ይህም የዮጋ ስርዓት ስልቱ ያቀረበለት ነው እንጂ 747 ገንብቶ አይደለም፡፡ በዚህም ከተማ ውስጥ ታላቅ ኩሬ የአበባ ስፍራ እንዲሁም የልእልት ታዛዥ አገልጋዮች ሁሉ ነበሩ፡፡ ታላላቅ ቤተ መንግስቶች ሁሉ ሲኖሩት ይህ ሁሉ ግን ተንቀሳቃሽ እና በሰማይ የሚበር ነበረ፡፡ በዚህም ፍጥረት እየተዘዋወረች የተለያዩትን ፕላኔቶች እንድታያቸው አበቃት፡፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም አራተኛውም ምዕራፍ ይህ ሁሉ ተገልጾ ታገኙታላችሁ፡፡ በዚህም መንገድ እንደ ዮጊ በመሆኑ በሁሉም ደረጃ ሊያሰደስታት በቃ፡፡ ከዚያም ልጆችን ለመያዝ ፍላጎት አደረባት፡፡ በዚህም ምክንያት ካርዳማ ሙኒ ዘጠኝ ልጃገረዶች እና አንድ ወንድ ልጅ ሊሰጣት በቃ፡፡ ይህንንም ቃል የገባላትም ልጆች ከሰጣት በኋላ ጥሏት እንደሚሄድ በመስማማታቸው ነው፡፡ ለዘለዓለም ከአንቺ ጋር ለመኖር አልችልም ብሎ ገልጾላት ነበር፡፡ እርስዋም ተስማምታ ነበር፡፡ ከእነዚህም ልጆችዋ መሀከል አንዱ ካፒላዴቭ ተብሎ የሚታወቀው ወንዱ ልጅዋ ነበረ፡፡ እርሱም ከአደገ በኃላ ለእናቱ እንዲህ አላት፡፡ ”እናቴ ሆይ አባቴ ቤቱን ለቅቆ እንደመሄዱ እኔም ቤት ለቅቄ መሄድ ይገባኛል።“ አላት፡፡ ከእኔም ትእዛዝ ወይም ምክር ለመቀበል የምትፈልጊ ከሆነ መውሰድ ትችያለሽ፡፡ ከዚያ በኃላ ግን መሄድ ይገባኛል፡፡ ብሎ አጫወታት፡፡ ከዚህም በኋላ ከመሄዱም በፊት ለእናቱ ምክርን መስጠት ጀመረ፡፡ ይህችም ዴቫሁቲ የነበረችበት ደረጃ ፍጹም ጥሩ የሆነ ነበር፡፡ አባቷ በጣም ጥሩ ነበረ፡፡ ባሏም በጣም ጥሩ የሆነ ነበረ፡፡ ልጇም ደግሞ በጣም የላቀ ነበረ፡፡ የሴት ልጅ በሕይወቷ ሶስት ደረጃ አላት፡፡ ወንድ ልጅ ደግሞ አስር ደረጃዎች አሉት፡፡ እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ማለት በልጅነትዋ የሴት ልጅ በአባትዋ እንክብካቤ ስር መኖር ይገባታል፡፡ ልክ እንደ ልእልት ዴቫሁቲ፡፡ ከአደገች በኃላ ለአባትዋ ይህንን አዋቂ ዮጊ ወይንም ባህታዊ ላገባው እፈልጋለሁ ብላ ጠየቀችው፡፡ አባትየውም ልጁን ለባህታዊው አቀረበ፡፡ ትዳር እስክትይዝ ግዜ ግን በአባትዋ እንክብካቤ ስር ሆና ትኖር ነበረ፡፡ ትዳር ስትይዝ ደግሞ በዮጊው ባልዋ እንክብካቤ ስር ሆና መኖር ጀመረች፡፡ የንጉስ ልጃገረድ ልእልት እንደመሆንዋም ከባልዋ ዘንድ ሆና ብዙ ችግሮችን አሳልፋለች፡፡ ዮጊው ባልዋ ትችሽ ግጆ ነበረችው ምግብ አልነበረውም መጠለያ አልነበረውም፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ መከራ ሊደርስባት ቻለ፡፡ አንድ ቀንም ቢሆን “እኔ የንጉስ ልጅ ነኝ ያደኩትም ብዙ ሀብት በተሞላበት ማዕረግ ነው፡፡” ብላ አታውቅም፡፡ “አሁን ቤት የማይሰጠኝ ጥሩ ምግብ የማይሰጠኝ ባል አግብቻለሁ እና ይህንን ዓይነቱን ባል መፍታት ይገባኛል” ብላ አታውቅም፡፡ ይህ በሀሳብዋ ውስጥ በፍጹም ገብቶ አያውቅም፡፡ የእርስዋ አመለካከት እንዲህ አልነበረም፡፡ “ባለቤቴ ምንም ዓይነት ሰው ቢሆንም ይህንን የመሰለ አዋቂ ሰው እንደ ባለቤቴ አድርጌ ሰለተቀበልኩት” እንደ ፍላጎቱ መኖር ይገባኛል፡፡ ምንም ዓይነት ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም ግድ አይሰጠኝም“ ብላ ታስብ ነበረ፡፡ ይህ የበጎ ሴት ሀላፊነት ነው፡፡ ይህም በቬዲክ ትእዛዝ የተመሰረተ ነው፡፡ በአሁኑ ገዜ ግን በትዳር ላይ tትንሽ ችግር ሲፈጠር ሀሳቡ ሁል ወደ መፋታት ይሄዳል፡፡ ሌላ ባል ልፈልግ አላለችም፡፡ ከባልዋ ጋር ፀንታ ቆየች፡፡ ከዚያም ደስ የሚያሰኘውን ካፒላ አብዩ አምላክን እንደ ልጅዋ ሆኖ ተወልዶ አገኘችው፡፡ እነዚህ ሶስቱ ደረጃዎች ናቸው፡፡ ሴት ልጅ ምኞት እንዲኖራት ያሰፈልጋል፡፡ በተፈጥሮ ባላት ካርማ በጥሩ አባት ቤት ተወልዳ ልትኖር ትችላለች፡፡ ከዚያም ተገቢ በሆነ ባል ስር እየኖረች ካፒላን የመሰለ ጥሩ ልጅ ለመውለድ ትበቃለች፡፡