AM/Prabhupada 0078 - እምነት በተሞላበት መንገድ ለማዳመጥ ሞክሩ፡፡
Lecture on SB 1.2.16 -- Los Angeles, August 19, 1972
"ሶ ሹሽሩሾ ሽራዳ ድሃናስያ ቫ ዱዴቫ ካትሃ ሩቺ" ባላፈው ጥቅስ እንዲህ ተገልጾ ነበር፡፡ "ያድ አኑድህያሲና ዩክታሃ" (ሽብ 1.2.15) አንድ ሰው የመንፈሳዊ ጎራዴውን በእጁ እንደያዘ አድርጎ እያሰበ፡ መንፈሳዊ አገለግሎቱን መቀጠል አለበት፡፡ የቅርሽና ንቃት እና አገለግሎትን ጎራዴ በእጁ ይዞ ከአለማዊ ኑሮ ነጻ መሆን አለበት፡፡ የተቋጠረው የአለማዊ ኑሮ ሊጎመድ የሚችለው በዚህ ጎራዴ ነው፡፡ ታድያ ይህንን ጎራዴ የምናገኘው ከየት ነው? የዚህም መመሪያ እዚህ ተሰጥቷል፡፡ በሙሉ ልቦና እምነት እና በጥሞና በማዳመጥ፡ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የመንፈሳዊውን ጎራዴ ማግኘት እንችላለን፡፡ በአሁኑ ግዜ፡ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበራችን እያደገ እና እየተሰፋፋ ይገኛል፡፡ በጥሞና በማዳመጥም፡ ይህንን ጎራዴ እያገኘን ነው፡፡ እንደምታውቁት ሁሉ ይህንን የክርሽና ንቃተ ማህበር የጀመርኩት፡ በኒው ዮርክ ውስጥ ነው፡፡ ጎራዴም በእጄ አለነበረም፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የሀይማኖት ተከታዮች፡ የቅዱስ መጽሃፍ በአንድ እጅ ይዘው፡ በሁለትኛ እጃቸው ደግሞ፡ የሰላ ጎራዴ ይይዛሉ፡፡ የሚሰጡትም መልእክት፡ “ይህን ቅዱስ መጽሀፍ ተቀበል፡ አለያ ግን አንገትህን በጎራዴው እጎረደዋለሁ” ይህም የተለየ አይነት ስብከት ነው፡፡ እኔም ብሆን ጎራዴ ነበረኝ፡ ይሁን እንጂ ይህን አይነት ጎራዴ አልነበረም፡፡ ይህ የእኔ ጎራዴ፡ ሰዎችን በጥሞና እንዲያዳምጡ እድል መስጠትን ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ “ቫሱዴቫ ካትሃ ሩቺ” ይህም ሰው ልክ “ሩቺ” (ጣእም) እንደአገኘ፡ ሩቺ ማለት ጣእም ማለት ነው፡፡ “አሀ ይህ የክርሽና ቃል ነው፡፡ ደስ ያሰኛል፡ ደጋግሜ ላዳምጥ” ብሎ ያሰላስላል፡፡ እንዲህ ነው የመንፈሳዊውን ጎራዴ የምታገኙት፡፡ ይህም ጎራዴ በእጃችሁ ነው፡፡ “ቫሱዴቫ ካትሀ ሩቺ” ታድያ ይህ ሩቺ ወይንም ጣእም የሚመጣው ከማን ነው? ከዚህም በፊት እንደ አስረዳሁት፡ ይህ ጣእም ልክ እንደ ስኳር ከረሜላ ይመሰላል፡፡ ሁላችንም የስኳር ከረሜላ በጣም ጣፋጭ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህንንም ጣፋጭ ከረሜላ ግን፡ በጆንደስ ለተበለከ ሰው ብትሰጡት፡ መራራ ሁኖ ያገኘዋል፡፡ ሁላችንም ጣፋጭ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን በጆንደስ የታመመው ሰው፡ ጣፋጩን ከረሜላ መራራ ሁኖ ያገኘዋል፡፡ ሁላችንም ይህንን ሁኔታ እናውቃለን፡፡ ታድያ ይህንን ሩቺ፡ የመንፈሳዊ ትምህርት የመስማትን ጣእም፡ “ቫሱዴቫ ካትሃ ክርሽና ካትሃ” ይህንን ጣእም፡ በአለማዊ ኑሮ የተበከለው ሰው በቀላሉ ሊያገኘው አይችልም፡፡ ይህንንም ጣእም ለማግኘት፡ አንዳንድ ተቀዳሚ ደረጃዎች መወሰድ አለባቸው፡፡ ይህስ ምንድን ነው? በመጀመሪያ ደረጃ፡ ምስጋና ማቅረብን ያሰፈልጋል፡፡ “ይህ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው” የሚል ስሜት ያሰፈልጋል፡፡ “አዶ ሽራድሃ ሽራዳድሀና” ሽራድሃ ወይንም ዕምነት እና ምስጋና ማቅረብን ያሰፈልጋል፡፡ ይህ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ ከዚያም ሁለተኛው፡ ”ሳድሁ ሳንጋ“ (ቼቻ ማድህያ 22.83) ማለትም ከመንፈሳዊ ህብረት ጋር መቀላቀል ”ከነዚህ ከሚዘምሩ እና ክርሽናን ከሚያወድሱ ሰዎች ጋር ልቀላቀል“ ማለት ያሰፈልጋል፡፡ እነርሱም ጋ ሂጄ: ልቀመጥ እና በጥሞናም ላዳምጥ ማለት ያሰፈልጋል፡፡ ይህ ”ሳዱ ሳንጋ“ ይባላል፡፡ ከክርሽና ድቮቲዎች ጋር ወይንም አገልጋዮች ጋር መቀላቀል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሁለተኛው ደረጃ ነው፡፡ ሶስተኛው ደረጃ ደግሞ፡ ”ብሀጀና ክሪያ“ ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ መንፈሳዊ ህብረት ሲዳብር፡ ተማሪ ለመሆንም ይሻል፡፡ በዚህም ሂደት ብዙ አመልካቾች ይፈራሉ፡፡ እንዲህም ይላሉ፡ ”ፕራብሁፓዳ ፈቃድህ ከሆነ እባክህ የአንተ ተማሪ አድርገን“ ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ይህም የ ”ብሃጃና ክሪያ“ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ ብሃጃና ክሪያ ማለትም በአምላክ ጌታ አገልግሎት ላይ መሰማራት ማለት ነው፡፡ ይህ ሶስተኛው ደረጃ ነው፡፡