AM/Prabhupada 0521 - የእኔ መመሪያ የሩፓ ጎስዋሚን ፈለግ መከተል ነው፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Los Angeles, December 2, 1968

ይህንንም ስርዓት በመከተል የክርሽና ንቃትን ለመረዳት ሞክሩ፡፡ በተገኘው መንገድ ህልውናችሁ ወደ ክርሽና እንዲቀርብ አድርጉ፡፡ በተገኘው መንገድ፡፡ “ዬና ፕራካሬና” ለምሳሌ አንድ የምትወዱትን ሰው ለማግኘት ስትፈልጉ እርሱን ለማግኘት የተለያየ ነገሮችን ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ይህም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ታክቲኮቹን ሁሉ እናውቃለን፡፡ እንስሳ እንኳን የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት እውቀቱ አለው፡፡ ለመኖር ትግል ማድረግ ማለት እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ብዙ ታክቲክ እየተጠቀመ ሙከራ ማድረግ ነው፡፡ እናንተም ይህንን የቁሳዊ ዓለም “ዊል ኦ ዘ ዊስፕ” ከመከታተል በተለያየ ታክቲክ ክርሽናን ለማግኘት ሞክሩ፡፡ በተቻለው መንገድ እና ታክቲክ ክርሽናን ለመያዝ ሞክሩ፡፡ ይህም ሕይወታችሁን የተሳካ እንዲሆንላችሁ ያደርጋል፡፡ ዬና ቴና ፕራካሬና ማናሀ ክርሽኔ ኒቬሻዬት ሳርቬ ቪድሂ ኒሴድሀህ ስዩር ኤታዮር ኤቫ ኪንካራህ አሁን እንደምናየው በክርሽና ንቃተ እንቅስቃሴያችን ብዙዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ እኔም ይህንን አንድ በአንድ እና ቀስ በቀስ እያስተዋወቅሁ እገኛለሁ፡፡ የክርሽና ንቃትንም በህንድ አገር ውስጥ የሚከታተሉት ሁሉ ብዙ መመሪያ እና ህግጋቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ሰውም እንዲህ ሲለኝ ይገኛል፡፡ “ስዋሚጂ ባህል አጥባቂ ሆኖ ብዙ መመሪያ እና ህግጋቶችን ያበዛል“ ነገር ግን አንድ በመቶ የሚሆንም አዲስ ነገር የጨመርኩት የለም፡፡ ምክንያቱም በዚህ በአገራችሁ እነዚያን ሁሉ መመሪያዎች እና ህግጋቶችን ለማስተዋወቅ አይቻልም፡፡ የእኔ መመሪያ ግን የሩፓ ጐስዋሚን መንፈሳዊ ፈለግ መከተል ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ብሏል፡፡ በተገኘው መንገድ በመጀመሪያ ደረጃ ለክርሽና ቅርበታቸውን እና ፍቅራቸውን ያዳብሩ፡፡ ይህ ነው የሚያስፈልገው መመሪያ እና ህግጋቶችን በኋላ ሊከተሏቸው ይችላሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ለክርሽና ቅርበት እና ፍቅር ይኑረው፡፡ የዮጋ ስርዓት ማለት ይህ ነው፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሎ አስረድቶናል ”ማዪ አሳክታ ማናሀ ፓርትሀ“ ስለዚህ ወደ ክርሽና ለመቅረብ ሞክሩ፡፡ የማትቀርቡበትስ ምን ምክንያት ይኖራችኋል፡፡ በክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ውስጥ ብዙ ቆንጆ ነገሮች አሉን፡፡ ሰዓሊዎች አሉን ብዙ ስእሎችንም አበርክተዋል የመደነስ ስርዓት አለን ሙዚቃም አለን አንደኛ ደረጃም ምግብ አለን አንደኛ ደረጃ ልብስም አለን አንደኛ ደረጃም ጤንነት እንዲሁም ያለን ነገር ሁሉ በአንደኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ሞኝ እና ተንኮለኛው ብቻ ነው ይህንን አንደኛ ደረጃ ነገሮች የማይቀበለው፡፡ እነዚህንም ለማድረግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ታድያ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ እና ስርዓቱን ለመከተል ምን ያዳግተናል? የማይከተልበት ምክንያት ካለው እርሱ አንደኛ ደረጃ ተንኮለኛ ሰለሆነ ነው፡፡ በእውነቱ ለመናገር ይኅው ነው፡፡ ማንም ሰው ክርሽና ንቃትን ባለመቀበሉ አንደኛ ደረጃ ተንኮለኛ መሆኑን የማይቀበል ከሆነ ወደ እኔ ይምጣ፡፡ እኔም ይህንን ላረጋግጥለት እችላለሁ፡፡ ስለዚህ አንደኛ ደረጃ ተንኮለኞች አትሁኑ፡፡ አንደኛ ደረጃ አዋቂ ሰዎች ሁኑ፡፡ የቼይታንያ ቻሪታምርታ ደራሲም እንደተናገረው ”ክርሽና ዬ ብሃጄ ሴይ ባዳ ቻቱራ“ የክርሽና ንቃትን የሚከታተል ማንም ሰው ቢሆን አንደኛ ደረጃ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ አንደኛ ደረጃ ሞኞች አትሁኑ፡፡ አንደኛ ደረጃ አዋቂ ሰው ሁኑ፡፡ የእኔ መጠይቅ ይኅው ብቻ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ ጥያቄ ያለው አለ? ባለፈው ግዜ ብዙ ተማሪዎች መጥተው ነበረ፡፡ ዛሬ ግን ብዙ ሰው የለም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ደረጃ ተንኮለኞች ለመሆን ሰለሚፈልጉ ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ ይህም እርግጥ ነው፡፡ ሰለዚህ አንድ ሰው አዋቂ ካልሆነ የክርሽና ንቃትን ለመከታተል አይችሉም፡፡ የሚፈልጉትም ለመሞኘት ለመታለል ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ ቀጥ ያለ ነገር ቀላል ነገር ሆኖ ውጤቱ ግን በጣም ትልቅ ነው፡፡ ይህንንም ለመቀበል አይስማሙም፡፡