AM/Prabhupada 0357 - ይህንን የዓብዩ ጌታ እምነት የሌለበትን ስልጣኔ ለመቋቋም አብዮት መፍጠር እፈልጋለሁ፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

ይህንን የዓብዩ ጌታ እምነት የሌለበትን ስልጣኔ ለመቋቋም አብዮት መፍጠር እፈልጋለሁ፡
- Prabhupāda 0357


Morning Walk -- December 11, 1973, Los Angeles

ፕራብሁፓድ፡ ጤንነቴ በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን እየሞከርኩኝ እገኛለሁ፡፡ ይህን ነው የእኔ ፍላጎት፡፡ ይህንን አንድ ትልቅ እንቅስቃሴ ለመጀመር እፈልጋለሁ፡፡ ይህንን አብዩ የመላእክት ጌታ የሌለበትን ስልጣኔያቸውን ለመቋቋም እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ የጋለ ፍላጎት፡፡ ይህንንም ስርዓት ለማስተማር እና ለመመምራት በአሜሪካኖች መጀመር ጥሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም እነሱ በአሁኑ ግዜ የዓለም መሪዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ አሁን ግን እውነተኛ መሪዎች መሆን ይገባቸዋል፡፡ በዚህም መንገድ መላ ዓለም ደስተኛ ይሆናል። ለዚህም መመሪያ መስጠት እችላለሁ፡፡ የበላይ ሀላፊነት ያላቸው አሜሪካኖች ወደ እኔ ቢመጡ እንዴት የዓለም መሪዎች ለመሆን እንደሚችሉ መመሪያ ለመስጠት እችላለሁ፡፡ ይህም የሀሰተኛ መሪ ሳይሆን እውነተኛ እና ትክክለኛ መሪዎች ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አብዩ አምላክ በብዙ ነገር በረከት ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም እንቅስቃሴ የጀመረው ከአሜሪካ ነው፡፡ ይህንንም እንቅስቃሴ የጀመርኩት ከኒው ዮርክ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህንን እንቅስቃሴ መንግስት ሶስተር ብሎ መውሰድ ይገባዋል፡፡

ህርዳያናንዳ፡ አሜሪካ በጣም አስፈላጊ አገር ነው የምትለውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ህርዳያናንዳ፡ እንደምታስበው.....

ፕራብሁፓድ፡ ሰለዚህም ወደ አገራችሁ መጥቻለሁ

ህርዳያናንዳ፡ ምናልባት...

ፕራብሁፓድ፡ ምክንያቱም እናንተ በጣም አሰፈላጊዎች ናቸሁ፡፡ አሁን ማድረግ ያለብህ... በእኔ መመሪያ ስር ደግሞ ከአሁኑ በላይ የውሸት ሳይሆን የእውነት አስፈላጊዎች ማድረግ ይቻላል፡፡

ህርዳያናንዳ፡ እንደዚያ ከሆነ እዚሁ በመቅረት ስብከቴን መቀጠል ይገባኛል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ?

ህርዳያናንዳ፡ ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ እኔም እዚሁ በመቅረት ሩፓ ኑጋን በማገዝ መርዳት አለብኝ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህንን መላ ሕብረተሰብ ወደ አብዩ አምላክ ንቃት ቀይሩት፡፡ ምክንያቱም በኮንስቲቲውሽናቸው አውጀውታል፡፡ “በአብዩ አምላክ እናምናለን” አሁን ታድያ ይህንን ኮስተር ብለው መከታተል ይገባቸዋል፡፡ “አብዩ አምላክ” ማለት ምን ማለት ነው? "እምነት“ ማለትስ ምን ማለት ነው? ይህንን ስብከት ጀምሩ፡፡ ይህንንም በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በአብዩ አምላክ እናምናለን፡፡ ሰለዚህም መላ ሕይወታችንን መስዋዕት አድረገን እንገኛለን፡፡ ይህ ነው በአብዩ አምላክ እምነት ማለት፡፡ በየአገልግሎቱ ቤት ሲጃራ እያጨሱ በአብዩ አምላክ እናምናለን ማለት አይበቃም፡፡ ይህ ዓይነቱ እምነት አይፈለግም፡፡ ትክክለኛ እምነት ግን ያሰፈልጋል፡፡