AM/Prabhupada 0305 - አብዩ ጌታ ሞቷል ብለን እናወራለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ምትሀት የተሸፈነውን ዓይናችንን መግለጥ ይኖርብናል፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0304
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0311 Go-next.png

አብዩ ጌታ ሞቷል ብለን እናወራለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ምትሀት የተሸፈነውን ዓይናችንን መግለጥ ይኖርብናል፡፡
- Prabhupāda 0305


Lecture -- Seattle, October 2, 1968

ፕራብሁፓድ፡ ቀጥል ታማላ ክርሽና፡ "ነዋሪው ነፍስ ልክ እንደ ፀሀይ ጮራ ሞሎኪዩል ሊመሰል ይችላል፡፡" "ክርሽና ደግሞ እንደሚውለበለበው የፀሀይ ኮከብ ሊመሰል ይችላል፡፡" ጌታ ቼታንያም እነዚህን ነዋሪ ነፍሳት ልክ እንደሚያውለበልብ የእሳት ቅንጣፊዎች አመሳስሏቸዋል፡፡ አብዩን የመላእክት ጌታ ደግሞ እንደሚያውለበልበው የፀሀይ እሳት አመሳስሎታል፡፡ ከዚህም ጋር የተያያዘ አንድ ጥቅስ ከቪሽኑ ፑራና ጠቅሶ ነበረ፡፡ በዚህም ጥቅስ እንደተጠቀሰው በዚህ ትእይንተ ዓለም የምናያቸው ፍጥረታት ሁሉ የአብዩ የመላእክት ጌታ ሀይል እንደመሆናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ከአንድ ቦታ የሚመነጭ እሳት ብርሀኑን እና ሙቀቱን በአካባቢው አቸራጭቶት ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ጌታ ምንም እንኳን በአንድ ቦታ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ተቀምጦ ቢገኝም የእርሱ ሀይል በመላው የትእይንተ ዓለም ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ ፕራብሁፓድ፡ ይህ ቀላል ነው፡፡ ለመረዳትም ጥረት አድርጉ፡፡ ለምሳሌ ይህ እሳት ወይም ፋኖስ አንድ ቦታ ተቀምጦ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ብርሀኑ በመላው ክፍል ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በትእይንተ ዓለም ውስጥ የምናየው ነገር ሁሉ የአብዩ የመላእክት ጌታ ሀይል ነው፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታ በአንድ ቦታ ይገኛል፡፡ ሰለዚህም በብራህማ ሰሚታ እንዲህ ብለን እንዘምራለን፡፡ "ጎቪንዳም አዲ ፑርሻም ታም አሃም ብሀጃሚ" እርሱም ሰው ነው፡፡ ልክ እንደ ፕሬዝደንት ሚስተር ጆህንሰን በዋሺንግተን ክፍሉ ውስጥ ተቀምጦ ሀይሉ እና ግዛቱ በመላው አገር ይሰማ ነበረ፡፡ ይህ በቁሳዊ ዓለም የሚቻል ከሆነ አብዩ አምላክ ክርሽናም በአንድ ቦታ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ይህም የአብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ቫይኩንታ ይባላል፡፡ ነገር ግን ሀይሉ በመላው የትእይንተ ዓለም ተሰራጭቶ ሲሰራ ይገኛል፡፡ ሌላው ምሳሌ ፀሀይ ናት፡፡ ፀሀይ በአንድ ሩቅ ቦታ ላይ ሆና እንደምትገኝ ለማየት እንችላለን፡፡ ቢሆንም ግን የፀሀይ ሀይል በመላው ትእይንተ ዓለም ተሰራጭቶ እናየዋለን፡፡ የፀሀይ ጮራ በክፍላችንም ውስጥ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የምንጠቀምባቸውም ሆነ እኛ እራሳችን የአብዩ አማላክ የተሰራጨን ሀይሎች ነን፡፡ እኛ ራሳችን ከእርሱ ተነጥለን ልንታይ አንችልም፡፡ ነገር ግን የማያ ዳመና ወይንም የቁሳዊው ዓለም ምትሀት ዓይናችንን ሲሸፍነው ይህንን ፀሀይ (አብዩ አምላክ) ለማየት ያዳግተናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የዚህ የቁሳዊው ዓለም ሕይወት አእምሮዋችንን ሲሸፍነው አብዩ አምላክን ለመረዳት ያዳግተናል፡፡ በዚህም ተሸፍነን አብዩ አምላክ ሞቷል እንላለን፡፡ ሰለዚህ ከዚህ ከቁሳዊው ዓለም ምትሀት ዓይናችንን መግለጥ ያሰፈልገናል፡፡ ከዚያም አብዩ አምላክን በቀጥታ ለማየት እንችላለን፡፡ "አምላክ እዚህ ነው" አዎን እንዲ ለማለት እንበቃለን፡፡ በብራህማ ሰሚታ ውስጥ እንዲህ ብሎ ተጠቅሷል፡፡ "ፕሬማንጀና ቹሪታ ብሀክቲ ቪሎቻኔና ሳንታሀ ሳዳይቫ ህርዳዬሹ ቪሎካያንቲ" "ያም ሽያማሱንዳራም አቺንትያ ጉና ስቫሩፓም ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሀጃሚ" (ብሰ፡5 38) ይህም የመላእክት ሁሉ ጌታ "ሽያማሱንዳራ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሽያማሱንዳራ "ሽያማ" ማለት ጨለም ያለ ነገር ግን በጣም በጣም ቆንጆ ማለት ነው፡፡ ይህም በጣም ቆንጆ የሆነው ሰው አብዩ ታላቅ ሰው ክርሽና በሁሉም መንፈሳዊ ሰዎች ሁሌ እንደታየ ነው፡፡ "ፕሬማንጃና ቹሪታ ብሀክቲ ቪሎቻኔና" እንዴት ነው እነርሱስ ለማየት የሚችሉት? ምክንያቱም ዓይናቸው በአብዩ የመላእክት ጌታ የፍቅር ዘይት የተቀባ እና የተገለጠ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ዓይኖቻችን የማየት ችግር ካላቸው ሀኪም ያዘዘልንን ጠብታ በመጠቀም ዓይናችን የፀዳ እና ከህመሙ የጠራ ከሆነ ሁሉንም ነገር በትክክል ለማየት እንችላለን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እነዚህ የቁሳዊ ዓለም ዓይኖቻችን በአብዩ የመላእክት ጌታ የፍቅር ዘይት ከተቀባ አብዩ አምላክን ለማየት እንችላለን፡፡ “አብዩ አምላክ እዚህ ነው” ለማለት እንበቃለን፡፡ አብዩ አምላክም ሞቷል ልንል አንበቃም፡፡ ይህም የቁሳዊ ዓለም ሽፋን ይገለጣል፡፡ ይህንንም ሽፋን ለማስወገድ የክርሽና ንቃታችንን በዚህ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በጥሞና መከታተል ይገባናል፡፡