AM/Prabhupada 0561 - “ደሚጐዶች” ማለት እንደ አማላክ ናቸው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የአብዩ አምላክ ባህርይ ስላላቸው ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0548
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0566 Go-next.png

“ደሚጐዶች” ማለት እንደ አማላክ ናቸው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የአብዩ አምላክ ባህርይ ስላላቸው ነው፡፡
- Prabhupāda 0561


Press Interview -- December 30, 1968, Los Angeles

ጋዜጠኛ፡ እሺ ይህንን ለመረዳት ልሞክር፡፡ አሁን የምትለኝ በጨረቃ ላይ ነዋሪዎች አሉ ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ጋዜጠኛ፡ እሺ በእርግጥ አሉ፡፡ እነዚህስ መላእክቶች ናቸውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ጋዜጠኛ፡ መላእክቶች አሉ፡፡ ይህንንስ የምታውቀው እንዴት ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይህም ከቬዲክ ስነጽሁፎቻችን ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ ከየትኛው ስነፅሁፍ?

ፕራብሁፓድ፡ የቬዲክ ስነጽሁፎች

ጋዜጠኛ፡ ፊደሎቹ እንዴት ናቸው?

ፕራብሁፓድ፡ ቬ ዲ ክ

ጋዜጠኛ፡ አሀ ቬዲክ ይቅርታ

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ጋዜጠኛ፡ እንዲህ ብጠይቅህ መቼም ትእግስት ታደርግልኛለህ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይህ ምንም አይደለም፡፡

ጋዜጠኛ፡ አንተን ማስቀየሜ አይደለም፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አንዳንድ ግዜ የንግግርህን አክሰንት መከተል ያዳግተኛል፡፡

ጋዜጠኛ፡ ተረድቻለሁ

ፕራብሁፓድ፡ ይህን የሚያመጣው የአገር ልዩነት ነው፡፡ ምንም ችግር የለውም፡፡

ጋዜጠኛ፡ በዚያም ስነጽሁፍ የቬዲክ ስነጽሁፍ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል ሰዎች በጨረቃ ላይ እንዳሉ?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ጋዜጠኛ፡ ነገር ግን እነዚህ መላእክቶች ናቸው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ መላእክቶች ማለት ከእኛ ከዚህ ምድር ሰዎች በላይ በጣም የበለፀጉ ናቸው ማለት ነው፡፡ እነርሱም እንደኛ ነዋሪ ነፍሳት ናቸው፡፡ ነገር ግን የሕይወታቸው እድሜ ረጅም ነው፡፡ ሕይወታቸው ጥራት ያለው ነው፡፡ ስልጣኔያቸው መንፈሳዊ እውቀታቸው ከሰው ሲወዳደር በጣም ወደፊት የገፋ ነው፡፡ሰለዚህም መላእክት ይባላሉ፡፡ ይህም ማለት እንደ አምላክ ባህርይ ያላቸው ማለት ነው፡፡ በስልጣኔያቸው በጣም ወደፊት የሄዱ ናቸው፡፡ መላእክት ማለት ልክ እንደ የመላእክት ጌታ ማለት ነው፡፡ የአብዩ የመላእክት ጌታ ባህርዮች አሏቸው፡፡ የትእይንተ ዓለንም ፍጥረታትን ይቆጣጠራሉ፡፡ አንዳንዶቹ የዝናብን ወቅት ይቆጣጠራሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሙቀትን ይቆጣጠራሉ፡፡ ይህም የሚመሰለው ልክ እዚህ እንደምናያቸው ተቆጣጣሪዎች ነው፡፡ እዚህም የክፍል ሀላፊዎች እና የክፍሎችም ሀላፊዎች ይታያሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ይህ የትእይንተ ዓለምም እንደዚሁ ትልቅ አእምሮ አለው፡፡ዳይሬክተሮች እንዲሁም አስተዳደር አሉት፡፡ ሰዎች ላይቀበሉት ይችላሉ፡፡ ተፈጥሮ፡፡ ተፈጥሮ ስንል ምን ማለት ነው? በተፈጥሮ በጣም የሚያምሩ እና ቆንጆ ነገሮች አውቶማቲካሊ ሲካሄዱ እናያለን፡፡ ይህስ ያለ ምንም ቁጥጥር ነውን? አያችሁ?

