AM/Prabhupada 0436 - በሁሉም ነገር ደስተኛ እና በክርሽና ንቃታችን ተመስጠን መገኘት ይገባናል፡፡
Lecture on BG 2.8-12 -- Los Angeles, November 27, 1968
አገልጋይ፡ ጥቅስ 11፡ የተባረከው ጌታ እንዲህ አለ፡ “ንግግር የአዋቂ ሰው ቢሆንም ሃዘን የማይገባው ነገር ላይ በሀዘን ላይ ሆነህ ትታያለህ፡፡” አዋቂ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ሕይወት ላለውም ሆነ ለሞተ ሰው ሀዘን አይሰማቸውም፡፡(ብጊ፡ 2.11) ገለፃ፡ “አብዩ ጌታም ወዲያውኑ የአስተማሪነትነ ደረጃ ያዘ፡፡ ተማሪውንም በጎን ሞኝነቱን እየገለፀለት መገሰፅ ጀመረ፡፡” አብዩ ጌታም እንዲህ አለ፡፡ “የምትናገረው ንግግር ሁሉ እንደተማረ ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ማን የተማረ እንደሆነ አታውቅም” “የቁሳዊ ገላችን ምን እንደሆነ ነፍስ ምን እንደሆነች በትክክል የሚያውቅ ሰው ገላ በደረሰበት በማናቸውም ደረጃ ላይ ሀዘን አይሰማውም፡፡” ”ይህም በሕይወትም ሆነ በሞት ደረጃ ላይ ቢሆንም ነው፡፡“ በሚቀጥሉት ምእራፎችም እንደተገለፁት እውቀት ማለት ቁሳዊ አካልን ነፍስን እና ሁለቱንም የሚቆጣጠረውን ሀይል ማወቅ ማለት ነው፡፡ አርጁናም እንዲህ ብሎ ተከራከረ “የሀይማኖት መመሪያዎች ከፖሊቲካ እና ከህብረተሰብ ጥናት በላይ አስፈላጊነት እንዲሰጣቸው ይገባል፡፡” ነገር ግን የቁሳዊ ነገሮች የነፍስ እና የጌታ እውቀት ከሀይማኖታዊ ስርአቶች በላይ አስፈላጊ መሆናቸውን የተረዳ አልነገረም፡፡ የእነዚህም እውቀቶች ስለ አልነበረው እራሱን እንደ አዋቂ አድርጎ ማቀረብ አልነበረበትም፡፡ በእነዚህ ርእሶችም ምሁር ሰለአልነበረ በዚህም ምክንያት ማዘን የማይገባላቸው ነገሮች ላይ በሀዘን ተመስጦ እንደነበረ ታይቶ ነበር፡፡ ቁሳዊ ገባችን ተወልዶ ዛሬ ወይንም ነገ ሊጠፋ የሚችል አካል ነው፡፡ ስለዚህ ቁሳዊ ገላችን እንደ ነፍሳችን አስፈላጊ ሆኖ መታየት አይገባውም፡፡ ይህንንም በትክክል የተረዳ ሰው የተማረ ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለእርሱም የየትኛውም የቁሳዊ ገላችን ደረጃ ሊያሳዝነው አይችልም፡፡
ፕራብሁፓድ፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል “ይህ ገላ በሞትም ላይ ሆነ በሕይወት እያለ ምንም ዓይነት ሀዘን ማምጣት የለበትም፡፡” የሞተ ገላ፡ ለምሳሌ ቁሳዊው ገላ ከሞተ ምንም ዓይነት ጥቅም አይኖረውም፡፡ ታድያ ማዘኑ ምን አይነት ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ለብዙ ሺህ ዓመታትም በሀዘን ብንቀመጥ ወደ ሕይወት ሊቀየር አይችልም፡፡ ስለዚህም በሞተ ገላ ላይ በሀዘን መቀመጥ ምክንያት አይኖረውም፡፡ የመንፈሳዊውም ነፍስም እንደሆነች ዘለአለማዊ ሕይወት ያላት ናት፡፡ ምንም እንኳን ቁሳቂ ገላ የሞተ ቢመስልም ወይንም ከሞተም በኋላ ነፍስ ልትሞት አትችልም፡፡ ታድያ ለምን አንድ ሰው በጣም ሊጨነቅ ይገባዋል? "ኦ አባቴ ሞተ“ ”እንዲህ ዓይነቱ ዘመዴ ሞተ“ ከዚያም ለቅሶ መቀመጥ? እነርሱም ሁሉ አልሞቱም፡፡ ይህ እውቀቱ እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ዓይነት የበሰለ አስተሳሰብ ሰው ከሀዘን መራቅ ይችላል፡፡ በክርሽና ንቃትም ያለው ፍላጐቱ እያደገ ይመጣል፡፡ ለቁሳዊው ገላ በሕይወትም ሆነ በሞት ግዜ ምንም ማዘን አይገባም፡፡ ይህም በክርሽና በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተገልጿል፡፡ ቀጥል
አገልጋይ፡ ”እኔ ያልኖርኩበት ግዜ የለም አንተም ወይንም እነዚህም ንጉሶች ሁሉ“ ወደፊትም ማናችንም ብንሆን ከመኖር የምንቆምበት ግዜ አይኖርም፡፡ (ብጊ፡ 2.12) ገለፃ፡ ”በቬዳዎች ውስጥ ማለትም በካትሀ ኡፓኒሻድ እና በሽቬታሽቫታራ ኡፓኒሻድ ውስጥ እንዲህ ተብሏል“
ፕራብሁፓዳ፡ ሽቬታሽቫታራ፡ ብዙ የተለያዩ ኡፓኒሻዶች አሉ፡፡ እነዚህም ሁሉ ቬዳዎች ይባላሉ፡፡ ኡፓኒሻዶች የቬዳዎች ርእሶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በየምእራፉ ርእሶች አሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ እነዚህ ኡፓኒሻዶች የቬዳዎች ርእሶች ናቸው፡፡ 108 የሚሆኑ አብይ የኡፓኒሻድ ስነፅሁፎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ሁሉ ዘጠኙ በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም ዘጠኝ ኡፓኒሻዶች የሚከተሉት አስፈላጊ ናቸው። ሽቬታስቫታራ ኡፓኒሻድ፡ ታይቲሬያ ኡፓኒሻድ፡ አይትሬያ ኡፓኒሻድ፡ ኢሾፓኒሻድ፡ ሙኩንዳ ኡፓኒሻድ፡ ማንዱክያ ኡፓኒሻድ፡ ካትሆ ኡፓኒሻድ እነዚህ ኡፓኒሻዶች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ በተጠቀሱትም ገለፃዎች ክርክር በተነሳም ቁጥር አንድ ሰው ከእነዚህ ኡፓኒሻዶች ጥቅስ መጥቀስ ይገባዋል፡፡