AM/Prabhupada 0268 - ንፁህ የክርሽና ትሁት አገልጋይ ሳይሆኑ ስለ ክርሽና ጠልቆ መረዳት አይቻልም፡፡

From Vanipedia


Nobody can Understand Krishna Without Becoming a Pure Devotee of Krishna - Prabhupada 0268


Lecture on BG 2.10 -- London, August 16, 1973

ስለዚህ አስቸጋሪ ነው: በልቦናው ንጹህ የሆነ የክርሽና አገልጋይ ካልሆነ በስተቀር: ማንም ሰው ክርሽናን ሊረዳው አይችልም:: ምክንያቱ ክርሽና እንዲህ ብሏል: "ብሃክትያምም አብሂጃናቲ ያቫን ያስ ቻስሚ ታትቫታሃ" (ብጊ 18 55) "ታትቫታሃ" በእውነት: "ታትቫታሃ" ማለት እውነት ማለት ነው:: አንድ ሰው ክርሽናን እንደ አለ ለመረዳት ከፈለገ: ክርሽናን በጥሞና የማገለገል ስርአትን መከተል አለበት "ብሃካታ" "ብሃክቲ" "ርሺኬና ርሺኬሻ ሴቫናም ብሃክቲር ኡችያቴ" (ቼቻ ማድህያ 19 170) አንድ ሰው የርሺኬሻ: ወይንም የስሜቶች ሁሉ : ጌታ (አምላክ) አገልጋይ ሁኖ ከተመደበ: ስሜቶቻችን ሁሉ: ጌታን ወይንም ህርሺኬሻን: (የስሜቶች ሁሉ ጌታ): በማገለገል ላይ ካሳተፍነው: እራሳችህም የስሜቶቻችን ሁሉ ጌታ ለመሆን እንበቃለን:: በዚህም መንገድ ስሜቶቻችን ሁሉ: ህርሺኬሻን በማገልገል ከተሳተፉ: በሌላ ስሜታዊ ስርአቶች ላይ አይሰማሩም: ይህም ጌታን በማገልገል ስለተቆለፉ ነው: "ሳቫይ ማናሃ ክርሽና ፓዳራቪንዳዮህ ((ሽብ 9 4 18) ይህ ነው በጥሞና የቀረበ መንፈሳዊ አገለግሎት ሂደት: የስሜታዊ ፍላጎቶች ሁሉ ጌታ መሆን ከፈለጋችሁ "ጎስዋሚ" "ስዋሚ" ስሜታችሁን ሁሉ ለህርሺኬች መስጠት ወይንም አምላክን ለማገለገል መስዋእት ማድረግ አለባችሁ:: ይህ ብቻ ነው መንገዱ: አለበለዛ ግን የማይቻል ይሆናል:: ;ልክ ስሜታችሁን ደግሞ: ለስሜት ጌታችን: ደስታ ማዋል: እንደሚገባችሁ ስትዘነጉ ደግሞ: ወዲያውኑ: ማያ ትቀርባችኋለች: "ና ወዲህ እባክህ" ትላችኋለች: ይህ ነው ፈለጉ:: "ክርሽና ብሁሊያ ጂቫ ብሆጋ ቫንቻ ካሬ ፓሳቴ ማያ ታሬ ጃፓቲያ ድሀሬ" ለትንሽ ግዜ እንኳን ክርሽናን ብንዘነጋ ማያ በአጠገባችን ትሆናለች፡፡ "ውድ ጓደኛዬ ሆይ በደእዚህ ተጠጋ" ሰለዚህ በጣም መጠንቀቅ ይጠበቅብናል፡፡ ክርሽናን ለጥቂት ግዜ እንኳን መዘንጋት የለብንም፡፡ ሰለዚህ የመዘመሪያ ፕሮግራም አለን "ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሀሬ ሀሬ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ" ሁልግዜ ክርሽናን አስታውስ፡፡ በዚህም ስርዓት ማያ ልትቀርብህ አትችልም፡፡ "ማም ኤቫዬ ፕራፓድያንቴ ማያም ኤታን ታራንቲ" ማያ ልትነካችሁ አትችልም፡፡ ልክ እንደ ሀሪ ዳስ ታኩር፡፡ እርሱም በህርሺኬሽ አገልግሎት ተሰማርቶ ነበር፡፡ ማያ ደግሞ በመላ ሀይሏ ልታሳስተው መጥታ ነበር፡፡ ነገር ግን በለሸነፍ በቃች፡፡ ሀሪ ዳስ ታኩር ለመሸነፍ አልበቃም፡፡