AM/Prabhupada 0600 - ሙሉ ልቦናችንን ለመስጠት ዝግጁ አይደለንም፡፡ ይህ ነው የዓለማዊው በሽታችን፡፡



Lecture on BG 2.23 -- Hyderabad, November 27, 1972

ሰዎች ክርሽናን ስላልተረዱ ቼታንያ መሀፕራብሁ መጥቷል፡፡ ክርሽናም በብሀገቨድ ጊታ ”ለእኔ ሙሉ ልቦናህን ስጥ“ ብሎ ጠይቆናል፡፡ እርሱስ ምን ማድረግ ይችላል፡፡ እርሱ አብዩ አምላክ ነው፡፡ እርሱ ክርሽና ነው፡፡ በዚህም ጥቅስ እንደተጠቀሰው ”ሙሉ ልቦናህን ሰጠኝ እና እኔ ሙሉ ለሙሉ እንከባከብሀለሁ፡፡“ ”አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔ“ ነገር ግን እንዲህም ተገልጾ ሰዎች ይህንንም ሊረዱት አልቻሉም፡፡ ”ኦ ለምን ብዬ ለክርሽና ሙሉ ልቦናዬን እሰጣለሁ፡፡ እርሱም እንደ እኔ ሰው ነው፡፡“ ”ምናልባት ከእኔ ትንሽ አስፈላጊ ደረጃ ላይ ያለ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ለምን ብዬ ሙሉ ልቦናዬን እሰጣለሁ?“ ምክንያቱም በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ ያለን በሽታ ልቦናችንን ለማንም ያለመስጠት ነው፡፡ ሁላችንም በትእቢት ላይ እንገኛለን፡፡ ”እኔ እንዲህ ነኝ“ ይህም የቁሳዊ ዓለም በሽታ ነው፡፡ ከዚህም በሽታ ለመዳን ካስፈለገን ለአብዩ የመላእክት ጌታ ሙሉ ልባናችንን መስጠት ይገባናል። ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴና ፓሪፕራሽኔና ሴቫያ ኡፓዴክስያንቲ ቴ ግያናም ግያኒናስ ታትቫ ዳርሺናሀ :(ብጊ፡ 4.34)

ስለዚህ አንድ ሰው ሙሉ ልቦናውን ከትእቢት ወጥቶ ለመስጠት ዝግጁ ካልሆነ ወደፊት መራመድ አይችልም ይህም ለዓለማዊ ሰው በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ይገኛል፡፡ ማንም ሰው ሙሉ ልቦናውን ለመስጠት አይፈልግም፡፡ መወዳደርን ግን ይፈልጋል፡፡ ይህም ውድድር በግል የተመሰረተ በሰው ለሰው የተመሰረተ በቤተሰብ ለቤተሰብ የተመሰረተ እንዲሁም በአገር ለአገር የተመሰረተ ነው፡፡ ሁሉም የበላይ ለመሆን ይፈልጋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ሙሉ ልቦና ሰጥቶ መቀመጥን ማን ይፈልጋል? ሙሉ ልቦናን ለመስጠት በጣም አዳጋች ሆኗል፡፡ በሽታችንም ይህ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህንን ተንኮለኝነትን ለማቆም እና ይህንን ስር ሰደድ በሽታን ለማዳን ክርሽና ሙሉ ልቦናህን ስጠኝ ብሎ ጠይቋል፡፡ ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ (ብጊ፡ 18.66) ከዚያስ እኔ ሙሉ ልቦናዬን ከሰጠሁ ሁሉም ነገር አይወድቅምን? ይህም ንግዴ ፕላኔ ብዙ ያቀድኳቸው ነገሮች ሁሉ ሊወድቁ አይችሉምን? አይደለም፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሎናል፡፡ ”እኔ ሀላፊነትህን ሁሉ እወስዳለሁ፡፡ እኔ ሀላፊነትህ ሁሉ እወስዳለሁ፡፡“ አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሻዪምስያሚ ማ ሱቻሀ፡፡ "አታስብ አትጨነቅ” ብዙ ማረጋገጫ ቃላቶችን ሰጥቶናል፡፡ እንዲህም ሁሉ ሆኖ ሙሉ ልቦናችንን ለመስጠት ዝግጁ አይደለንም፡፡ በሽታችንም ይህ ነው፡፡ ስለዚህም ክርሽና እንደገና እንደ ትሁት አገልጋይ ሆኖ መጥቷል፡፡ ይህም እንዴት አድረገን ሙሉ ልቦናችንን ለመስጠት እንደምንችል ነው፡፡ ቼይታንያ መሀፕራብሁ፡፡ “ክርሽና ቫርናም ትቪሳክርሽናም ሳንጎፓንጋስትራ ፓርሳዳም” (ሽብ፡ 11.5.32)

ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ሳይንቲፊክ እና ስልጣን ያለው ነው፡፡ ይህም ስልጣን የሌለው በግምታዊ አእምሮ የተመሰረተ እንቅስቃሴ አይደለም፡፡ ስልጣን ያለው ነው፡፡ ይህም ክርሽና በቬዲክ ትእዛዞች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ክርሽናም እንዲህ ገልጾታል፡፡ “ሳርቫ ድሀርማ ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ” (ብጊ፡ 18.66) እኛ የምናስተምረው ይህንኑ ፍልስፍና ነው፡፡ ክርሽና አብዩ የመላእክት ጌታ እዚህ አለ፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታን እየፈለግህ ነው፡፡ አብዩ አምላክም ምን እንደሆነ ለመረዳት አልቻልክም፡፡ እኛም ይህንኑ አብይ አምላክ ክርሽናን እያቀረብን እንገኛለን፡፡ ይህም ቅዱስ ስሙን እንቅስቃሴዎቹን፡፡ እነዚህም ሁሉ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተጠቅሰው ይገኛሉ፡፡ እርሱንም ተቀብለህ ሙሉ ልቦናህን ስጥ፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ “ማን ማና ብሀቫ ማድ ብሀክቶ ማድ ያጂ ማም ናማስጁሩ” (ብጊ፡ 18.65) እኛም የምናስተምረው ይህንኑ ነው፡፡ ይህም በብሀቨገድ ጊታ ውስት የተገለፀውን ነው፡፡ መልእክቱን አንቀይረውም፡፡ የብሀገቨድ ጊታን መልእክትም አበላሽተን አናቀርብም፡፡ ይህንን ዓይነት ቀጣፊነት አናደርግም፡፡ አንዳንድ ግዜ ሰዎች እንዲህ ይሉኛል፡፡ “ስዋሚጂ የሰራኅው ስራ በጣም ጥሩ ነው፡፡” ነገር ግን ምን ተአምር ሰርቻለሁ? እኔ ማጂሻን አይደለሁም፡፡ የእኔ ጥሩ ስራ ግን ብሀገቫድ ጊታን አለመበረዜ ነው፡፡ ይህንንም ብሀገቨድ ጊታ ልክ በክርሽና እንደተዘመረው አድርጌ አቅርቤዋለሁ፡፡ ሰለዚህም በጣም የተሳካ እንቅስቃሴ ይዘን እንገኛለን፡፡ እናመሰግናለን፡፡