ጋዜጠኛ፡ አዎን በእርግጥ ይህም ነው አንድ ሰው ሁልግዜ ሲጠይቅ የምናየው፡፡ ይህም የሰው ልጅ በሕይወቱ መልስ ሊያገኝለት የሚፈልገው ጥያቄ እና ስለ እራሱም ሊረዳበት የሚፈልገው ጥያቄ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ነገር ግን ስሜት የሚሰጥ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ያሰፈልጋል፡፡ የሰው ልጅ መንኮራኩርን ለማምጠቅ ይፈልጋል፡፡ ብዙ የሳንቲፊክ አእምሮዎች ሲሰሩ እናያለን፡፡ ስንትና ስንትም እንደመንኮራኩር በህዋ ላይ የሚንሳፈፉ ፕላኔቶችም እናያለን፡፡ እነዚህም በሰማይ ላይ ሲንሳፈፉ እናያለን፡፡ ይህም ምንም አእምሮ የለውም ማለት ስሜት ይሰጣልን? ይህ ምንድን ነው? ይህ ትክክለኛ ሙጉትን የያዘ ነውን?

ጋዜጠኛ፡ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ይህንንም ማሰብ አለብኝ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይህንንም ማወቅ አለብህ፡፡ እንዴት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም ትእይንተ ዓለም በላይ ታላላቅ አእምሮዎች እንዳሉ መረዳት ይኖርብናል፡፡ እነዚህም አእምሮዎች እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ጋዜጠኛ፡ ታድያ ጨረቃ ምን ደረጃ ይዛ ትገኛለች? ምን ልበልህ? የደሚጐዶች ሁሉ ዋና ፅህፈት ቤት ናት ማለት እንችላለን?

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም በጨረቃም ደረጃ ብዙ ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ በጣም ብዙ ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ ጨረቃም አንዷ ናት፡፡

ጋዜጠኛ፡ እነዚህስ መላእክቶች መሬትን ጐብኝተዋት ያውቃሉ?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ከዚህ በፊት ይመጡ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በስልጣኔያቸው የገፉ እና በመላእክትም ለመጐብኘትም ብቁ ነበሩ፡፡ አየህ?

ጋዜጠኛ፡ ከዚህ በፊት ስትልስ መቼ ነው? ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ማለትህ ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም ይህም ቢያንስ ቢያንስ ከ 5000 ዓመታት በፊት ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ ተረዳሁለመጨረሻ ግዜ የመጡት ቢያንስ 5000 ዓመት በፊት ነው፡፡ ታድያ የሰው ልጅ ምስል ይዘው ነው የሚመጡትን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህንን የመሰለ መረጃ ነው ያለን፡፡ አንዳንድ ግዜ ታላላቅ መስዋእቶች ይደረጉ ነበረ፡፡ በዚህን ግዜም መላእክት ከሌሎች ፕላኔቶች ተጋብዘው ይመጡ ነበረ፡፡ ይህንንም ግብዣ አክብረው ይመጡ ነበረ፡፡

ጋዜጠኛ፡ ከየት የመጡ ነበረ? ይህስ መረጃ የተመሰረተው በቬዲክ መፃህፍት ውስጥ ሰለተጠቀሰ ነው?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ጋዜጠኛ፡ ተረዳሁ

ፕራብሁፓድ፡ በእኔ የተፈጠረ ነገር አይደለም፡፡

ጋዜጠኛ፡ አዎን በእርግጥ እርሱን አውቃለሁ፡፡ ይህንንም ማለቴ አይደለም፡፡ መረጃው ከየት እንደመጣ ለማወቅ ስለፈለግሁ ነው፡፡