AM/Prabhupada 0599 - የክርሽና ንቃት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታ ታላቅ ነው፡፡ ሙሉ ልቦናችንንም ካልሰጠነው ልናገኘው አንችልም፡፡

Revision as of 06:05, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 2.23 -- Hyderabad, November 27, 1972

በሌላ ምዕራፍ በ ብራህማ ሰሚታ ስነ ፅሁፍ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ “ቬዴሱ ዱርላብሀም አዱርላብሀም አትማ ብሀክቶ” (ብሰ፡ 5 33) ”ቬዴሹ“ ምንም እንኳን የቬዲክ ስነፅሁፎችን የማጥናት ዓላማ ክርሽናን ለማወቅ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ክርሽናን ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህንም ቬዳዎች በእራሳችሁ በግምታዊ መንፈስ ለመረዳት ጥረት ይምታደርጉ ከሆነ ክርሽና በቀላሉ ሊከሰትላችሁ አይችልም፡፡ ቬዴሹ ዱርላብሀም አዱርላብሀም አትማ ብሀክቶ (ብሰ፡ 5 33) ነገር ግን የአብዩ ጌታን ትሁት አገልጋይ የሆነ መምህርን የቀረባቸሁ ከሆነ እርሱ መልእክቱን በትክክል ሊያቀርብላችሁ ይችላል፡፡ ማሂያሳም ፓዳ ራጆ ብሂሴካም ኒስኪንቺናናም ና ቭርኒታ ያቫት ናይሻም ማቲስ ታቫድ ኡሩክራማንግህሪም (ሽብ፡ 5.7.32) ፕራህላድ በሀራጅ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ “የክርሽና ንቃትን ያለ መምህር ማዳበር አዳጋች ነው” ”ናይሳም ማቲስ ታቫድ ኡሩክራማንግህሪም“ የክርሽና ንቃት ቀላል አይደለም፡፡ ሙሉ ልቦናችሁን ካልሰጣችሁ ንቃቱ ሊኖራችሁ አይችልም፡፡ ኒስኪንቻናናም ማሂያሳም ፓዳ ራጆ ብሂሴካም ኒስኪንቻናናም ና ቭርኒታ ያቫት የሎተስ እፅዋት ከመሰለው ከንፁህ አገልጋይ እግር የሚገኘውን አቧራ እስከአልወሰዳችሁ ድረስ “ኒስኪንቻናናም” ንቃቱ አዳጋች ይሆናል፡፡ እርሱም ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ጋር ምንም ፍቅር የለውም፡፡ ፍላጎቱ እና ሀሳቡ ሁሉ የተመሰጠው አብዩ አምላክን ለማገልገል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ከመሰለ ትሁት አገልጋይ ጋር ካልተገናኛችሁ የክርሽና ንቃታችሁን ለማዳበር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ እነዚህም የሻስትራ ወይም የቅዱስ መፃህፍቶች ድምደማ ነው፡፡ ክርሽና አብዩ እና ፍፁም የሆነው እውነት እና አብዩ ሰው ነው። ነገርግን እርሱን ለመረዳት በክርሽና ብሀክታ (ትሁት አገልጋይ) በኩል ካላለፍን በስተቀር ልንረዳው አንችልም፡፡ ስለዚህም ክርሽናን ለመረዳት ክርሽና እራሱ እንደ ብሀክታ (አገልጋይ) ሆኖ መጣ፡፡ ይህም ጌታ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና ቼይታንያ ፕራብሁ ኒትያናንዳ ሽሪ አድወይታ ጋዳድሀራ ሽሪቫሳዲ ጐውራ ብሀክታ ቭርንዳ ስለዚህ ክርሽናን ለመረዳት በጌታ ቼይታንያ በኩል መሄድ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ክርሽና እራሱ መጥቷል.....“ክርሽናያ ክርሽና ቼይታንያ ናምኔ“ በአንደኛው ሳይሆን በሁለተኛው ግዜ ሩፓ ጎስዋሚ ጌታ ቼይታንያ መሀፕራብሁን ያገኘው ግዜ በመጀመሪያው ግዜ የተገናኙት ሩፓ ጎስዋሚ የናዋብ ሁሴን ሻህ የመንግስት ሚኒስቴር ሆኖ ያገለግል የነበረ ግዜ ነው፡፡ በሁለተኛ ግዜ ከተገናኙም በኋላ ቼታንያ መሀፕራብሁ ተልእኮውን እንዲያሟሉለት ምኞቱን ገለፀ፡፡ ከዚህም በኃላ ሁለቱም ወንድማማቾች ከመንግስት ስራ ወጥተው ወደ ቼታንያ መሀፕራብሁ ሚሽን በመግባት የክርሽና ንቃትን ለማስፋፋት ውሳኔ አደረጉ፡፡ ስለዚህ ሩፓ ጎስዋሚ በአላሀባድ በፕራያግ ላይ ከቼይታንያ መሀፕራብሁ ጋር ሲገናኝ የመጀመሪያው ጥቅስ ገጥሞ ያዘጋጀው ይህ ነበረ፡፡ ናሞ መሀ ቫዳንያያ ክርሽና ፕሬማ ፕራዳያቴ (ቼቻ፡ ማድህያ 19,53) ”ጌታዬ ሆይ አንተ ከሁሉም በላይ የሆንክ ቸር እና መለኮታዊ ትውልድ ነህ“ ለምን? "ይህም የክርሽናን ፕሬማ (ፍቅር) ለሁሉም እያደልክ ስለምትገኝ ነው፡፡“ ሰዎች ክርሽና ማን እንደሆነ እንኳን ሊያውቁ አይችሉም፡፡ የክርሽናን ፍቅር ይቅርና፡፡ ነገር ግን ይህንን የክርሽና ፕሬማ አንተ በሰፊው እያደልከው ትገኛለህ፡፡ ”ናሞ መሀ ቫዳን“ ”ሰለዚህም አንተ ከሁሉም በላይ የሆንክ ቸር ሰው ነህ፡፡“ “ናሞ ማሀ ቫዳንያያ” ቫዳንያያ ማለት በጣም ቸር የሆነ ሰው ማለት ነው፡፡ ይህም ቸርነቱን እሰከሚፈለገው ድረስ የሚሰጥ ማለት ነው፡፡