AM/Prabhupada 0274 - እኛ ያለንበት በብራህማ ሳምፐረዳያ የድቁና ስርዓት ውስጥ ነው፡፡
Lecture on BG 2.7 -- London, August 7, 1973
ሰለዚህ አብዩን የመላእክት ጌታ ክርሽናን ወይም የእርሱን ተወካይ መቅረብ ይኖርብናል፡፡ ሌሎቹ ሁሉ ተንኮለኞች እና ሞኝነት የተሞላባቸው ናቸው፡፡ ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) ወይንም የክርሽናን ተወካይ ያልሆነውን ሰው ከቀረባችሁ ተንኮለኛ ሰው እና አሳሳች ሰው ቀረባችሁ ማለት ነው፡፡ በዚህስ ሰው እንዴት አድርጋችሁ በክርሽና እውቀት ለመንቃት ትችላላችሁ? ክርሽናን በቀጥታ ወይንም ተወካዮቹን መቅረብ ይገባችኋል፡፡ “ታድ ቪግናርትሀም ሳ ጉሩም ኤቫ አብሂጋቼት (ሙኡ 1 2 12) ታድያ ጉሩ የምንለው ማነው? ሳሚት ፓኒሀ ሽሮትሪያም ብራህማ ኒስትሀም ጉሩ ማለት በክርሽና ንቃት ሙሉ በሙሉ የነቃ ማለት ነው፡፡ ”ብራህማ ኒስትሀም“ ”ሽሮትሪያም“ ማለት ደግሞ አንድ የሰማ ሰው ማለት ነው። ይህም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ካለ ባለስልጣን በ”ሽሮትሪያም ፓትሀ“ በማዳመጥ እውቀትን የተቀበለ ማለት ነው ኤቫም ፓራምፓራ ፕራፕታም ኢማም ራጃርሻዮ ቪድሁህ (ብጊ፡4 2) እዚህም ከአርጁና መማር ያስፈልገናል፡፡ እርሱም በጭንቀት ላይ እያለ ወይንም ትክክለኛ ሀላፊነታችንን ስንዘነጋ ግር የሚል ደረጃ ላይ እንወድቃለን በዚህም ግዜ ሀላፊነታችን አርጁና እንደ አደረገው ክርሽናን መቅረብ ነው፡፡ ለምሳሌ ክርሽና የት ነው ብላችሁም ብትጠይቁ ክርሽና በአጠገባችሁ ላይታይ ይችላል ነገር ግን የክርሽና ተወካይ በአጠገባችሁ ይኖራል፡፡ ይህንንም የክርሽና ተወካይ መቅረብ ይገባችኋል፡፡ ይህ የቬዲክ መመሪያ ነው፡፡ ”ታድ ቪግናናርትሀም ሳ ጉሩም ኤቫ አብሂጋቼት“ (ምኡ፡ 1 2 12) አንድ ሰው ጉሩን መቅረብ ይገባዋል፡፡ ጉሩ ማለት ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ክርሽና ነው፡፡ ቴኔ ብራህማ ህርዳ ያ አዲ ካቫዬ ሙህያንቲ ያት ሱራያሀ (ሽብ፡ 1 1 1) ጃናማድያስያ ያታሀ አንቫያት ኢታራታሽ ቻ አርትሄሹ አብሂግናህ ስቫራት ጉሩን መቅረብ አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ ጌታ ብራህማን እንውሰድ ብራህማ በዚህ ትእይንተ ዓለም ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ የተፈጠረ በመሆኑ እንደ ጉሩ እንቀበለዋለን፡፡ እውቀትንም ሰጥቷል.....እኛም ከብራህማ ሳምፕራዳያ የድቁና ስርዓት ወገን እንገኛለን አራት አይነት የቫይሽናቫ የድቁና ስርዓቶች ወይንም ሳምፕራዳያዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ብራህማ ሳምፕራዳያ ሽሪ ሳምፕራዳያ ሩድራ ሳምፕራዳያ እና ኩማራ ሳምፕራዳያ ይባላሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ማሀጃናዎች (ታላላቅ መምህራን) ይባላሉ፡፡ “ማሃጃኖ ዬና ጋታሀ ሳ ፓንታሀ” (ቼቻ፡ ማድህያ 17 186) በእነዚህም በመሀጃናዎች መስመር የሚመጣውን መመሪያም መቀበል ይገባናል፡፡ ሰለዚህ ብራህማ ማሀጃን ይባላል፡፡ የብራህማንም ስዕል ቬዳ በእጁ ውስጥ ሆኖ ልታዩት ትችላላችሁ፡፡ እርሱም የመጀመሪያው ጉሩ እና የመጀመሪያውንም የቬዲክ ትእዛዝ የሰጠው እርሱ ነው፡፡ ታድያ ይህንንስ የቬዲክ እውቀት ያመጣው ከየት ነው? ሰለዚህ የቬዲክ እውቀት "አፖሩሴያ“ ይባላል፡፡ ይህም ሰው ሰራሽ ሳይሆን በአብዩ አምላክ የተፈጠረ ነው ማለት ነው፡፡ ድሀርማም ቱ ሳክሳድ ብሀገቫት ፕራኒታም (ሽብ፡6 3 19) ታድያ አብዩ አምላክስ ለብራህማ እንዴት አድርጎ ይህንን እውቀት ሰጠው? ”ቴኔ ብራህማ ህርዳያ“ ብራህማ፡ ብራህማ ማለት የቬዲክ እውቀት ማለት ነው፡፡ ”ሻብዳ ብራህማ“ ቴኔ ማለት ደግሞ ጌታ ይህንን የቬዲክ እውቀት ከህርዳ ወይንም ከልቡ አስተላለፈ ማለት ነው፡፡ ቴሻም ሳታታ ዩክታናም ብሀጃታም ፕርቲ ፑርቫካም (ብጊ፡10 10) ብራህማ ለመጀመሪያ ግዜ እንደተፈጠረ በጭንቀት ላይ ነበረ፡፡ ”ሀላፊነቴ ምንድነው፡፡ ሁሉም ነገር ጨለማ ይመስላል፡፡“ ከዚህም በኋላ ወደ ጥልቅ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡ ከዚያም ክርሽና እውቀቱን ሰጠው፡፡ ”ሀላፊነትህ ይህ ነው፡፡ ማድረግ የሚገባህ ይህን ነው፡፡“ ”ቴኔ ብራህማ ህርዳ ያ አዲ ካቫዬ“ አዲ ካቫዬ (ሽብ፡ 1 1 1) ብራህማ አዲ ካቫዬ ተብሎ ይታወቃል፡፡ በዚህም መንገድ ዋነኛው ጉሩ ክርሽና መሆኑን እንረዳለን፡፡ እዚህም እንደዚሁ....ክርሽና በብሀገቨድ ጊታ ምክሩን ሲሰጥ እናየዋለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተንኮለኛ እና ሞኞች ክርሽናን እንደ ጉሩ አይቀበሉትም፡፡ ነገር ግን ወደ ተንኮለኛ ሞኝ አታላዮች እና ሀጥያተኞች በመሄድ ጉሩ ናቸው ብለው ተቀብለዋቸው እናያቸዋለን፡፡ እነዚህስ እንዴት ጉሩ ሊሆኑ ይችላሉ?