AM/Prabhupada 0303 - በመንፈስ የተሻገረ “በመንፈስ የተሻገርክ ነህ”

Revision as of 13:03, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture -- Seattle, October 2, 1968

ፕራብሁፓድ፡፡ ቀጥል ታማላ ክርሽና፡ "የአንተ ደረጃ መንፈሳዊ ነው፡፡" ፕራብሁፓድ፡ መንፈሳዊ "አንተ ከዚያም ባሻገር ነህ፡፡" ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጿል፡፡

"ኢንድሪያኒ ፓራኒ አሁር ኢንድሪዬብህያህ ፓራም ማናሀ ማናሳስ ቱ ፓራ ቡድሂር ዮ ቡድሄህ ፓራታስ ቱ ሳሀ"
(ብጊ፡3 42)

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ገላ ምን እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ ይህም ገላ ማለት በስሜቶች የተመሰረተ ነው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከምናየው ገላ ባሻገር ስንሄድ ሀሳብን ከስሜቶቻችን ፍላጎቶች ሁሉ መሀከል ተቀምጦ እናየዋለን፡፡ ይህም ሀሳብ ንቁ ካልሆነ በስሜቶቻችን ግፊት ብቻ እንቅስቃሴ ውስጥ ልንገባ አንችልም፡፡ ሰለዚህም እንዲህ ተብሏል፡፡ "ኢንድሪየብህያህ ፓራም ማናሀ" ሰለዚህ ከእነዚህ ስሜቶቻችን ባሻገር ሀሳብ አለ፡፡ ከዚህም ሀሳብ በላይ አእምሮ አለ፡፡ ከዚህም ከአእምሮ በላይ ደግሞ ተሸጋግራ የምትገኘው ነፍስ አለች፡፡ ይህንን በትክክል እንድንረዳው ይገባናል፡፡ ቀጥል ታማላ ክርሽና፡ "የላቀ ሀይል ያለው ክርሽና በመሰረቱ አብይ እና መንፈሳዊ ነው፡፡ በቁሳዊ ዓለም የሚገኘው ሀይሉ ደግሞ ዝቅተኛው ቁሳዊ ሀይሉ ነው፡፡" እኛ ነፍሳት ደግሞ በዚህ የላቀው መንፈሳዊ ሀይል እና በዝቅተኛው የቁሳዊ ሀይል መሀከል የምንገኝ ነን፡፡ ሰለዚህ ደረጃችን ማእከላዊ ነው፡፡ በሌላም አነጋገር እኛ የምንመደበው ከክርሽና የማእከላዊ ሀይሉ መደብ ውስጥ ነው፡፡ እኛ ከክርሽና ጋር በአንድ ግዜ ውስጥ የተለያየንም ስንሆን አንድም ሆነን እንገኛለን፡፡ መንፈስ እንደመሆናችን ከክርሽና ተለይተን አንታይም፡፡ ነገር ግን እኛ በጣም ያነስን የክርሽና ወገን እና ቅንጣፊ በመሆናችን ከእርሱ የተለየን ሆነን እንገኛለን፡፡ ፕራብሁፓድ፡ እዚህም የተጠቀምንበት አንድ ቃል አለ፡፡ በዳርቻ የሚገኝ ሀይል፡፡ የዳርቻ ሀይል ትክክለኛ የሳንስክሪት ቃሉ "ታታስትሀ" ይባላል፡፡ ለምሳሌ ከመሬቱ መጨረሻ ላይ ባህሩ ይገኛል፡፡ እዚህም የዳርቻው መሬት ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በፓስፊክ ውቅያኖስ ዳርቻ ስትሄዱ መሬት ታያላችሁ፡፡ ይህም የዳርቻ መሬት አንዳንድ ግዜ በውሀ ተሸፍኖ አንዳንድ ግዜ ደግሞ ግልፅ የሆነ መሬት ሆኖ ይገኛል፡፡ ይህ የዳርቻ መሬት ባህርይ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛ ነፍሳት ሁሉ ምንም እንኳን በመሰረታችን ከአብዩ አምላክ ጋር አንድነት ቢኖረንም አንዳንድ ግዜ በማያ (የቁሳዊ ዓለም ምትሀት) ተሸፍነን ስንገኝ አንዳንድ ግዜ ደግሞ ነፃ ሆነን እንገኛለን፡፡ ሰለዚህ እኛ ያለንበት ደረጃ በዚህ የዳርቻ አቅዋም ላይ ይገኛል፡፡ የእኛ ደረጃ ምን እንደሆነ በትክክል ስንረዳ ደግሞ ..... ልክ እንደሰጠሁት ምሳሌ በትክክል ልትረዱት ሞክሩ በባህሩ ዳርቻ አንዳንድ ግዜ በውሀ የተሸፈነ እና አንዳንድ ግዜ ደግሞ ግልፅ የሆነ መሬትን እናያለን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም አንዳንድ ግዜ በማያ ወይም በቁሳዊው ዓለም ዝቅተኛው ሀይል ተሸፍነን እንገኛለን፡፡ አንዳንድ ግዜ ደግሞ ነፃ ሆነን እንገኛለን፡፡ ሰለዚህ የእኛ ሀላፊነት ያንን ነፃ የሆነውን ደረጃ አለመልቀቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ግልፅ በሆነው መሬት ላይ ውሀ የለም፡፡ ይህም ከባህሩ ራቅ ብላችሁ ከተገኛችሁ ነው፡፡ በዚህም አካባቢ የባህሩ ውሀ አይገኝም፡፡ የሚታየውም መሬት ብቻ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እራሳችሁን ከዚህ ከቁሳዊ ዓለም ህልውና አውጥታችሁ ወደ መንፈሳዊው መሬት ወይንም የክርሽና ንቃት ውስጥ ብተፀኑ በዚህ ደራጃ ላይ ሁሌ በነፃነት ላይ ትገኛላችሁ፡፡ ነገር ግን እራሳችሁን በዚህ በዳርቻ ላይ ካደረጋችሁት አንዳንድ ግዜ በማያ ትሸፈናላችሁ፡፡ አንዳንድ ግዜ ደግሞ በመንፈሳዊ ነፃነት ላይ ተገኛላችሁ፡፡ ይህንን ነው ማግኘት የሚገባን፡፡