AM/Prabhupada 0071 - በጥሩ ሁኔታ አስተዳድሩ፡፡
Room Conversation With French Commander -- August 3, 1976, New Mayapur (French farm)
እኛ ግድ የለሽ፣ ደንታ የሌለን እና የምናባክን የዓብዩ ጌታ ልጆች ሆነን በምድር ላይ እንገኛለን፡፡ የዓብዩ ጌታ ልጆች ስለመሆናችን ጥርጥር የለውም፡፡ ቢሆንም ግን በአሁኑ ግዜ በማባከን እና ለዚህም ግድ የለሽ ሆነን እንገኛለን፡፡ በጣም ብርቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ሕይወታችንን በማባከን ላይ እንገኛለን፡፡ ለዚህም ምንም ደንታ የሚሰጠን አይመስልም፡፡ ስለዚህ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ የተቋቋመው ይህንን ግድ የለሽነትን ለማስተካከል ነው፡፡ የሰውን ልጅንም ወደ ሀላፊነቱ እንዲመለስ ለማድረግ ነው፡፡ ይህም እንቅስቃሴውን ሁሉ ወደ ዋነኛው ቤቱ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመመለስ እንዲችል ነው፡፡ ይህም ማለት በክርሽና ንቃት አማካኝነት ማለት ነው፡፡ ቢሆንም ግን ሰዎች ደንታ የማይሰጣቸው ይመስላል፡፡ ስለ ዓብዩ ጌታ ንግግር ማድረግ ስንጀምርም፤ ወዲያውኑ መሳቅ ይጀምራሉ፡፡ “ኦ ይህ የአምላክ ውይይት ስሜት አይሰጠንም፡፡” በማለት ይሸሻሉ፡፡ ይህም ታላቁ ግድ የለሽነት ነው፡፡ ሕንድ አገር ስለ ዓብዩ ጌታ በጥብቅ እና በአንገብጋቢነት የምትከታተል አገር ነበረች፡፡ በአሁኑ ግዜም በጥብቅ የምትከታተል ሆና ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ግዜ ያሉ የዓለም መሪዎች ግን ሕንዶች ስለ ዓብዩ ጌታ በማሰብ እና በመከታተል ብቻ ሕይወታቸውን በማባከን ላይ ናቸው ብለው ያስባሉ፡፡ ሕንዶች እንደ አሜሪካውያን እና እንደ አውሮፓውያኖች ሀብትን ለማስፋፋት በጥረት ላይ አይገኙም ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ ነው አሁን ያለንበት ደረጃ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ትምህርቱን ለማከፋፈል አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ቢሆንም ግን ለሰው ልጅ ብዙ ለማድረግ የምንችለው ነገር ይኖራል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃትን በማስተማር እና እንቅስቃሴውን በማስፋፋት ነው፡፡ እድለኞች የሆኑትም ሰዎች ሁሉ ወደ እዚህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ በመቅረብ ንቃቱን በጥብቅ ለመከታተል ይበቃሉ፡፡ ስለነዚህም ግድ የለሽ እና የሚያባክኑ ዓይነት ሰዎች ብዙ ምሳሌ ለመስጠት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የተከማቸ ነዳጅ አለ እንበል፡፡ ነዳጅ ከተገኘም ያለ ፈረስ መኪናን በመንዳት ለማሽከርከር ይቻላል የሚለው መረጃም አላቸው እንበል፡፡ በዚህም ምክንያት በሚልዮን የሚቆጠሩ መኪናዎችን ሲያመርቱ እና ምድር ያላትን ነዳጅ ሁሉ ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ ይህም ግድ የለሽነት ነው፡፡ ይህም ነዳጅ ባክኖ ሲያልቅ ወደ ሀዘን ይገባሉ፡፡ ማለቁም የማይቀር ነውና፡፡ እንዲህ ዓይነቱም ግድ የለሽነት ሲካሄድ እናያለን፡፡ ለምሳሌ ለአንድ ቀበጥ ልጅ አባቱ ውርስ ትቶለት ይሆናል፡፡ ይህም ሀብት በእጁ እንደገባ ወዲያውኑ ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ይህም ግድ የለሽነት ነው፡፡ ገላውም ትንሽ አቅም ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለ ወሲብም ትንሽ ጣእም ሲኖረው፤ ያለውን ሀብት እና ሀይል ለማባከን ይበቃል፡፡ አእምሮውም ባዶ በመሆን በትክክል ሲያስተውል አይታይም፡፡ ከ12 ዓመት ጀምሮ 30 ዓመት እስኪሆነው ድረስ ሁሉንም ነገር ሊያባክን ይችላል፡፡ ከዚያም ሀይል ሊያጣ ያችላል፡፡ በልጅነታችንም ግዜ፤ ማለትም ጠና