AM/Prabhupada 0722 - ሰነፍ አትሁኑ፡፡ ሁልግዜ በስራ ተሰማሩ፡፡
Arrival Lecture -- Mexico, February 11, 1975, (With Spanish Translator)
እኔም እናንተን በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ብዙ የክርሽና ወገኖችን እያየሁ ነው፡፡ የክርሽና ንቃትንም ለመረዳት መጥታችኋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እነዚህን መመሪያዎች አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ሕይወታችሁም የተሳካ ይሆናል፡፡ መመሪያው እራሳችሁን ከዓላማዊ አንደበት ንጹህ ለማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሽተኛ ሲሆን ለመዳን እንዲችል እራሱን ከበሽታ ማጽዳት አለበት፡፡ ይኅውም የመቆጣጠርያ መመርያዎችን በመከተል ምግብን በመመምረጥ መድሀኒትን በመውሰድ የመሳሰሉትን ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ እኛም በዚህ በቁሳዊ አካል የተሸፈነ የዓለማዊ በሽታዎች አሉን፡፡ የዚህም በሽታ የመከራ ምልክቱ መወለድ መሞት ማርጀት እና መታተም ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ከዚህ ከቁሳዊ ዓለም ወጥመድ ኮስተር ብሎ ለመውጣት ከፈለገ እንደዚሁም እራሱን ከመወለድ ከመሞት ከማርጀት እና ከመታመም ለመዳን ከፈለገ የክርሽና ንቃቱን ማዳበር አለበት፡፡ ይህም ቀላል እና የሚቻል ነው፡፡ የምታውቀው ነገር ከሌለ ያለተማርክ ከሆነ እና ምንም ሀብት ከሌለህ በቀላሉ የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር ትችላለህ፡፡ የተማርክ ከሆንክ የሎጂክ ሰው እና ፋላስፋ ከሆንክ ደግሞ ወደ ሀምሳ የሚሆኑትን መፃህፍቶቻችንን ለማንበብ ትችላለህ፡፡ ወደ መቶ ገጽ የሚኖራቸው ወደ 75 የሚሆኑ መፃህፍቶች አሉ፡፡ እነዚህም መፃህፍት የታተሙት ፈላስፋዎችን ሳይንቲስቶችን መምህራንን የክርሽና ንቃት ምን እንደሆነ ለማስተማር ነው፡፡ እነዚህም መፃህፍት በእንግሊዘኛ እና በሌላ የአውሮፓውያን ቋንቋዎች ታትመው ይገኛሉ፡፡ ሰለዚህ ተጠቀሙባቸው፡፡ በዚህ ቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የደይቲ ስግደት እና በቀን እስከ 5 ሰዓት የሚሰጠውን ትምህርት ተከታተሉ፡፡ ልክ በትምህርት ቤቶች እና በኮሌጆች እንደምናየው በየግዜው የሚሰጡ ትምህርቶች አሉ፡፡ ይህም እሰከ 45 ደቂቃ ይሆናል፡፡ ከዚያም 5 ደቂቃ እረፍት እንደገና ደግሞ 45 ደቂቃ ትምህርት በመሆን ይካሄዳል፡፡ እኛም በቂ የሆኑ ለጥናት የሚሆኑ ርእሶች አሉን፡፡ እነዚህንም መፃህፍቶች ሁሉ የምናጠና ከሆነ ለመጨረስ ብቻ ወደ 25 ዓመት ሊፈጅብን ይችላል፡፡ እናንተ ሁሉ ወጣቶች ናችሁ፡፡ የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ጊዜያችሁን እነዚህን መፃህፍቶች በማንበብ እንድትጠቀሙበት ነው፡፡ በተጨማሪም በመዘመር በደይቲ ስግደት በመስበክ እና መጻህፍትን በመሽጥ እንድትሳተፉ ነው፡፡ ስንፍና እንዳይሰማቸሁ፡፡ ሁልግዜ በዚህ መንፈስ በመንቀሳቀስ ላይ ተገኙ፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ ክርሽናም በብሀገቨድ ጊታ እንደዚህ ብሏል፡፡ “ማም ሂ ፓርትሀ ቭያፓሽሪትያ ዬ ፒ ስዩህ ፓፓ ዮናያህ” ስትሪያሀ ቫይሽያስ ታትሀ ሹድራስ ቴ ፒ ያንቲ ፓራም ጋቲም (ብጊ፡ 9.32) “ይህ ሰው ይፈቀድለታል ይህቺ ሴት አይፈቀድላትም” እየተባለ ምንም አይነት ልዩነት ማድረግ አያስፈልግም፡፡ ክርሽና የሚለው “ማናቸውም ሰው” ስትሪያሀ ቫይሽያስ ታትሀ ሹድራስ የክርሽና ንቃትን ለመውሰድ የሚበቃ ሰው ሁሉ ከቁሳዊው ዓለም ወጥመድ ነፃ ለመሆን ይችላል። በዚህም ስርዓት ወደ ቤቱ ወደ አብዩ አምላክ ቤተ መንግስት ለመሄድ ይችላል፡፡ ሰለዚህ የዚህን የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ መመሪያ በመከተል በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ተሳተፉ፡፡ ይህም ስጋ ባለመብላት አግባብ በሌለው ወሲብ ባለመሰማራት የሚያሰክሩ እና ሱስ የሚያስዙ ነገሮችን ባለመውሰድ ቁማር ላይ ባለመሰማራት እና እስከ 16 ዙርያዎች የሚሆኑ የቅዱስ ስምን በመዘመር ይሆናል፡፡