AM/Prabhupada 0299 - ሳንያሲ ወይንም መነኩሴ ሰው ሚስቱን ማየት አይችልም፡፡
Lecture -- Seattle, October 4, 1968
ታማላ ክርሽና: ፕራብሁፓድ፡ ጌታ ቼይታንያ ሳንያስ (መነኩሴነት) ከወሰደ በኋላ በጌታ ቼታንያ ትምህርቶች መፅሀፍ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "እናቱን አገኘ" የእኔ አስተሳሰብ ግን ሳንያሲ (መነኩሴ) ይህንን ማድረግ አይችልም ነበረ፡፡ ፕራብሁፓድ፡ አይደለም፡፡ ሳንያሲ ሚስቱን ማግኘት አይገባውም፡፡ ሳይያሲ ቤቱ ሂዶ ሚስቱን ማግኘት አይገባውም፡፡ ይህ የተከለከለ ነው፡፡ ሌሎችን ግን ማግኘት ይችላል፡፡ ነገር ግን.... ቼታንያ መሀፕራብሁ ወደ ቅድሞ ቤቱ አልሄደም፡፡ እቅድ ተደርጎ ግን አድቨይታ ብራብሁ እናቱ ጌታ ቼታንያን እንድታየው አመጣት፡፡ ቼታንያ መሀ ብራብሁ ሳንያስ ከወሰደ በኋላ በሽሪ ክርሽና ናፍቆት ተመስጦ እንደ እብድ ሆኖ ነበረ፡፡ የጋንጀስ ወንዝ ምን እንደሆነም በመዘንጋት ወደ ጋንጀስ ዳርቻ ይሄድ ነበረ፡፡ ያስብ የነበረውም "ይህ የያሙና ወንዝ ነው፡፡ ወንዙንም በመከተል ወደ ቭርንዳቫንም እየሄድኩ ነው" በማለት ያስብ እና ይጓዝ ነበረ፡፡ ስለዚህም ኒትያናንዳ ፕራብሁ አንድ ሰው ከእርሱ ጋር እንዲሄድ ይልከው ነበረ፡፡ "ጌታ ቼታንያን እየተከተልኩ ነው፡፡ እባክህ አድቫይታ አንድ ጀልባ ወደ ወንዙ ዳርቻ እንዲልክልኝ ንገረው፡፡" ይህም ወደ ቤቱ ሊወስደው እንዲችል ነበረ፡፡ በዚህም መንገድ ቼታንያ መሀፕራብሁ በተሰመጠ ደስታ ውስጥ ነበረ፡፡ ከዚያም በድንገት አድቫይታ ፕራብሁን ጀልባ ይዞ ሲጠብቀው አየው፡፡ ከዚያም እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡፡ “አድቫይታ እዚህ ምን እያደረግህ ነው? ይህቺ የጃሙና ወንዝ ናት፡፡” አድቨይታም እንዲህ ብሎ ይመልስለት ነበረ፡፡ “እውነት ነው ጌታዬ ሆይ፡፡ ያለህበት ቦታ ሁሉ ጃሙና ትገኛለች፡፡ ሰለዚህ አሁን ወደ ቤትህ ተመለስ፡፡” በዚህም እቅድ ወደ አድቨይታ ቤት ይመለስ ነበረ፡፡ ከዚያም ቤት እንደደረሰ እንዲህ ይል ነበረ፡፡ “አሳሳትከኝ፡፡ ያመጣኅኝ ወደ ቤትህ ነው እንጂ ወደ ቭርንዳቫና አይደለም፡፡ ይህ ቭርንዳቫን አይደለም፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” “እሺ ጌታዬ በስህተት እዚህ መጥተሀል፡፡ አሁን እዚሁ ቆይ፡፡” ከዚያም አድቨይታ የጌታ ቼይታንያ እናት ወደ እዚህ ቤት እንድትመጣ ሰው ላከ፡፡ ምክንያቱም ጌታ ቼታንያ ሳንያስ በመውሰዱ ወደ ቤቱ እንደማይሄድ ያውቅ ነበረ፡፡ እናቱ ደግሞ አንድ ልጇ በመሆኑ እሷም በናፍቆት እብድ ሆና ነበረ፡፡ ሰለዚህ እናቱ ለመጨረሻ ግዜ እንድታየው እድል ሰጣት፡፡ ይህም የታቀደው በአድቨይታ ነበረ፡፡ እናቱም እንደመጣች ቼታንያ መሀፕራብሁ ወዲያውኑ ወደ መሬት እግርዋ ላይ ወደቀ፡፡ እርሱም የ24 ዓመት ወጣት ነበረ፡፡ እናቱም በዚህ እድሜው ሳይያስ (መነኩሴነት) መውሰዱን ስታይ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ምክንያቱም ቤት ሚስቱ አለች እንዲሁም እናት እንደመሆኗ በተፈጥዋ ሀዘን ተሰማት፡፡ ሰለዚህ ቼታንያ መሀ ፕራብሁ እናቱን ለማባበል በጥሩ ቃላቶች ማነጋገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አላት፡፡ “እናቴ ሆይ ይህ ገላዬ በተፈጥሮ የተሰጠኝ በአንቺ በኩል ነው” ሰለዚህም ይህንን ገላዬን ለአንቺ አገልግሎት መጠቀም ይገባኝ ነበረ፡፡ ”ነገር ግን እኔ ሞኝ ልጅሽ ነኝ፡፡ ስህተትም አድርጌአለሁ፡፡ ሰለዚህም ምህረት አድርጊልኝ፡፡“ ይህም ታሪክ ሀዘን የተሞላበት ነው......የእናት እና ልጅ መለያየት..........