AM/Prabhupada 0345 - ክርሽና በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡
Lecture on SB 1.15.1 -- New York, November 29, 1973
እያንዳንዳችን ከክርሽና ጋር በጣም በቀረበ ሁኔታ የተገናኘን ነን፡፡ ክርሽናም በየእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው፡፡ በልባችን ቁጭ ብሎ ሲጠብቀን ይገኛል፡፡ “መቼ ነው ይህ ተንኮለኛ ፊቱን ወደ እኔ የሚያዞረው?” እንዲህ በማለት ይጠብቃል፡፡ በጣም ሩህሩህ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ በቁሳዊው ዓለም የምንገኝ ነፍሳት በተንኮለኛነታችን ፊታችንን ሁሌ ከክርሽና በቀር ወደ ሁሉ ስናዞር እንገኛለን፡፡ ይህ ነው የእኛ ደረጃ። በተለያዩ ሀሳቦች ሁሌ ለመደሰት እንፈልጋለን፡፡ ሁሉም የየራሱን ሀሳብ እያውጠነጠነ ነው፡፡ “አሁን ይህንን ላድርግ!“ እነዚህም ተንኮለኞች ትክክለኛውን መንገድ አልተረዱም፡፡ ደስታን ለማግኘትም ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ እና መሰረቱ ክርሽና እንደሆነ አልተረዱም፡፡ ይህንን አያውቁም፡፡ ”ና ቴ ቪዱህ ስቫርትሀ ጋቲም ሂ ቪሽኑም ዱራሻያ ዬ ባሂር አርትሀ ማኒናሀ (ሽብ፡ 7.5.31) በአገራችሁ እንደምታቱትም ብዙ የተለያዩ ነገሮችን እየሞከሩ ነው፡፡ ይህም ብዙ ከፍተኛ ፎቆችን በመገንባት ብዙ መኪናዎችን ትላልቅ ከተማዎችን በመገንባት ደስታን ለማግኘት እየሞከሩ ነው፡፡ ነገር ግን ልብ የሚያረካ ደስታ ጠፍቷል፡፡ ይህም ምን እንደጐደለባቸው ሰለማያውቁ ነው፡፡ ይህንንም የጐደለ ነገር እኛ እየሰጠን እንገኛለን፡፡ “ክርሽናን ውሰድ እና ደስተኛ ትሆናለህ፡፡” ይህ ነው የክርሽና ንቃት የሚባለው፡፡ ክርሽና እና ነፍሳት ሁሉ በጣም ቅርበት ባለው ደረጃ የተገናኙ ናቸው፡፡ ልክ እንደ አባት እና ልጅ ወይንም እንደ ሁለት ጓደኛሞች ወይንም እንደ ጌታ እና እንደ አገልጋይ በመሰለ ሁኔታ፡፡ እኛ ከክርሽና ጋር በጠበቀ ግኑኝነት ይዘን እንገኛለን፡፡ ነገር ግን ይህንኑን ከክርሽና ጋር ያለንን ግኑኝነታችንን ሰለዘነጋነው በዚህም ሁኔታ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ደስታን ለማግኘት በጥረት ላይ ስለአለን በውጤቱ ብዙ መከራ እና ስቃይ ስናይ እንገኛለን፡፡ ይህ ነው በዚህ ቁሳዊ ዓለም ያለንበት ደረጃ፡፡ “ክርሽና ቡሊያ ጂቭ ብሆጋ ቫንቻ ካሬ” እኛ ነፍሳት ሁሉ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ብዙ ደስታን ለማግኘት ስንሻ እንገኛለን፡፡ “ለምንድነው በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የምንገኘው? ለምን በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ አልተቀመጥንም?” በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ማንም ነፍስ ብሆክታ ወይንም የደስታ ተቀባይ ሊኖን አይችልም፡፡ ይህ የደስታ ተቀባይ አብዩ ጌታ ብቻ ነው፡፡ “ብሆክታራም ያግያ ታፓሳም ሳርቫ” (ብጊ፡ 5.29) በዚህም ስህተት የለም፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ግን ክርሽና የደስታ ሁሉ ተቀባይ እና የሁሉ ነገር ባለቤት እንደሆነ የሚያውቁ ነፍሳት ይኖራሉ፡፡ ይህም የመንፈሳዊ ዓለም ወይንም ቤተ መንግስት ተብሎ ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በዚህም በቁሳዊ ዓለም እንኳን እኛ የደስታ ተቀባዮች አለመሆናችንን የተረዳን ከሆነ ወይንም ክርሽና የደስታ ሁሉ ተቀባይ እርሱ መሆን እንደሚገባው የተረዳን ከሆነ ይህ እራሱ የመንፈሳዊ ዓለም ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ሁሉን ለማስተማር እና ለማሳመን የሚሞክር ነው፡፡ እኛ የደስታ ሁሉ ተቀባዮች አይደለነም፡፡ የደስታ ተቀባይ መሆን የሚገባው ሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ለምሳሌ ይህንን ገላችንን ስናየው የደስታ ተቀባይ የሆነው ሆድ ነው፡፡ ነገር ግን እጆቻችን እግሮቻችን ዓይኖቻችን ጆሮዋችን አእምሮዋችን እና ሁሉም ነገራችን ደስታ ሊያመጣ የሚችለውን ምግብ ሁሉ በመፈለግ እና በማዘጋቸት ስራቸው ለሆድ መስጠትን ነው፡፡ ይህም በተፈጥሮ ያለ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም የአብዩ አምላክ ክርሽና ወገን እና ቅንጣፊዎች ነን፡፡ የደስታ ተቀባዮች አይደለም፡፡ ክርሽናንም በማስደሰት የእኛ ደስታ ወዲያውኑ ይመሰረታል፡፡