ላለ ሰው ከ80 ዓመት በፊት ወይንም ከ100 ዓመት በፊት፤ ምንም ዓይነት መኪናዎች አልነበሩም፡፡ በአሁኑ ግዜ ግን በመላው ዓለም በየትኛውም አገር ላይ ብታዩ በሺህ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ መኪናዎችን ታገኛላችሁ፡፡ ይህም ግድ የለሽነትን ያሳያል፡፡ ከመቶ ዓመት በፊት ያለ መኪና ለመኖር እንችል ነበር፡፡ በአሁኑ ግዜ ግን ያለመኪና ለመኖር የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህንንም በመሰለ መንገድ ያላስፈላጊነት የቁሳዊ ገላችንን ምቾት ከፍ ለማድረግ የቁሳዊ ነገሮች አስፈላጊነትን ስናሳድግ እንገኛለን፡፡ ይህም ደንታ ያለመኖር እና ግድ የለሽነት ያሳያል፡፡ ይህንንም ግድ የለሽነት የሚደግፉ የአገር መሪዎች ሁሉ ልክ እንደ ጥሩ መሪዎች ሆነው ይታያሉ፡፡ እንዲህስ የሚል ማን አለ? “ይህንን ስሜት የማይሰጥ ስራ አቁሙ፡፡ ወደ ክርሽና ንቃትም ተመለሱ፡፡” የሚል ሰው ማን አለ? ማንም ሰው ስለዚህ ደንታ የሚሰጠው አይመስልም፡፡ “ አንድሀ ያትሀንድሄር ኡፓኒያማናስ ቴ ፒሻ ታንትርያም ኡሩ ዳምኒ ባድሃህ” (ሽብ፡ 7.5.31) ይህም ዓይነ ስውር ሌላ ዓይነ ስውሮችን እንደሚመራቸው ሆኖ ይመሰላል፡፡ እያንዳንዳቸውም በተፈጥሮ ሕግጋት በጥብቅ ተጠፍረው የታሰሩ መሆናቸውን አልተረዱም፡፡ ይህም የተፈጥሮ ሕግ እንዴት እንደሚሰራ ባለማወቅ በድንቁርና ላይ ይገኛሉ፡፡ ምንም እውቀቱ የላቸውም፡፡ የግዜው ስልጣኔም ይኅው ነው፡፡ ተፈጥሮ የራስዋን ሕግጋት ፈለግ ተከትላ ስራዋን ትፈጽማለች፡፡ ስለዚህም የተፈጥሮ ሕግጋት ደንታ ቢሰጥህም ወይንም ባይሰጥህም የራስህ ጉዳይ ነው፡፡ ቢሆንም ግን የተፈጥሮ ሕግ ሳይቀየር የሚሰራ ነው፡፡ “ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉኔይህ ካርማኒ ሳርቫሻሀ” (ብጊ፡ 3.27) እነዚህ ተንኮለኞች ግን የተፈጥሮ ሕግ እንዴት እንደሚሰራ የተረዱ ሰዎች አይደሉም፡፡ ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ ለመሆን በሞኝነት እና በሰው ሰራሽነት ከሚፈለገው በላይ ትግል ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ይህም ሳይንሳቸው ነው፡፡ ይህም የተንኮለኛ ሳይንስ ነው፡፡ የተፈጥሮን ሕግ ለመቋቋም የማይቻል ነው፡፡ እነርሱ ግን ተፈጥሮን ለመቋቋም በታላቅ ትግል ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ተንኮለኝነት እና እብደት ይባላል፡፡ ሳይንቲስቶችስ እንዲህ አይሉምን? "የተፈጥሮን ሕግ ለማሸነፍ ጥረት እያደረግን ነው፡፡“ ተንኮለኛ፡፡ ይህንንስ ለማድረግ ፈፅሞ የማይችሉት ነገር ነው፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ዓይነቱ ተንኮለኝነት ሲካሄድ እናየዋለን፡፡ ሲያጨበጭቡም እናያቸዋለን፡፡ ”ኦ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በጣም ጥሩ፡፡“ ”ኦ ወደ ጨረቃ በመጓዝ ላይ ነህ፡፡“ ነገር ግን ከዚያ ሁሉ ትግል በኋላ ወይኑ መራራ ሆኖ ይገኛል፡፡ ”ጠቃሚ ሆኖ አይገኝም፡፡“ ይኅው ነው፡፡ የቀበሮውንስ ታሪክ ታውቁታላችሁን? ወይኑንም አውርዶ ለመብላት ይዘላል፡፡ ይዘላል፡፡ ይዘላል፡፡ ማውረድ ሲያቅተው ግን ”ይህ ወይን ዋጋ የለውም፡፡ መራራ ነው፡፡ ምንም ጥቅም የለውም፡፡“ ብሎ ትቶት ይሄዳል፡፡ (ሳቅ) እነዚህም ሳይንቲስቶች በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ቀበሮዎች በመዝለል ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ቀበሮዎች እንዴት አድርገው ጥቅም ለሌለው ነገር በመዝለል ላይ እንዳሉም እናያቸዋለን፡፡ (ሳቅ) ስለዚህ የዓለም ህዝብ እነዚህን ቀበሮዎች በመከተል እንዳይሳሳት በማስተማር ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህ አዋቂ ሁኑ፡፡ የክርሽናም ንቃት ይኑራችሁ፡፡ ይህም የሕይወታችሁን ዓላማ እና ግብ እንድትደርሱበት ያደርጋችኋል፡፡