AM/Prabhupada 0526 - ሽሪ ክርሽና አጥብቀን ከያዝነው “ማያ” ምንም ልታደርገን አትችልም፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Los Angeles, December 2, 1968

ታማላ ክርሽና፡ ማያ አንድን ሰው ጥብቅ አድርጋ ከያዘች ይህ ሰው በአስቸኳይ ሊወጣበት የሚችልበት መንገድ ምንድን ነው?

ፕራብሁፓድ፡ ኦ ከዚህ ክርሽና ብቻ ነው የሚያወጣህ የማያ ፍላጎት በተሰማህ ግዜ ሁሉ ወደ ክርሽና ሁሌ ፀሎት አድርግ፡፡ “እባክህ አድነኝ! እባክህ አድነኝ!“ ይህ ብቻ ነው፡፡ ከዚህም ሊያድንህ ይችላል፡፡ እኛም ያለነው በማያ ቤተ መንግስት ነው፡፡ ማያም እዚህ ሀይል ያላት ሆና ትገኛለች፡፡ ነገር ግን ክርሽናን በጥብቅ ከያዝነው ማያ ምንም ነገር ለማድረግ አትችልም፡፡ ሰለዚህም መንፈሳችን ዳብሮ ክርሽናን አጥበቀን የመያዝ ስልቱ እንዲኖረን ያሰፈልጋል፡፡ በዚህም ፈለግ መውደቅ የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ ማድሁቪሳ፡

ፕራብሁፓድ፡ በሳንኪርታን ላይ ውጪ እየዘመርን እያለን የተሰበሰበውን ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው ከበውን ከእኛ ጋር እንዲዘምሩ ለማድረግ ምን ማድረግ ይገባናል፡፡ የትኛው ነው አመቺ መንገድ?

ፕራብሁፓድ፡ አመቺው መንገድ መዘመራችሁን መቀጠል ብቻ ነው፡፡ ዋናው ዓላማችሁ ህዝቡን ለማርካት አይደለም፡፡ ዋናው ዓላማችሁ ክርሽናን ለማርካት መሆን አለበት፡፡ በዚህም ስርዓት ህዝቡ አውቶማቲካሊ ሊደሰት ይችላል፡፡ እኛ ህዝቡን ለማስደሰት አይደለም የምንሄደው፡፡ እኛ የምንሄደው ክርሽናን ልንሰጣቸው ነው፡፡ ስለዚህ ክርሽናን እንዴት በትክክል እንደምትሰጡ በጥንቃቄ አጥንታችሁ እና አረጋግጣችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ በዚህም ስርዓት ሁሉም የረካ ይሆናል፡፡ ዋናውም ዓላማችሁ ክርሽናን ለማስደሰት መሆን አለበት፡፡ በዚህም ስርዓት ሁሉም ደስተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ”ታስሚን ቱስቴ ጃጋት ቱስታ“ ክርሽና የተደሰተ ከሆነ መላ ዓለም ደስተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ውሀ ወደ ዛፉ ስር የምታፈሱ ከሆነ አውቶማቲካሊ መላ ቅርንጫፎች እና ቅጠላ ቅጠሎች እንደሚረኩ የተረጋገጠ ነው፡፡ ክርሽና እንደዚህ ትልቅ ዛፍ ይቆጠራል፡፡ እናንተም ይህንን ዛፍ ውሀ የምታጠጡ ትሆናላችሁ፡፡ የክርሽናን ቅዱስ ስም ሀሬ ክርሽናን ዘምሩ መመሪያዎችንን እና ስርዓቶችን ተከተሉ፡፡ ከዚያም ሁሉ ነገር የተሳካ ይሆናል፡፡