AM/Prabhupada 0718 - ልጆች እና ተማሪዎችን ሁልግዜ መቆጣት ያስፈልጋል፡፡
Morning Walk -- February 1, 1977, Bhuvanesvara
ድቮቲ፡ ሽሪላ ፕራብሁፓድ ልክ እንደ መቀስ ምሳሌ የሰጠኅው እንዴት ሳይንቲስቶችን ክርሽናን እና ብሀገቨድ ጊታን እንዲቀበሉ ማስገደድ እንችላለን። ሳይንቲስቶችን እንዴት አድረገን ብሀገቨድ ጊታን እንዲቀበሉ ማስገደድ እንችላለን?
ፕራብሁፓድ፡ ትክክል ነው ማስገደድ ይገባናል፡፡ ይህም ትክክል ነው፡፡ ይህም ማስገደድ በትክክል መንፈስ ካልሆነ የግትርነት መንፈስ ነው፡፡ እውነት ከሆነ ማስገደድ ይቻላል። ለምሳሌ አባት ልጁን ማስገደድ ይችላል፡፡ “ትምህርት ቤት ሂድ” ምክንያቱም ያለ ትምህርት ሕይወቱ አስጨናቂ እንደሚሆን ያውቀዋል፡፡ ሰለዚህ ልጁን ማስገደድ ይችላል፡፡ እኔ ተገድጄ ነበረ፡፡ ትምህርት ቤት አልሄድም በማለት አስቸግሬ ነበረ፡፡ (ሳቅ) እናቴም አስገደደችኝ፡፡ አባቴ ብዙ አላስገደደኝም ነበረ፡፡ እናቴ ግን አስገድዳኝ ነበር፡፡ አንድ ሰው እኔን ጐትቶ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስድ ሰው አስቀምጣ ነበረ፡፡ ሰለዚህ ማስገደድ አስፈላጊ ነው፡፡ ጉሩክርፓ፡ እነዚህ ግን ባለስልጣኖችህ ነበሩ፡፡ ወላጆችህ ባለስልጣኖችህ ነበሩ፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን ጉሩክርፓ፡ ”ሳይንቲስቶች ግን እኛን እንደ ባለስልጣን አያዩንም፡፡ እኛም ከእናንተ ጋር እኩል ነን ይላሉ፡፡“ ”እንድየውም ከእናንተ በላይ እናውቃለን ይሉናል፡፡“
ፕራብሁፓድ፡ ይህም ሌላ ሞኝነት ነው፡፡ አባት እናት አሳዳጊዎች ሁሉ ለማስገደድ ይችላሉ፡፡ ስቫሩፕ ዳሞዳር፡ ታላቁን እውቀት ወይንም መረዳት ያለባቸውን አብይ እውቀት ልናሳያቸው ይገባናል፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ ልጁ ሞኝ ሊሆን ይችላል፡፡ አባት እና እናት ግን ልጃቸው ሞኝ ሆኖ እንዲቀር ቁጭ ብለው ለማየት አይገባቸውም፡፡ ለማስገደድ ይችላሉ፡፡ መንግስትም እንዲሁ ማስገደድ ይችላል፡፡ የወታደር ሀይል ለምን አለ? የፖሊስ ሀይል ለምን አለ? ከሕግ ውጪ ለመውጣት ከፈለግህ ህጉን በግድህ እንድትከተል ትገደዳለህ፡፡ ሀይል ያስፈልጋል፡፡
ድቮቲ፡ በመጀመሪያ ግን አንድ ተማሪ የትምህርት ጥቅም ምን እንደሆነ እንዲረዳ ይገባዋል፡፡
ፕራብሁፓድ፡ ልጅ ይህንን ለማየት አይችልም፡፡ ልጅ ተንኮለኛ ነው፡፡ በጫማ መመታት አለበት፡፡ ያንን ግዜ ለማየት ይችላል፡፡ አለበለዛ ለማየት አይችልም፡፡ ፑትራም ቻ ሺሽያም ቻ ታዳዬን ና ቱ ላላዬት (ቻናክያ ፓንዲት) “ልጆች እና ተማሪዎች ሁልግዜ መገሰፅ አለባቸው፡፡” ይህ የቻናክያ ፓንዲት ትምህርት ነው፡፡ “ጀርባቸውን መትቶ ሁሌ ማመስገን አያስፈልግም፡፡” ላላኔ ባሃቮ ዶሳስ ታዳኔ ባሃቮ ጉናህ “ሁሌ ጀርባ እየመታህ የምታመሰገን ከሆነ ልጁ ሊበላሽ ይችላል፡፡” “ነገር ግን የምትገስፀው ከሆነ ጥሩ ሰው እየሆነ ይመጣል፡፡” ስለዚህ የድቁና ተማሪም ሆነ ልጅ ሁልግዜ መገፀስ አለባቸው፡፡ የቻናክያ ፓንዲትም መመሪያ ይህ ነበረ፡፡ በጀርባ እየመቱ ማመስገን የለም፡፡ ጉሩክርፓ፡ ሰዎች መመስገንን ይፈልጋሉ፡፡ ማንም ሰው እንዲሰደብ ወይም እንዲጮህበት አይፈልግም፡፡
ፕራብሁፓድ፡ የድቁና ተማሪዎችም ደረጃ ይህ ነው፡፡ ቼይታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሏል፡፡ “ጉሩ ሞሬ ሙርክሀ ዴክሂ” (ቼቻ፡አዲ 7.71) ቼታንያ መሀፕራብሁ እራሱ አብዩ ጌታ ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበረ፡፡ “የእኔ ጉሩ መሀራጅ እኔን እንደ የአንደኛ ደረጃ ሞኝ እና ተንኮለኛ አድርጎ ያየኝ ነበረ፡፡” መገሰፅ አስፈላጊ ነው፡፡ ቻናክያ ፓንዲት፡ ታላቁ የሞራል አስተማሪ እንዲህ ብሎ መክሮ ነበረ፡፡ “ታዳዬን ና ቱ ላላዬት” “ሁልግዜ ገስጿቸው፡፡ አለበለዛ ይበላሻሉ፡፡” ስቫሩፕ ዳሞዳራ፡ አዋቂ የሆነው ልጅም ይኅው መገሰፅን እንደ በረከት አድርጐ ያየዋል፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